ዳግም የሲዳማ እናቶች እንዳያነቡ!
Sidaamu Amuwi Lanyikimeesho Wila’anoki Gede ፖለቲካ እና ሥልጣንአርብ ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ.ም. የአዋሳ ከተማ ከወትሮው የተለየ ግርግር ይታይባታል። ያ አመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በተሃድሶ ፕሮግራም ቁም ስቅሉን እያየ የነበረበት ቀውጢ ጊዜ ነበር። ወቅቱ ነባር የህወሓት ታጋዮች ከቀድሞው የትግል አጋሮቻቸው ጋር በፖለቲካው መግባባት ባለመቻላቸው ምክንያት ድርጅታቸው ለሁለት የመሰንጠቅን አደጋ ያስተናገደበት ወቅት ነበር፡፡ አዋሳም የዚህ ወላፈን ተቋዳሽ ብቻም ሳትሆን ትዕይንቱን ዘግናኝ በሆነ ታሪካዊ ክስተት ያስተናገደች ከተማ ነበረች።የአዋሳ ከተማ ከ1994 በፊት በተደነገገው የፌዴራል ሥርዓት መሰረት የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስትና የሲዳማ ዞን መስተዳደር የጋራ ዋና ከተማ ወይም ማዕከል ሆና እስከ 1994ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ዘለቀች። ይሁን እንጂ ከመንግስት ተላልፏል በተባለ ትዕዛዝ መሰረት አዋሳ የክልሉ መንግስት ርዕሰ ከተማ ብቻ እንድትሆንና ‹‹የሲዳማ ዞን መስተዳደር ወደ አለታወንዶ ከተማ እንደተዛወረ ተወስኗል›› የሚል ትዕዛዝ ተላልፏል የሚለው ዜና የሲዳማ ብሄር ተወላጆችን እጅግ አስቆጣ፡፡ ህዝቡም ህገ-መንግስቱ ይፈቅድልኛል ባለው ሰላማዊመቃወሚያ ዘዴን ተጠቅሞ ብሶቱን ለማሰማት ወደአደባባይ ለመውጣት መሰናዶውን አጠናቀቀ። በወጣው ፕሮግራም መሰረት ሰልፉ ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ.ም. እንደሚካሄድና መነሻውም ከሃዋሳ ከተማ በስተደቡብ ከ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ‹‹ሎቄ›› ከተባለች ከተማ ሆኖ የሰልፍ መጨረሻም በአዋሳ እምብርት ከሚገኘው አብዮት አደባባይ እንዲሆን ታቀደ። በታቀደው ፕሮግራም መሰረት የብሄሩ ተወላጆች ከየመንድራቸው የተውጣጡ ቁጥራቸው ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጐች በባ