የሲዳማ ክልል ጥያቄ የሚመለሰው በኣቶ ሽፈራው በጎ ፍቃድ ሳይሆን ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በመሆኑ ጥያቄውን በቀጠይነት ለምመለከቻቸው ከፍተኛ የፈደራል መንግስት ኣካላት እንደሚያቀርቡ የሲዳማ ሽማግሌዎች ኣስታወቁ፤ ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው የሲዳማን ክልል ጥያቄ ባለመቀበል ኣቋማቸው እንደሚገፉ ገለጹ
የሲዳማ ሽማግሌዎች በዛሬ እለት በሲዳማ ባህል ኣዳራሽ የከተሙት የሲዳማ ሽማግሌዎች በሲዳማ የክልል ጥያቄ ዙሪያ ከደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ከኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጋር ሲመክሩ ውለዋል። በስብሰባው ላይ ከኣንድ ወር በፊት በወጣው የማወያያ ጽሁፍ ላይ በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ በኣንዳንድ መደቦች ላይ ከሲዳማ ተወላጆች ውጪ ለማስቀመጥ እና ከተማዋን ከሌሎች ብሄሮች ጋር ለማስተዳደር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ለመወያያት የማወያያ ጽሁፍ ተዘጋጅቶ ነበር ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ኣምነዋል። የተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ በድንገት ከህዝብ እጅ መግባቱ እና የማወያያ ጽሁፉ ይዘትም ለህዝባዊ ንቅናቄ ምክንያት መሆኑን ኣስታውሰው:፤ መንግስትም ይህንን የተያዘው እቅድ መተውን እና በከተማዋ ኣስተዳደር ውስጥ ክፍት በነበሩ ቦታዎችም ላይ የሲዳማ ተወላጆች መሾሙን ተናግረዋል። ኣክለውም የማወያያ ጽሁፉ በማስቀረት እና ክፍት በነበሩ መደቦች ላይ የሲዳማ ተወላጆችን በመሾም መንግስት ህዝባዊ ንቅናቄውን ለመረጋጋት ጥረት ማድረጉን ጠቁመው፤ ህዝባዊ ንቅናቄ ተባብሶ ለምን ልቀጥል እንደቻሉ ሽማግሌዎቹን ጠይቀዋል። ሽማግሌዎቹን የሲዳማ ህዝባዊ ንቅናቄ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ብቻ የተመለከተ ሳይሆን የክልል ጥያቄን ያነገበ መሆኑን ኣስረድተው፤ የክልል ጥያቄውን ለሚመለከተው ከፍተኛ የመንግስት ኣካል እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል። ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ኣቶ ሽፈራውም ሽማግሌዎቹ ያቀረቡትን የክልል ጥያቄ እንደማይቀበሉ ገልጸው፤ ሲዳማ በደቡብ ክልል ውስጥ መሆኑ የበለጠ የልማት ተጠዋሚ ያደርገዋል የሚለውን እና ሌሎች ነጥቦችን በማንሳት የክልል ጥያቄው እንዲቀር ኣሳስበዋል። የሲዳማ ሽማግሌዎቹም በበኩላቸው ሲዳማ ክልል መሆኑ ለህዝቡ ልያስገኝላቸው የሚችለውን ኢ