Posts

ሲዳማን ጨምሮ በዲላ ከተማ ከሶስት ዞን ለተውጣጡ የዓይን ህሙማን የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው

ዲላ ሃምሌ 11/2004በጌዴኦ ሲዳማና ቦረና ዞኖች በአይን ሞራ ግርዶሽና ትራኮማ ለተጎዱ ወገኖች የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ሀንሴሻ ተራድኦ ልማት ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ገለጸ። የድርጅቱ ስራ አሰኪያጅ አቶ ታደሰ አላኮ በዲላ ከተማ ከሶስቱ ዞኖች ለተውጣጡ የዓይን ህሙማን የህክምና አገልግሎት በተሰጠበት ወቅት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የአይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ህሙማን በመለየት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። ባለፉት ስድስት ዓመታት በአይን ህክምናው በተለይ በዓይን ሞራ ግርዶሽና በትራኮማ የተያዙ ከሁለት ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች ህክምና ማግኘታቸውን ገልጸዋል። ድርጅቱ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምናን በዝዋይና ቡታጅራ በሚገኙ የህክምና ማእከላት እንደሚሰጥ ገልጸው የትራኮማ ቀዶ ህክምናና ሌሎች ቀላል ህክምናዎችን በዲላ ሆስፒታል እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል። ማየት ተስኗቸው በቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ 20 ልጆችን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የብሬል ስልጠና በመስጠት ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረጉን አቶ ታደሰ ገልጸዋል። በጌዴኦ ዞን የዲላ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ አቶ አለማየሁ ገመዴ ሁለት ልጆቻቸው በአይን ሞራ ግርዶሽ ማየት ተስኗቸው እንደነበር አስታውሰው ባለፈው ዓመት በተደረገላቸው ቀዶ ሕክምና ሙሉ ለሙሉ ለማየት መቻላቸውን ተናግረዋል። በድርጅቱ አጋዠነት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙት ተማሪዎች መካከል ተማሪ ጥላሁን ተፈራና ሁሴን መሃመድ ከዚህ ቀደም ድጋፍ የትምህርት እድል ሳያገኙ መቆየታቸውን ገልጸው አሁን ባገኙት ድጋፍ ሶስተኛ ክፍል መድረስ መቻላቸውን ተናግረዋል።

ፉራ ሲዳሙ ቃሪቴ

Image
Harro Sidaamu Siirbba

በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞች ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው

ሐምሌ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደቡብ ዘጋቢ እንደገለጠው በሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ ይርጋለም ከተማ 3 የልማት ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፤ ከትናንት በስቲያ ከታሰሩት መካከል ደግሞ፣ የግብርና ሰራተኞች የሆኑት አቶ ዳዊት ኡጋሞና አቶ በለጠ በልጉዳ፣ የመዘጋጃ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዘሪሁን፣ መምህር ተስፋየ ተሻለ፣ መምህር አብዮት ዘሪሁን፣ መምህር በፍቃዱ ዱሞ፣ መምህር ለገሰ ገሰሰ፣ መምህር ዶልቃ ዱጉና እና ቀበሌ አመራሩ አቶ ካያሞ ፋቶ ይገኙበታል። በአለታ ጭኮ ወረዳ ደግሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ክፉኛ በመደብደባቸው አዛዡ ሆስፒታል ተኝተዋል። አዛዡ የፖሊስ አባል መሆኑን መታወቂያውን በማውጣት ለፖሊሶች ቢያሳይም ፣ መታወቂያህን ለእናትህ አሳያት በማለት ቀጥቅጠው ደብድበውታል።  በሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት ተብትነዋል። በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወጪ እንዲሸፍኑ በመጠየቃቸው ፣ ከክልሉ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። የወረዳው ሀላፊዎች ለፖሊሶች ተብሎ የተያዘ በጀት በሌለበት ሁኔታ እንዴት ወጪያቸውን እንሸፍናለን የሚል ጥያቄ ቢያቀረቡም፣ የክልሉ መንግስት ለሴፍትኔት ተብሎ ከተያዘው ባጀት አውጥተው እንዲከፍሉ አዟል። አብዛኛው የሴፍትኔት ባጀት የሚያዘው ከአለም ባንክ በሚበጀት በጀት ነው። በቀርቡ በአዋሳ እና በጪኮ ወረዳ የታሰሩት ወጣቶች ከአሸባሪው የግንቦት7 ጋር ተባብራችሁዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ______________________

Yirgalem was the first provincial capital of Sidamo province and it has the famous YIRGALEM HOSPITAL & RAS DESTA SCHOOL

Image
ከዩ ቱይብ ላይ ያገኘሁት ቪዲዮው ነው፤ ቪዲዮው በኣብዛኛው በኣማተር የተቀረጸ ትራክንግ ሾት ነው። ምናልባት ውጭ ኣገር ብዙ ጊዜ ለቆያችሁ የዳሌ ይርጋለም ልጆች ትዝታ ይጫርባችሁ ብዬ ነው ።   

Wish you were here: Yirgalem, Ethiopia

Image
Khieta Davis at the Aregash Eco Lodge. (Provided photo I visited the Aregash Eco Lodge in the town of Yirgalem, Ethiopia, as part of a Fulbright Group Project Abroad. The bamboo thatched tukul dwellings are built in the style of a traditional Sidama village. The tukuls are built entirely by hand, except the floors, and took two years to construct. The high ceilings, beautifully appointed furnishings and modern amenities make the bungalow a home away from home, except without television. The sounds of nature — flowing streams, serenading crickets and the faint howl of hyenas — create a distinctive and relaxing ambiance. The grounds were lush and immaculately landscaped. The surrounding forest is home to more than 100 species of birds and mammals. Source: Democrat and Chronicle.com