በሀዋሳ ከተማ ከ40ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ተጀመረ፡፡
ሃዋሳ ሃምሌ 9/2004 በሀዋሳ ከተማ ከ40ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ዛሬ ተጀመረ፡፡ የወጣቶችን የስራ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እንዲጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የፕሮግራሙ መጀመር ምክንያት በማድረግ በሀዋሳ መስቀል አደባባይ ዛሬ በተዘጋጀው የትውውቅ ስብሰባና የቸግኝ ተከላ ስነ ስርዓት ላይ የከተማው ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት መልካሙ ጋጋዶ እንደገለጸው የከተማው ወጣቶች ባለፉት ሶስት ዓመታት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደራጀ መንገድ ተሳታፊና ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶቹ ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ለአካባቢው ልማትና ደህንነት በነፃ ያበረከቱበት በሂደትም ሌሎችን በመርዳት ከማህበረሰቡ የተለያየ እውቀት የቀስሙበት የተግባር መሳሪያ ነው ብሏል፡፡ በዘንድሮም ክረምት ከከተማው የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር እራሳቸውንና ህብረተሰቡን ጠቅመው የከተማውን ልማት በሚያፋጥኑ የበጎ አድራጎት ተግባራት ለመሰማራት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ወጣት መልካሙ አብራርቷል ። የከተማው አስተዳደር ህፃናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ፣ መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ስምረት ግርማ በበኩላቸው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በከተማው ከተጀመረ ወዲህ የወጣቶች ተነሳሽነትና ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡ በ2002 የክረምት ወራት በስድስት ዓይነት የበጎ ፈቃድ አገልገሎት መስኮች 9ሺህ 463 ወጣቶች ተሳታፊ የነበሩበት ሲሆን በቀጣይ አመት የስራ መስኮቹ ወደ ስምንት የተሳታፊ ወጣቶች ቁጥር ደግሞ ከ36 ሺህ በላይ በማሳደግ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል፡፡ በ