Posts

በሀዋሳ ከተማ በበጀት ዓመቱ ከ6 ሺህ በላይ ባለቤት አልባ ውሾች ተወግደዋል

Image
ሀዋሳ፣ ሀምሌ 27፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ6 ሺህ በላይ ባለቤት የሌላቸው ውሾች መወገዳቸውን የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ፅፈት ቤት ገለፀ። ውሾቹ ባለቤት አልባና በእብድ ውሻ በሽታ ተጠቂ በመሆናቸው ምክንያት በሽታው በሰዎችም ላይ እየተስፋፋ የመጣበት ሁኔታ በመኖሩ ተወግደዋል ብሏል ፅፈት ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት። ከዚህ ባሻገርም በከተማዋ የሚገኙ ባለቤት ያሏቸው ውሾችን የእብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን ነው ያስታወቀው። በእብድ ውሻ የተነከሱ ሰዎችም በ48 ስአት ውስጥ ወደ ህክምና ተቋማት ከመጡ በሽታው የመዳን እድሉ ሰፊ በመሆኑ በከተማዋ የሚገኙ የጤና ተቋማት አገልገሎቱን እየሰጡ እንደሚገኙ ኤልሳቤጥ ካሳ ዘግባለች ።

የሲዳማ ዞን ካቢኔዎች የክልል ጥያቄውን ውድቅ ኣደረጉ፤ሲዳማ ለጊዜው ክልል ኣያስፈልገውም ኣሉ

ከሃያ ኣንዱም የዞኑ ወረዳዎች እና ከከተማ ኣስተዳደሮች የመጡት እነዚሁ ካቢኔዎች በወቅቱ የሲዳማ ዞን ኣንገብጋብቢ ኣጀንዳ በሆነው የሲዳማ ክልል ጥያቄ በተመለከተ ተወያይተዋል። በውይይቱም ላይ ስለ ክልል ኣስፈላጊነት እና ካቢኔዎቹ ጥያቄውን በተመለከተ በግል በያዙት ኣቋም ላይ ሂስ እና ግሌ ሂስ ኣካህደዋል። በግምገማው ላይ የዞኑ ካቢኔዎች የሃሳብ መለያየት የታየባቸው ሲሆን፤የክልል ጥያቄውን የምደግፉት የካቢኔ ኣባላት ኣብላጫውን ቁጥር ይዘው ነበር ተብሏል። መድረኩን ይመሩ የነበሩት ካላ ሽፈራው ሽጉጤ  ጽኑ ጸረ ሲዳማ ክልል ኣቋም ያንጸባረቁ ሲሆን፤ የክልል ጥያቄ የመላው የሲዳማ  ህዝብ ጥያቄ ሳይሆን ከኣገሪ ውጭ የሚኖሩት የጥቂት ግለሰቦች ጥያቄ ነው በማለት ኣጣጥለዋል። ከሂስ እና ከግሌ ሂስ ባኃላ ብዙዎቹ ሃሳባቸውን የቀየሩ ሲሆን፤ ሲዳማ ክልል ለጊዜው ኣያስፈልገውም በማለት ኣቋም ይዘዋል። የኣጠቃላይ የግምገማውን ሁኔታ በተመለከተ የውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ በግምገማው ወቅት የካቢኔ ኣባላቱ  የሲዳማን ክልል ጥያቄ እንዳይደግፉ በ ካላ ሽፈራው ሽጉጤ  ከፍተኛ ግፊት ተደርጎባቸዋል። ኣስተያየታቸውን የሰጡት ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች፤ የዞኑ ካቢኔዎች የሲዳማ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፧ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮቹን እንዲያስፈጽሙለት የመረጣቸው የገዛ ልጆቹ እስከመሆናቸው ድረስ የህዝቡን ጥያቄ በኣግባቡ የመመለስ ግደታ እያለባቸው ለምን የክልል ጥያቄ ወደጎን ልገፉት እንደወደዱ ጠይቀዋል። ይህ በእንዲህ እያለ፤ ከሁለት ሳምንት በፊት ሃዋሳ ዙሪያ ከምገኙት ማልጋ እና ወንዶ ገነት ወረዳዎች ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ህዝቡ የክልል ጥያቄ እንዲያነሳ የማሳመን ስራ ሰርታችሃል በሚል

The Heroes and the Villains in the Sidama Liberation Struggle: Undoing the Misinformation

Ever since Bushe and Maldia, the ancestors of the Sidama nation, settled in Teelamo, the epicentre of the Sidama civilization and nation building, as they returned back from Dawa in search of better lands for cattle herding and sedentary farming, the society lived in peace and tranquillity albeit minor ethnic conflicts from neighbouring tribes for control of grazing lands. However, the situation changed drastically when the Abyssinian army invaded the southern nations immediately after the 1882 Berlin Conference of the western nations that decided to divide Africa among themselves. The Abyssinian army supplied with rifles and other modern weapons by these rival western colonizing powers, marched towards the south between the late 1880s and the beginning of the 20th century for control of the vast fertile land and other resources owned by the peoples of the free southern nations. These nations waged bitter armed struggle against the occupying forces of King Minelik during this period

በሲዳማ ዞን መልጋ ወረዳ በበልግ ወቅት የተዘሩ ሰብሎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ::

Image
በሲዳማ ዞን መልጋ ወረዳ በበልግ ወቅት የተዘሩ ሰብሎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ:: የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ታከለ አርጋው እንደገለጹት የወረዳውን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በበልግ ሥራ 2 ሺህ 5 መቶ 21 ሄክታር መሬት በበቆሎ፤ በድንች እንዲሁም በተለያዩ የጓሮ አትክልቶች እንደተሸፈነ ገልጸው ለዚህ ሥራም 3 መቶ 75 ኩንታል ማዳበሪያ እንደተጠቀሙ አስረድተዋል:: ስራው ውጤታማ እንዲሆን የልማት ሠራተኞችና በየቀበሌው የተቋቋሙ የልማት ቡድኖች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ባደረጉት ርብርብ እንደሚጠቀስ መግለጻቸውን አካሉ ጥላሁን ከጅንካ ቅርንጫ ጣቢያ ዘግቧል:: http://www.smm.gov.et/_Text/23HamTextN304.html

በሃዋሳ ከተማ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የትራፊክ ማዕከል ግንባታ በሁለት ወር ውስጥ ተጠናቆ ስራ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 17፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃዋሳ ከተማ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የትራፊክ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ ስራ ሊጀምር ነው። በቅርቡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ክልሎች በራሳቸው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማትን በአቅራቢያቸው ከፍተው የአሽከርካሪዎች የብቃት ማረጋገጥ አገልግሎት ማቅረብ የሚችሉበት ሁኔታ እንዲኖር አቅጣጫ አስቀምጧል። የደቡብ ክልል ትራንስፖርት ቢሮም ይህን መሰረት በማድረግ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታውን እያካሄደ ይገኛል። ማዕከሉ አዲስ አበባ ከሚገኘውና በሀገሪቱ ብቸኛ ከሆነው የአሽከርካሪወች ማሰልጠኛ ተቋም ጋር በአደረጃጀቱና በይዘቱ ተመሳሳይ መሆኑ ነው የተገለፀው ። በ3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ማዕከል ለግንባታው 9.5 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገለት ሲሆን ፥ በሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል። ማዕከሉ በክልሉ ብቁ የሆኑ አሽከርካሪዎችን በማፍራቱ ሚናው  ከፍተኛ እንደሚሆን  ታምኗል ።