የሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ፤ የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄ ያለ ምንም ቅድምያ ሁኔታ አፋጣኝ መልስ እንዲያሰጠው ጠየቀ
ከሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ኀብረት፡ ስለሲዳማ የወቅቱ ሁኔታን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ ተንኰለኞችና ወንጃለኞች በተፈጥሮአቸው የገሙ ስለሆኔ እነሱን ያካተተ መንግሥት፡ አገርንና መንግሥትንም ጭምር ያገማል፡ ላል ሚካኤል ጋድ ስለመንግሥት ተመራማሪ። የወያኔ አገዛዝም በኢትዮጵያ በዚህ መልክ የሚታይ ነው። ወያኔ የሕዝቦች አብሮ መኖርንና ሰላማዊ ሕይወትን የማይቀበል ስለሆነ እንደታመሰ ለ20 ዓመታት የቆየ ሲሆን፡ ሀገራዊ ራዕይ የሌላቸው የወንጃለኖች ጥርቃሞ ነው። የሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት ይህንን ከተረዳ የቆየ ቢሆንም አሁን የደረሰንበት ደረጃ በጣም አደገኛ እየሆነ በመምጣቱ፡ ወያኔ በአስቸኳይ ተመንግሎ መውደቅ ያለበት መሆኑን ህብረቱ አሰምሮበታል። ድርጅታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ በመካሄድ ላይ ያለውን ሁኔታ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ፡ ለመላው ኢትዮጵያውያን ለማሳወቅና እንደ ስልቻ በትዕቢት የተወጠረው ወያኔ ከዚህ ተንኰለኛ ተግባሩ ይቆጠብ ይሆን በማለት ለማሳሰብ የወጣ መግለጫ ነው። ሴራኛው ወያኔ በሲዳማ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ዛሬ ሳይሆን የአዲስ አበባን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡በዚህም በሲዳማ ውስጥ ተወልዶ ያደገውን እጅጉ ገ/ሚካኤል የተባለውን ትግሬ በመመልመልና በመሾም የሲዳማ ታጋዮችን እነፊሣ ፍቾን በስውር አስገድሎዋል። ቀጥሎም የተቃሚዎችን ጐራ ለማዳከም አንዳንድ ለጥቅማጥቅም የተገዙ ግላሰቦችን በመናኛ ገንዘብና መሬት (ቤት መሥሪያ ቦታ) በመስጠትና በመደለል ወደ ወያኔ እንድቀላቀሉ በማድረግ ትግለችን ለማኰለሸት ሞክረዋል: ግን አልተሰካላቸውም። ከዚህም ሌላ፡ በረከት ስሞን ኤርትራዊውን አማራ፡ ኩማ ደመቅሣ ትግሬውን ኦሮሞ ብለው እንደ ሾሙው ሁሉ በሲዳማ ውስጥ ተወልደው ያደጉትን፡ 1ኛ ሽፈረው