Posts

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብቡን አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በአመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው 6 ሚሊዮን ብር ሲሆን  ከ9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሰበሰበብ መቻሉን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስራቅ በቴ ገልፀዋል ፡፡ የአመቱ እቅድ ክንውን አፈፃፀም 98 ነጥብ 2 ከመቶ መሆኑንና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ3 ሚሊዮን 61ዐ ሺህ 196 ብር ብልጫ ማሳየቱን ኃላፊው አስረድተዋል ፡፡ ገቢው ሊሰበሰብ የቻለው ከቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች መሆኑን አብራርተዋል ፡፡ ለገቢው መጨመር የግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብር የመክፈል ግንበዛቤ እያደገ መምጣት፣ የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነት መፈጠርና የወረዳው መስተዳደርና ባለድርሻ አካላት ከገቢ ሰብሳቢው ጽህፈት ቤት ጋር የተቀናጀ ሥራ በማከናወናቸው መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል ፡፡ በቀጣይ አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በማፈላለግ የተጀመረውን የ5 ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አቶ ምስራቅ መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/14NehTextN604.html

የደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን መሪር ሀዘን ገለፁ

  አዋሳ ነሐሴ 17/2004 በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ መስሪያ ቤቶችና ተቋማት አመራር አባላትና ሰራተኞች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ነዉ ። የደቡብ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ፣የክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ፣የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋምና የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ሠራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች በታላቁ መሪያችን ሞት ጥልቅና መሪር ሀዘን ተሰምቶናል ብለዋል ። ቢሮዎቹና ተቋማቱ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ ላይ እንዳስታወቁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከወጣትነት እድሜያቸዉ ጀምሮ እስከ እለተ ሞታቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ከድህነት ተላቆ በእድገትና ብልጽግና ጎዳና እንዲጓዝ ታላቅ ራእይ ሰንቀዉ የተነሱ ቆራጥና አስተዋይ መሪ ነበሩ ብለዋል ። የየቢሮዎችና የተቋማቱ ሰራተኞች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የአመራር ጥበባቸውን በመጠቀም ኢትዮጵያን በልማት ለማሳደግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አሁን ለደረሰንበት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ያበቁ ታታሪና ብልህ መሪ እንደነበሩ አስታዉቀዋል ። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ "ለመጪው ትውልድ ዕድገት፣ ብልፅግናና ልማትን እንጂ ድህነትን አናወርስም "በማለት በቆራጥነትና በታላቅ ኃላፊነት መንፈስ ሲሰሩ የቆዩ የለውጥ ሐዋሪያ ናቸው ሲሉ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ገልፀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኢትዮጵያ በአለም ከምትታወቅበት የተመፅዋችነትና የረሃብ ታሪክ እንድትላቀቅ በዓለም ትልቅ የልማት ተስፋ ሆነው ከሚታዩ የዓለም አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያደረጉ ጀግናና በሳል መሪ ነበሩ ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የእርሳቸዉን በጎ ተግባር በመከተል ብቃት ያለው የልማት ሠራዊት መሆን የሚችል በሁሉም መስክ የሰለጠነ የሰው

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ዕረፍት አስመልክቶ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሰጡት አስተያየት

Image
በመገናኛ ብዙኅን የሰማሁት ነገር እጅግ ልብ የሚነካና የሚያሳዝን ነው፡፡ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትልቅ ራዕይና አቅም የነበራቸው መሪ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ይኼ ነው የማይባል ጊዜያቸውን መስዋዕት አድርገው፣ አምባገነኑን የደርግ ሥርዓትን መክቶ ማሸነፍ የቻለ ፓርቲ መመሥረት የቻሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ ከዚያም በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ነው የማይባል የፖለቲካና የኢኮኖሚ መነቃነቅን የፈጠረ አቅም የነበራቸው ግለሰብ ነበሩ፡፡ ወደፊትም በኢትዮጵያ ውስጥ ረጅም ርቀትን ለመሄድ የሚያስችል አቅም የነበራቸው ግለሰብ ናቸው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ለኢትዮጵያ ካቀዱትና ይዘውት ከተነሱት ዓላማ አኳያ መታጣታቸው እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ በተረፈ እንደ አባት ደግሞ ለቤተሰቦቻቸው እጅግ ትልቅ እጦት ነው፡፡ ለአፍሪካ ማኅበረሰብም አፍሪካን በማስተሳሰርና አንድነትን በማምጣት፣ በልማት መስመር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ቀላል የማይባል ሚና የተጫወቱ ግለሰብ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ስናያቸው እንደ አገር መሪ ይዘውትና ሰንቀውት የተነሱት ነገር ረጅም ርቀት የሚወስደን መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ወደፊትም ቢሆን በጀመሩት ነገር ላይ ተጨማሪ ሥራ ለመሥራት አቅም የነበራቸው ግለሰብ ነበሩ፡፡ እስከዛሬ ድረስ የሰበሰቡት ዕውቀት፣ ያከማቹት ግንዛቤና ተሞክሮ ወደሚቀጥለው ኃይል ተላልፎ አለማየትም ትልቅ እጦት ነው፡፡ በቀጣይ የሚጠበቀው ነገር ከኢሕአዴግ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ ላይ በሰፈረው መሠረት ኢሕአዴግ የሥልጣን ሽግግሩን በአግባቡ መወጣት አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ፣ በማያሻማና በሚታይ ሁኔታ መሆን አለበት እላለሁ፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ አገርን በማልማትና በማሳደግ ሒደት ውስጥ ቀዳዳ እንዳይኖረው

