በ5 አመቱ (2002-2007) የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና አቶ አለማየሁ አሰፋ በሲዳማ ህዝብ ላይ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደባ ለመፈጸም ያዘጋጁት ምስጥራዊ እቅድ ተጋለጠ
Top secret /unclassified Dossi / ከውስጥ ኣዋቂ ምንጭ(ሲዳማ ዊኪሊክ) የ5 አመቱ (2002-2007) ለሲዳማ የታቀደ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድና ውይይትና ውሳኔ ማስታወሻ፡- 1) የዚህ ዕቅድ ውይይትና ውሳኔ ፋይል በከፍተኛ ሚስጥር የሚጠበቅ ሆኖ ለኔም የደረሰኝ በጣም ቅርብ ከሆነው ጓደኛዬና ከሁሉም በላይ ለሰው ልጅ ማንነትና መብት ከሚቆረቆር ዜጋ ነው፡፡ 2) ውይይቱ የተካሄደው በሶስት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሲሆን እነሱም፡- አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና አቶ አለማየሁ አሰፋ ናቸው፡፡ ቦታው በኃ/ማሪያም ደሳለኝ ቢሮ አ/አበባ ነው፡፡ ውይይቱ የተደረገው ከአራት ወር በፊት ሲሆን ዕቅዱ የተነደፈው በ2002ዓ.ም ሆኖ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእቅዱ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሆኖ የዚህኛው ውይይት ውሳኔ ካለፈው በበለጠ ተግባራዊ ስለሚደረግበት ሁኔታ ነው፡፡ 3) የውይይቱ ውሳኔ ሙሉ ይዘቱ ለሌሎች አምስት ም/ፕረዝዳንቶች ባሉት ብቻ የተገለፀው በአቶ ሽፈራውና በአቶ አለማየሁ አሰፋ ሲሆኑ ሌሎቹ የካብኔ አባላት ግን ሙሉውን ውሳኔ ሳይሆን ለጊዜው ተግባራዊ ለማድረግ የፈለገውን ውሳኔ ብቻ ተራ በተራ ነው፡፡ 4) የትኛው ውሳኔ በምን ጊዜ በአጀንዳነት ተዘጋጅቶ ለታችኛው መዋቅር መውረድ እንዳለበ የሚወሰኑት አቶ ሽራውና አቶ አለማየሁ ናቸው፡፡ 5) አንዳንድ ውሳኔዎች ለታችኛው መዋቅር በተለይም ለሲዳማ ካድሬዎች የማይወርዱ/የማይገለፁ/ እንዳሉ የሚገልፅ ቢሆንም የትኞቹ ውሳኔዎች እንደሆኑ ግን በግልፅ አያስቀምጥም፡፡ 6) ወደ ውይይቱና ወደ ውሳኔው ከመግባታቸው በፊት ሦስቱም እርስ በእርስ ሂስና ግለሂስ የተደራረጉ ሲሆን በኃ/ማሪያም ላይ የቀረበው ሂስ ‘አንተ የራስህ ወገ