በባህላዊ ማዕድናት ልማት ዘርፍ የታቀደውን ያህል ምርት አልተገኘም፤ ኣዲሱ እቅድ የሲዳማን ወርቅ ኣምራቾች ይጠቅም ይሁን?
የባህላዊ ማዕድናት ምርትና ግብይትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትናንት በተደረገው ውይይት እንደተመለከተው፤ ከጋምቤላ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎች የባህላዊ ማዕድናት ምርት ከዕቅድ በታች ነው። ከ2001 ዓ.ም ወዲህ የባህላዊ ማዕድናት ምርት ጭማሪ እያሣየ ቢሆንም በ2004 በጀት ዓመት ግን እንደታቀደው አይደለም። በዘርፉ የ2004 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2005 በጀት ዓመትን ዕቅድ ያቀረቡት በማዕድን ሚኒስቴር የባህላዊ ማዕድናት ምርትና ግብይት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ ታምራት ሞጆ እንደሚናገሩት፤ ከተወሰኑ ክልሎች በስተቀር የባህላዊ ማዕድናት ምርት በአብዛኛዎቹ ክልሎች የመቀነስ ሁኔታ ታይቶበታል። በዘርፉ የምርት መቀዛቀዝ እንደታየና የ2004 በጀት ዓመት አፈፃፀም 63 በመቶ እንደሆነ አመልክተው፤ ከገቢ አንፃር ከዕቅድ በላይ የሆነ አፈፃፀም መመዝገቡን ግን ያመለክታሉ። ለገቢው መጨመር እሴት ተጨምሮላቸው የሚላኩ ምርቶች ማደግና የወርቅ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር በአብነት ተነስቷል። እንደ አቶ ታምራት ገለፃ፤ በዘርፉ ችግሮች እያጋጠሙ ሲሆን በተለይም የሚመለከታቸው አካላት በሚፈለገው መንገድና ፍጥነት በቅንጅት አለመሥራት፣ ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት ማነስ፣ የባለሙያ መፍለስ፣ ፈቃዶችን በአግባቡ አለማስተዳደር ዋና ዋናዎቹ ችግሮች ናቸው። ሕገ ወጥ የማዕድናት ምርት እንዲሁም ወርቅ በባህላዊ መንገድ የሚመረትባቸው አብዛኞቹ አካባቢዎች የመሠረተ ልማት ችግሮች መኖራቸውም ሌሎች የዘርፉ ተግዳሮቶች ናቸው። «በዘርፉ ማኅበራትን ማደራጀት አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለሮያሊቲ ክፍያ ያለው የግንዛቤ ማነስ ተጨማሪ ችግር ነው» ሲሉም ይናገራሉ። በውይይቱ ተሣታፊ የሆኑ የክልል የማዕድን ቢሮ ተወካዮች በበኩላቸው እንደሚሉት፤ ለዘርፍ ዕድገት ከላይ እስከታች በቅን