Posts

ውቧ ሃዋሳ ከተማ የሲዳማ መዲና!

Image
የኣረንጓደዋ እና የንጽህዋ ሃዋሳ ከተማ መንገዶች እና ህንጻዎች፤ የቅርብ ጊዜ ትራክንግ ሾት 

Quotes from Great Sidama Heroes

Aliito Heewano:  “Ille’ya diamaxxeemmo; La’anna shiiyye’e; Ille’ya amaxxummoro, dagganoo ilamara gedensu bushanno.”  English translation:'I do not cover my eyes; kill me while I am watching; If I do cover my eyes, it would be devastation for generations to come'.   Taklu Yota :  "Koo! mannu taaloho!Massangeenna gulufoottohu dirri; Massagoottohu gulufi; massagssiisoottohu massagi". English translation: 'All men are equal! the one who are riding guided horse, dismount; the one who are guiding, get up on it; the one who ordered the guiding, do it yourself '.  

ሃዋሳ የከተማ አውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ልትጀምር ነው

Image
ሀዋሳ ፣ ሀምሌ 20፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃዋሳ የከተማ አውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ልትጀምር ነው። በቅርቡም አራት አውቶብሶች ገብተው ስራ እንደሚጀምሩ ነው የከተማዋ አስተዳደር  ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  የገለፀው ። አውቶብሶቹ ከከተማዋ ውጭ ለሚገኙ አዋሳኝ ከተሞችም የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣሉ ። የከተማዋ አስተዳደር እንደሚለው ለነዋሪዎች የትራንስፖርት አማራጭ ከመስጠትም ባለፈ በከተማዋ ቀስ በቀስ ደረጃቸውን በጠበቁ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል ። አውቶብሶቹን ስራ ለማስጀመር 24 የማቆሚያ ፌርማታዎች ተለይተዋል። በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ከ3 ሺህ በላይ የሚበልጡ ተሽከርካሪዎች ሲኖሩ ፥ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ባጃጆች ናቸው። የአስተዳደሩ የትራንስፖርት ፅህፈት ቤት እንደሚለው የአውቶብሶቹ ወደ ከተማዋ መግባት ነዋሪው አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል ፤ ዘገባው የታደሰ ብዙዓለም ነው።

የአስራ ሁለተኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ፤ ለሲዳማ ተማሪዎች መልካም እድል እንመኛለን

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 20፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስራ ሁለተኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ረፋድ ላይ በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ድረ ገጽ ይፋ ተደረገ። ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ድረ ገጽ  WWW. nae.gov.et  መመልከት ይችላሉ። በ2004 ዓ.ም ወደ ዪኒቨርሲቲ መግቢያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ቁጥር 156, 997 ነው። የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ አራዓያ ገብረእግዚአብሔር ዛሬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

ከሃዋሳ -ጐፋ ፣ ከሃዋሳ – አርባ ምንጭ፣ ሃዋሳ -ተርጫ አዳዲስ የትራንስፖርት መስመሮች ተከፈቱ

Image
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2004 (ዋኢማ) -  በደቡብ ክልል ባለፈው የበጀት ዓመት የተከፈቱት 11 አዳዲስ የትራንስፖርት መስመሮች የአካባቢውን ሕዝብ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ አስችለውታል። ነዋሪዎቹም ይህንን የሚመሰክሩት አዳዲስ የትራንስፖርት መስመሮች እንዲከፈቱና የተከፈቱትንም እንዲጠናከሩ በማሰባሰብ ጭምር ነው። መነሻቸውን ሃዋሳ መናኸሪያ ካደረጉና ወደተለያዩ አካባቢዎች ከሚጓዙ ተሳፋሪዎች መካከል ወደ አርባ ምንጭ ከተማ ለማቅናት በዝግጅት ላይ ያገኘናቸው ወይዘሮ መሰለች መስቀል ከዚህ በፊት ከነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ጋር ሲያነፃፅሩት በአሁኑ ወቅት ምቹ ሁኔታ መኖሩን ይጠቁማሉ። «ከዚህ በፊት ከሃዋሳ ወደ አርባ ምንጭ በተቆራረጡ መስመሮች ነበር የምንጓዘው። በዚህ ምክንያት ላልተፈለገ ወጪ፣ ለጊዜ ብክነትና ለእንግልት እንዳረግ ነበር» የሚሉት ወይዘሮዋ፤ በአሁኑ ወቅት ግን አዲስ መስመር ተከፍቶ አገር አቋራጭ አውቶቡስ በመመደቡ ችግሮቹ መቃለላቸውን ተናግረዋል። እንደ ወይዘሮ መሰለች ገለፃ፤ ከዚህ በፊት በቅጥቅጥ ተሽከርካሪ ወይም በተለያዩ የተሽከርካሪ ዓይነቶች ከሃዋሳ – አርባ ምንጭ ከ85 ብር በላይ ክፍያ ይጠየቅ፣ ጉዞውም ከስምንት ሰዓት በላይ ይወስድ ነበር። በአሁኑ ወቅት በአገር አቋራጭ አውቶቡሶቹ ለመጓዝ የሚጠየቀው ክፍያ 81 ብር መሆኑንና ጉዞውንም ከስድስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ይቻላል። ከዚህ በፊት ተገልጋዩ ከተሣፈረ በኋላ ከታሪፍ ዋጋ በላይ ጭማሪ የሚደረግበት ሁኔታ እንደነበር አመልክተው፤ የአዳዲስ መስመሮች መከፈት እነዚህንና መሰል ችግሮች ማስወገዱን ይገልፃሉ። ተገልጋዩ ጥሩ መስተንግዶ እንደሚያገኝም ይናገራሉ። «አዳዲስ የትራንስፖርት መስመሮች ከተከፈቱ በኋላ የተመደቡት አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች የተሳፋሪው