Posts

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ2005 በጀት ዓመት ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

Image
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2004 (ዋኢማ) -  የደቡብ ክልል ምክር ቤት በ2005 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ። የጸደቀው በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ4 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው። በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለብርሃን ዜና እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ በክልሉ ለሚከናወኑ የተለያዩ የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የተመደበው በጀት ብር 14 ቢሊዮን 14 ሚሊዮን 594 ሺህ 988 ብር ነው። የበጀቱ ምንጭም ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከከልሉ የሚሰበሰብ ገቢ ነው፡፡ በጀቱ ለክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶች መደበኛና ካፒታል ወጪ፣ ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጥቅል በጀት፣ ለክልላዊ ፕግራሞች፣ ለሚሊኒየሙ ግብ ማስፈጸሚያና ለክልሉ መጠባበቂያ በተዘጋጀው የበጀት ማከፋፈያ ቀመር መሰረት የተደለደለ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ መንግስት ለ2005 የበጀት ዓመት ያጸደቀው በጀት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የ4 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን ይህም በክልሉ የሚከናወኑ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ ለማሰቀጠል የሚያሰችል መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም ጉባኤው በዛሬ ውሎው የክልሉ መንግስት የ2005 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ያጸደቀ ሲሆን በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በኦዲት ቢሮ የዕቅድ ክንውን ላይ በመወያየት ዛሬ ማምሻውን ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

An Overview of the Sidama Resistance Movements

Image
...Various armed groups began to wage armed struggle to uproot the remnants of the Abyssinian regime from the Sidama land. Notable among these fighters and Sidama freedom leaders were: Yetera Bole, Wena Hankarso, Hushsula Xaadisso, Mangistu Hamesso and Lanqamo Naare and Fiisa Fichcho... ... The Sidama people had never accepted the Abyssinian conquest peacefully. They made various attempts to repulse the invading army. The first group of intruders led by Menelik's general Beshah Aboye were annihilated by the Sidama army and civilians led by the ingenious King of Sidama called Baalichcha Worawo. The army of Beshah was totally defeated and left in disarray until the second wave of attack was launched on by Leulseged, another general of Minelik, with superior military force on the Eastern front of Sidama. It was Leulseged's army which was able to establish full Abyssinian domination in the Sidama land and assassinate Baalichcha Worawo, the last king of Sidama. The patte

መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚሰራውን ድራማ በሲዳማ ለመፈጸም እየተዘጋጀ ነው ተባለ::

Image
ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞውን ለማኮላሸት መንግስት በክፍለሀገራት የሚገኙ ሙስሊም የሆኑና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ከየቦታው በማሰባሰብ እንቅስቃሴውን እንዲያወግዙ በማድረግና በቴሌቪዥን ቀርጾ በማቅረብ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ስራ እየሰራ ሲሆን፣ ይህንኑ ስትራቴጂ በሲዳማ ላይ ለመድገም ዝግጅት ጀምሯል። በሲዳማ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ ጊዜዎች እያገረሸ በንጹህን ዜጎች እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል። ይህንኑ ተከትሎ የክልሉ መንግስት የፊታችን ማክሰኞ  የተወሰኑ ደጋፊዎችን አዋሳ በሚገኘው የባህል አዳራሽ በድብቅ በመጥራት፣ “የሲዳማን ችግር የሚፈጥሩት ጸረ ሰላም ሀይሎች ናቸው” የሚል ፕሮፓጋንዳ ለመስራት በዝግጅት ላይ ነው። በመንግስት ባለስልጣናት በጥንቃቄ የተመረጡ ከ1ሺ በላይ ሰዎች ጥሪ እንደተደረገላቸው ለማወቅ ተችሎአል። ይህ ስትራቴጂ ህዝቡን ከሁለት በመክፈል  ጥያቄውን ለማዳፈን የታለመ መሆኑን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ። ካለፈው ወር ጀምሮ በዞኑ የሚታየውን አለመረጋጋት ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።

ባለፈው ሳምንት ግጭት ተከስቶባቸው የነበሩት የማልጋ እና የወንዶ ገነት ወረዳዎች እየተረጋጉ መምጣታቸው ተገለጸ

Image
በፈዴራል ፖሊስ እና በመልጋ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ  በወረዳው የነበረው ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት በመቀነስ ላይ ያለ ቢሆንም መንግስታዊ ስራዎች እንደቆሙ ናቸው። ግጭቱን ምክንያት ኣድርጎ ወደ ወረዳው የገባው የመንግስት የጸጥታ ኃይል እስከኣሁን ድረስ ጉጉማን ጨምሮ በወረዳው እንደሰፈረ ይገኛል። ኣንዳንድ የወረዳው ነዋሪዎች የጸጥታው ኃይል ከወረዳው በኣስቸካይ ለቆ እንዲወጣ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ባለፈው ሳምንት በወረዳው ህዝብ እና በፊዴራል ፖለስ ኃይል መካከል በተፈጠረው ግጭት ከሁለቱም ወገን ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል። በተያያዘ ዜና የማልጋ ወረዳ ግጭት ተከትሎ በወንዶ ገነት ወረዳ ተፈጥሮ የነበረው ኣለመረጋጋት እንዲሁ በመስከን ላይ ነው።  

ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ከተወጣጡ ሽማግሌዎች ጋር በክልል ጥያቄ ዙሪያ ልመክሩ ነው

Image
ውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደጠቆሙት፤ ካለፈው ወር ጀምሮ በሲዳማ ዞን ውስጥ ክልልን ጨምሮ በሌሎች የመልካም ኣስተዳር ጥያቄዎች ላይ ዙሪያ በተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ በተመለከተ ከሲዳማ ሽማግሌዎች ጋር ለመምከር የክልሉ ርእስ መስተዳደር ቀጠሮ ይዘዋል። በሚቀጥለው ማክሰኞ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በዚሁ ምክክር ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ከ 40 እስከ 50 የሚሆኑ የኣገር ሽማግሌዎች የተጋበዙ ሲሆን፤ የኣገር ሽማግሌዎቹ ምንን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደተመረጡ ኣልታወቀም። እንደ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኞች ከሆነ እነዚህ ወደ ኣንድ ሺ የሚጠጉ ሽማግሌዎች የሲዳማ ህዝብ ያነሳውን የክልል ጥያቄ እንዲተው የማሳመን ስራ እንዲሰሩ በመንግስት የተመለመሉ ሳይሆኑ ኣይቀሩም። መንግስት በቅርቡ የሲዳማ ህዝብ ያነሳውን ክልል ይገባኛል ጥያቄ  ለመቀልበስ በተለያዬ መልክ ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ሳምንት የምደረገው ጉባኤ የጥረቱ ኣካል ነው። ከኣስር ኣመት በፊት በተመሳሳይ መልኩ መንግስት ደጋፊ ሽማግሌዎችን በማሰባሰብ በወቅቱ የክልል ጥያቄ  ኣንስተው የነበሩት ሰዎች ጸረ ሰላም ኃይሎች በማስባል ማስኮነኑ ይታወሳል።