የሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው? በሚል የደኢህዴን ስራ ኣስፈጻም ኮሚቴ በሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ በየደረጃው ካሉት ከሚመለከታቸው ኣመራሮች ጋር ውይይት ለማድረግ ኣዘጋጅቶት በነበረው በለ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ ላይ ትችት ቀረበ:: የማወያያ ጽሁፉ የሲዳማ ህዝብ ማህበራዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ እሴቶቹን የሚያንቋሽሽ እና ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ለ ህዝቡ ያለውን ንቀት የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ::
የሲዳማ ምሁራን የማወያያ ጽሁፉን በተመለከተ በተለያዩ ማህበራዊ መረቦች ላይ ያቀረቡት ትችት እንደምያመለክተው፡ በደኢህዴን ስራ ኣስፋጻሚ ኮሚቴ የተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ የሃዋሳ ከተማ በጥቂት ኣመታት ውስጥ ያሳየችው እድገት በሲዳማ ኣስተዳደር ብቃት መሆኑን የ ሚ ክድ፤ የሲዳማን ህዝብ እንግዳ ተቀባይነትን ከግምት ውስጥ ያላስገባና በጭፍን የሲዳማን ህዝብ የሚያጥላላ ነው ብለዋል :: በማወያያ ጽሁፉ ላይ የቀረበውን ሙሉ ትችት እንደምከተለው ኣቅርበናል :: ሲዳማ ከዘመነ አፄ ምኒልክ እስከ ደኢህዴን/ኢህአዴግ የአፄ ምኒልክ ተዋጊ ኃይል የሲዳማን ህዝብ በአስከፊ ጭቆናና ብዝበዛ ስር ለማስተዳደር ባካሄደው ወረራ በወቅቱ ይጠቀምበት የነበረውን የጦር መሳሪያ ከህዝቡ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት አንጻር የማይጣጣም በመሆኑ የሲዳማን ህዝብ በግፍ እየጨፈጨፈ እስከ ደቡባዊ አገር ድረስ መዝለቁ አልቀረም፡፡ በወቅቱ ያደረሰው ብዝበዛና ጭቆና የህዝባችንን ሰብዓዊ ክብር ያዋረደና ነፃነቱን ያሳጣ በመሆኑ የሲዳማ ህዝብ በቡድንና በተናጥል ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ከምኒልክ ወረራ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለስላሴ ውድቀት ድረስ ለማንነቱና ለሰብዓዊ ክብሩ ያደረጋቸው የነፃነት ተጋድሎዎች ለታሪክ የሚዘከሩ ናቸው፡፡ በተለያየ መንገድ ፈርጀ ብዙ የሆኑ የፀረ ነፍጠኛ ወይንም መልከኛ ትግል እስከ ደርግ መንግስት ቀጥሎ የመልከኛ ስርዓት ተወገደ፡፡ እንደማንኛውም ነፃነት ፈላጊና ገባሪ ብሔሮች ሁሉ የሲዳማ ሕዝብ የተቀማውን የመሬት ባለቤትነት መብት አገኘ፡፡ ቀጣይ የማንነትና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎች ባይመለሱለትም የሲዳማ ሕዝብ ከ70 ዓመታት በፊት ከአባቶቹ እጅ የተነጠቀውን መሬት መልሶ በማግኘት ለአጭር ጊዜም ቢሆን እፎይታ ያገኘ መስሎ ቢታይም ሰው በላው የወቅቱ መንግሥት ግን በር