ፍትህ የተሰኘው ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ነው፡፡ “ሲዳማ 2፣ ዳግም የሲዳማ እናቶች እንዳያነቡ /Sidaamu Amuwi Lanyikimeesho Wila’anok Gede” (በላቲን ፊደል የተፃፈው ሲዳምኛ ነው) በሚል ርዕስ በሰኔ 15፣ 2004 ዓ.ም ዕትሙ ከላይ የተጠቀሰውን ለውይይት ቀረበ የተባለ ሰነድ መነሻ አድርጎ ያስነበበው ፅሁፍን በተመለከተ የኢህኣዴግ ደጋፊ የሆነው ኣይጋ ፎረም ተብሎ ከሚታወቀው ወይብ ሳይት የሰጠው ምላሽ።
ሰሞነኛው ውዥንብር ኢብሳ ነመራ የደቡብ ብሔር ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማ የሆነችው ሀዋሳ፣ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ የውጭና የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ትኩረት ማረፊያ ሆና ሰንብታለች፡፡ የመገናኛ ብዙሃኑ የሃዋሳ ከተማን አስታከው የሲዳማን ብሄር የሚመለከቱ ጉዳዮችንም አንስተዋል፡፡ የመገናኛ ብዙሃኑ መነሻ፣ ግንቦት 2004 ዓ.ም ማገባደጃ ላይ “ሜትሮ ፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራት” በሚል በክልሉ መንግስት የቀረበ ጥናታዊ ሰነድ ላይ የተደረገ ውይይት መሆኑንም ነግረውናል፡፡ ጉዳዩን አስቀድሞ ያነሳው ፍትህ የተሰኘው ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ነው፡፡ “ሲዳማ 2፣ ዳግም የሲዳማ እናቶች እንዳያነቡ /Sidaamu Amuwi Lanyikimeesho Wila’anok Gede” (በላቲን ፊደል የተፃፈው ሲዳምኛ ነው) በሚል ርዕስ በሰኔ 15፣ 2004 ዓ.ም ዕትሙ ከላይ የተጠቀሰውን ለውይይት ቀረበ የተባለ ሰነድ መነሻ አድርጎ አንድ ፅሁፍ አስነብቦናል፡፡ ፍትህ ከዚህ ቀደም የጋዜጣው አቋም መሆኑን እስኪያሳብቅ ድረስ በብሄር ላይ የተመሰረተውን የኢትዮጰያ የፌደራል አወቃቀር ክፋትና ስጋት ሲሰብከን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ርዕስ በጋዜጣው አምደኛ ሙሉነህ አያሌው በቀረበው ፅሁፍ ግን ለብሔር ተከል የአስተዳደር ስርዓት ሕልውና ያለውን ተቆርቋሪነት ሊያሳይ ሞክሯል፡፡ የጋዜጣው አዘጋጆች የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከሁለት አስርት አመታት በፊት ከቀበርነው የአንድ ብሄር የበላይነት ሲንፀባረቅበት ከነበረው አሃዳዊ የመንግስት ስርዓት ኑፋቄ ደዌ መፈወሳቸው ደግ በሚስልም፤ የአቋም ለውጡ ዱብዳ ስለሆነ “እንኳን ተፈወሳችሁ” ብዬ ከማጨብጨብ ይልቅ፣ መገለባበጡ ውስጥ የተሰነቀረ አንዳች ጤናማ ያል