Posts

በአንዳንድ የሲዳማ ወረዳዎች በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መታሠራቸውና ቀጥለው ባሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እነሽፈራው ሊፈጽሙ ያሉት ክህደትና በህዝባችን በኩል መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች

የዚህ መልዕክት በጣም አጭር የሆነው ክፍል ከጉዳዩ አንገብጋቢነትና አጣዳፊነት አንጻር አስቀድሞ በጣም ባጠረ መልክ በ 2 ገጽ ተለቋል፡፡ ነገር ግን 2 ቱ ገጽ የተፈለገውን መልዕክት አሟልቶ ማስተላለፍ ስለማይችል ይህ ጽሁፍ እንዲዳረስ ለማድረግ ተወስኗል፡፡ የተከበራችሁ አባቶቻችን ( ሽማግሌዎች ) ፣ የተወደዳችሁ ተማሪዎች፣ የተከበራችሁ ነጋዴዎችና አርሶአደሮች፣ ውድ ምሁራን አሁን ያለንበት ወቅት ከምን ጊዜውም በላይ ፈታኝ መሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ ያለነው ከምን ጊዜውም በላይ መብታችን ተረግጦ፣ ህገ - መንግሥታዊ ጥያቄያችንንና ክልል ለመሆን ያስተላለፍነው ውሳኔያችንን ተከልክለን ባለንበት ሁኔታ ነው፡፡ የህዝብ ቁጣ ተባብሶ ባለበት ሁኔታ አሁንም የባሰ ክህደት ሊፈጽሙ እየሠሩ መሆኑ ስለተደረሰበት ይሄንን መልዕክት ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ እነሽፈራው ከየወረዳው ሁሉም ቀበሌዎች ቢቻል የራሱ ዘመድ የሆኑና ታማኝ የሆኑ ሽማግሌዎችን ካልተቻለም የዋህ የሆኑና ለማታለል የሚመቹ ሰዎችን ወደ ሐዋሳ ጠርተዋል፡፡ ዋና የማደናገሪያ አጀንዳቸው፡ - የህዝብ ጥያቄው ተመልሷል፡፡ በከተማው በሁሉም የሹመት ቦታዎች የሲዳማ ተወላጆች ተሹመውበታል፡፡ የክልል ጥያቄ ለማንሳት ግን አሁን ጊዜው አይደለም አይጠቅመንም፡፡ ስለዚህ ተውት የሚል ነው ፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ይሄንን ሴራ የጠነሰሱት ከሁሉም ቀበሌያት ያን ሁሉ አመራርና የተገኘ ሽማግሌ ሁሉ ጠርተው ሲዳማን የሚወክል ሰፊ ህዝብ የተስማማ ለማስመሰል የተለያዩ የዜና አውታሮችን ( የመገናኛ ብዙሃንን ) ጠርተው የተለመደውን ውሸታቸውን ሊያስተጋቡ ተዘጋጅተው ነው፡፡ እዚህ ጋ ልብ ልንል የሚገባው ተሰብሳቢዎች የተናገሩት ሳይሆን የሚተላለፈው በዋናነት የውሸትና

ሲዳማ ዞን “አስተዳዳሪ” ሚሊዮን ማቴዎስ ሐምሌ 04/2004 የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫን በተመለከተ ህዝቡ ያለውን ስሜት ለመግለጽ የተሰጠ መግለጫና አቅጣጫዎቻችን