‹‹መለስን መተካት ከባድ ነው››

ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ‹‹የተጀመረው ልማት እንዲቀጥል አደራ›› የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኑዛዜ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕልፈት ምክንያት በተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲሠሩ ኃላፊነት የተጣለባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ‹‹መለስን መተካት ከባድ ነው›› አሉ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠል ግን አዲሱ አመራር ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ትናንት አመሻሽ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ‹‹ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደ ሻማ ቀልጠዋል፤›› ብለዋል፡፡ ላለፉት 38 ዓመታት በሰው ልጅ ታሪክ የሚጠቀስና በብቃት የሚፈለግባቸውን መሥራታቸውን ገልጸዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕልፈትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ ከፍተኛ ሐዘን እንደተሰማው ተናግረው፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘለዓለም በታሪክ ሊዘክራቸው የሚገባ መሪ ነበሩ፤›› ብለዋል፡፡ በእሳቸው አመራር የተገኘው ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማስቀጠል አዲሱ አመራር ቃል ኪዳን የሚገባበት ፈታኝ ጊዜ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ ‹‹በእሳቸው አመራር የተጀመረው የአመራር መተካካት ሒደት አይደናቀፍም ወይ?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ሒደቱ በጥናት ላይ የተመሠረተና በኢሕአዴግ ውስጥ ሙሉ መተማመን ላይ የተደረሰበት ስለሆነ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መሞት የሚደናቀፍ አይሆንም በማለት፣ በእሳቸው ጊዜ የተጀመረው የአዲሱ ትውልድ የአመራር መተካካት በብቃት እንደሚከናወን አስረድተዋል፡፡ በማገገም ላይ ሳሉ ከአራት ቀናት በፊት ኢንፌክሽን አጋጥሟቸው ሕይወታቸው አደጋ ላይ እስኪወድቅ ድረስ በስልክ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር በተደጋጋሚ መ

የሃዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ድንገተኛ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ

አዋሳ ነሐሴ 16/2004 የሃዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ሞት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡ ኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጠንካራ፣ ስራ ወዳድና የዓላማ ጽናት የነበራቸዉ ቆራጥ መሪ በመሆናቸው ያቀዱት ዕቅድ ያለሙት ዓላማ ሁሉ ውጤት ሊያስገኝ ችሏል፡፡ ዜጎች በራስ በመተማመን በአብዛኛው በቴክኒክና ሙያ በመሰማራ ሥራ እየፈጠሩና ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በተቀመጠው አቅጣጫ ብዙ ዎች ሃብትና ንብረት በማፍራት የሀገር ኩራት እስከመሆን ደርሰዋል ብለዋል ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከድህነት እንዲላቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ውጤት በመሆኑ መልካም ስራቸዉ ህያዉ ሆኖ እንደሚኖር የኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች አስታዉቀዋል ። ታላቁ መሪያችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለኢትዮጵያ ሀዝብ እድገትና ብልጽግና የሚበጁ መሰረቶችን የጣሉ ብሩህ አዕምሮና አርቆ አሳቢ መሪያችንን በሞት መነጠቃችን ጎድቶናል፡ ብለዋል ። የእሳቸው ዕቅድና ስትራቴጂ ተከትለን ለአገራችን እድገትና ብልጽግና በበለጠ ጥንክረን ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን አየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸውና ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን ብለዋል ፡፡