ሲዳማ ህዝብ ክልል ለመሆን ያስተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ ሰሞኑን የዞኑ “አስተዳዳሪ” ሚሊዮን ማቴዎስ በሐምሌ  04/2004  እትም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ደኢህዴን ጋዜጣ ላይ እንደወትሮው የጓዶቹ መግለጫዎችና ዜናዎች ሁሉ ንቀት የበዛበትና ተራ ስድብ ያዘለ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ የጋዜጣው ተነባቢነት ከሚገመተው በላይ መጥበቡና በአጠቃላይ በህዝብ ዘንድ እንኳንስ አሁን ባለንበት ሁኔታ ቀድሞውንም ቢሆን ተቀባይነት የለሌው ከመሆኑ የተነሳ ወደሰፊው ህዝብ ጆሮ መድረስ በነበረበት ፍጥነት በሰፊው ባይደርስም ከአጀንዳው አንገብጋቢነት አንጻር አሁን የመነጋገሪያ ርዕስ በመሆኑ ይሄንን ምላሽ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ጋዜጣ በፊት ገጹ ላይ  “የሐዋሳ ከተማ ነዋሪውን ህዝብ የሚወክል አመራር እንዲኖሩት የቀረበውን አቅጣጫ በመቃወም በቅርቡ የሐዋሳ ከተማ ተሸጠች የሚል ውዥምብር በመንዛት ድብቅ አላማቸውን ለማሳካት ሲሯሯጡ የነበሩ ፀረ - ልማት ኃይሎች በመላው ህብረተሰብ ትብብርና በድርጅቱ የጠራ መስመር ሊከሽፍ ችሏል”  በማለት የነበረውን የህዝብ ቁጣ “ውዥምብር” ብለው በማጣጣል እርሱም ቢሆን በሲዳማ ህዝብና በድርጅታቸው መክሸፉን አስነብበውናል፡፡ እዚህ ላይ ተቃውሞው መነሻ እንዳለው ካለመካዳቸውም በላይ በተቃውሞው የተሳተፉት እነርሱ እንደሚሉት “ፀረ - ልማት ኃሎች” ሳይሆኑ ሰፊው የሲዳማ ህዝብ መሆኑን “ውዥምብር” የሚለው ቃላቸው ያሳብቅባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ጥቂት “ፀረ - ልማት ኃሎች” “ውዥምብር” መፍጠር አይችሉምና፤ ሊፈጥሩ የሚችሉት ሹክሹክታ፣ ሀሜትና ጥቂት “ንፋስ” ነው፡፡ “ውዥምብር” ሊኖር የሚችለው ሃይለኛ የሆነ እንቅስቃሴና ተቃውሞ ሲኖር ነው፡፡ ይሄንንም እውነታ ለመግለጥ እየሞከርን ያለነው ከሲዳማ ውጭ ላሉ አንባቢያን

የሲዳማ ፊቼ በኣል በደማቅ ሁኔታ በሃዋሳ ከተማ ተከብሮ ዋለ፤ ቁጥሩ ከመቶ ሺ በላይ ህዝብ ጉድማሌ ላይ ተገኝተዋል

Image
በዛሬው እለት ከሃያ ኣንዱም የሲዳማ ወረዳዎች እና ከከተማ ኣስተዳደሮች የተሰባሰበው ህዝብ የሲዳማን ኣዲስ ኣመት የፊቼን በኣል በደማዊ ሁኔታ ኣክብሯል። ከጠዋት ጀምሮ ከየወረዳዎች ወደ ሃዋሳ የተመመው ህዝብ እንደተለመደው ከተማዋን በጭፈራ ያደመቃት ሲሆን፤ ሃዋሳ የብሄሩን ባህል በሚያንጸባርቁ ልብስ ለባሾች ተሞ ልታ ውላለች። ጉድማሌ ላይ በነበረው የበኣሉ ኣካባበር ስነ ስርኣት ላይ የተገኙት የብሄሩ ሽማግሌዎች በህላዊ መንገዱን በጠበቀ መልኩ መልካም ኣዲስ ኣመት ለመላው የሲዳማ ህዝብ የተመኝተዋል። በደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኣሉ ላይ ተገኝተው መልካም ኣዲስ ኣመት ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ በጠለፋን በሌሎች ጎጂ ባህሎች ላይ እና እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር ለማድረግ የያዙት እቅድ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ምክንያት ሳይሳከ ቀርተዋል። በበኣሉ ላይ የነበረው ህዝብ በወቅታዊ የሲዳማ ክልል ጥያቄ ላይ የተለያዩ መልእክቶች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በጭፈራ መልክ ያስተላለፈ ሲሆን፤መልእክቶቹም በክልል ኣስፈላጊነት ላይ ያጠነጠኑ ነበሩ። ከጉዱማሌ ላይ ተሰብሰቦ የነበረው ህዝብ በኣሉን በየቤቱ ከጎሮቤት፤ወዳጅ ዘመድ ጋር በጋራ ለማክበር ወደየቤቱ የተመለስ ሲሆን፤ ምንም ኣይነት የጸጥታ ችግር ኣለመከሰቱ ተሰምቷል።