Posts

Ethiopia: Ethnic Clashes Feared in Sidama Zone, SNNP

New 22 June 2012 [ESAT] There are reports of heightened fear in Sidama Zone following the conflict in Aleta Chuco town two days ago. There are reports of student demonstrations and road blockades in Tula town 10 KM outside of Awassa. Government workers were denied passage to do their field work in the surrounding towns. The students who are believed to be ethnic Sidama are stopping cars and asking ethnic Wolaitas to come out. Two ethnic Wolaitas are so far reportedly killed inside of Awassa referral hospital as of today. The news of the two killed at the hospital have inflamed Wolaitas and many fear could ignite ethnic conflict. Our reporter who has been traveling in the area said businesses at the outskirts of Awassa town are closed since two days ago. There is a huge presence of Federal Police in Awassa and its environs. A lot of fliers are circulating in Awassa and the surrounding towns. ‘Awassa is being sold to Wolaitas!’, ‘Let us save Awassa!, come out to protest and resist

በሲዳማ ዞን ከፍተኛ የሆነ የዘር ግጭት ሊነሳ ይችላል በማለት የአካባቢው ሰው በስጋት ወድቋል

Image
New ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአዋሳ ዘጋቢዎች እንደገለጡት ትናንት በአለታ ጩኮ የተነሳውን ተቃውሞ ተክትሎ በዛሬው እለትም ከአዋሳ በ 10 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ቱላ ከተማ ውስጥ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውንና መኪኖችን አግተው ለመስክ ስራ የሄዱ ሰራተኞች ስራ ሳይሰሩ እንዲመለሱ ማድረጋቸው ታወቋል። ተማሪዎች በየመኪኖች ውስጥ እየገቡ የወላይታ ተወላጆችን እንዲወርዱ ሲጠይቁ እንደነበር የገለጠው ዘጋቢያችን ትናንት ማታ 2 የወላይታ ተወላጆች በአዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ተገድለው መገኘታቸው ውጥረቱን አባብሶታል ብሎአል። በአዋሳ ከተማ ዳርቻዎች የሚገኙ ሱቆች ግጭት ይነሳል በሚል መዘጋታቸውን ዘጋቢአችን ገልጧል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት በአዋሳና አካባቢዋ መስፈራቸውም ታውቋል። “አዋሳ ለወላይታ ተሽጣለች፣” አዋሳን እናድን፣ ለተቃውሞ ሰልፍ ውጡ” የሚሉ በራሪ ወረቀቶች እየተበተኑ ነው። አዋሳ ለወላይታ ተሽጣለች የተባለው ምናልባትም ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውለድ ቦታ ጋር ሳይያዝ እንደማይቀር ነው ዘጋቢያችን የጠቆመው። ትናንት በአለታ ጩኮ በተነሳው ተቃውሞ 4 ሰዎች መገደላቸውን ፣ በዛሬው እለትም ሱቆች ፣ ትምህርት ቤትና መስሪያ ቤቶች ተዘግተው መዋላቸውን ዘጋቢአችን አክሎ ገልጧል። በቅርቡ በፌደራል መንግስትና በሲዳማ ዞን ባለስልጣናት መካከል የተካሄደው ውይይት ያለውጤት መበተኑን መግለጣችን ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። http://www.ethsat.com

Ethiopian Regime Resumes Another Massacre of Sidama People: 2 dead, 7 wounded

June 20 2012 (SLF)- While the Sidama people are remembering victims of Loqqe massacre on the 10th year anniversary, the regime has started another wave of killings of innocent Sidama people in Chuko area. The killing took place when students and other Sidama people were staging demonstration to demand answer about the plan to control Hawaasa city by the Federal government. According to our sources from the area, 2 people were reported dead; one a business person and the other is a farmer. Seven others were wounded. A teenage girl that critically wounded is being treated at Yirgalem hospital. There is no denying that the Ethiopian regime always responds with brutal force to any peaceful quest instead of listening and understanding what people want. 10 years ago, over 100 Sidama people were massacred when peacefully demonstrating to request the government of their basic human rights. The Ethiopian regime and its affiliates have already controlled most resources of Sidama while coun

የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ በተመለከተ ኣስታያየቶች እየጎረፉ ነው

ከኣስታያዬቶቹ መካከል፥ የዳንግላው ዋርካ ተብሎ በሚታወቀው ትልቁ የኢትዮጵያውን ዌይብ ሳይት ላይ እንደጻፈው: የሲዳማ ሕዝብ በሀዋሳ ከተማ ባለቤትነት ጥያቄ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በአዋሳ ከተማ በፌደራል / ወያኔ መልዕክተኞችና በሲዳማ ክልል የፓርላማ ተወካዮች መካከል በተደረገው ፍጥጫ የሲዳማ ተወካዮች ጉባኤውን ረግጠው ሲወጡ በርካታ የሲዳማ ተወላጅ ባለሀብቶች : ባለስልጣኖችና ተማሪዎች ከየቤታቸው በሌሊት እየታፈኑ እየታሰሩ ሲሆን አንድ ግለሰብ በአጋዚ ተደብድቦ ሕይወቱን አጥቷል :; ከተማዋ በአጋዚ ሠራዊት ታንክና ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ሄሊኮፕተሮች በብዛት እያንዣበቡባት ነው :: አዋሳ ባሁኑ ጊዜ በፍርሐትና በጭንቀት ተውጣለች :: ሲዳሞች ሲዳማ ሕዝብ በአዋሳ ከተማ የዞን ዋና መሥሪያ ቤቶች አዋሳ ውስጥ እንዳይኖሩ በከተማዋ ውስጥ ሲዳሚኛ እንዳይነገሩ ባህላችን ተገፍትሮ ከገዛ ወገኑ እንዲርቅ ተገዷል ይላሉ :: ኃ /ማሪያም ደሳለኝ ከ 6 ዐመት በፊት የሲዳማ ተወላጅ የሆነውን የቀድሞ የደቡብ ፕሬዚዳንት አባተ ኪሾን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በገዛ ፊርማው ከሥልጣን አባሮ በወንበሩ ላይ ጉብ ብሎ ፕሬዚዳንት እንደሆነ ይታወሳል :: በጊዜው በተነሳውም ረብሻ የ 121 ሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ወንጀለኛው ኃይለማሪያም ፕሮሞት ተደርጎ ላሁኑ ቦታ እንደበቃ ይታወቃል :: አሁን ደግሞ የክልሉ መደበኛ ስብስባ ሲደረግ የሲዳማ ተወካዮች ሁሉም ባንድ ቃል መብታችን ይከበርልን ብለው ሲጠይቁ አምባገነኑ ኃይለማሪያም ይህን ጥያቄ ደጋግማቹ የምታነሱ ከሆነ አዋሳ ይገባናል ካላችሁ የደቡብ ዋና ከተማ ወደ ራሴ ትውልድ ቦታ ወላይታ ሶዶ ይሆናል ብሎ አረፈው ::         This message expresses the views and opinions

በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገለጸ

New በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገልጿል:: በሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰላማዊ ሰልፍኞ የክልል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከሶስት ቀናት ባሃላ ተመሳሳይ የክልል ጥያቄ ሰልፍ በሃዋሳ ለማካሄድ ታስቧል:: በዛሬው እለት በሲዳማ ዞን በጭሬ ወረዳ በጭሬ ኩንቡልታ፣ በበንሳ፣ሁላ እና በጠጥቻ የክልል ጥያቄ ባነሱ ሰዎች የተካሄዱ ሰልፎች ያለምንም ግጭት በሰላም መጠናቀቃቸው ተገልጿል:: ዴኢህደን/ ኢህኣዴግ የሃዋሳን ከተማ በኮታ ለማስተዳዳር በሚል ያቀረበውን ኣማራጭ  ሀሳብ በመቃወም የተጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ተቀጣጥሎ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ያለ ኮታ የማስተዳደር መብት ጥያቄነት ኣልፎ ክልል ይገባኛል ጥያቄ በመሆኑ በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ፍጥሯል:: በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገልጿል:: በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ የተቀጣጠለውን የክልል ጥያቄ ለመቀልበስ የግዥው ፓርቲ ኣባላት ወይም ካድሬዎች ህዝቡን እንዲያወያዩ ወደየ ወረዳዎች በመላክ ላይ ሲሆን፥ የወረዳዎቹ ህዝብ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ መምጣቻቸውን በመጠባባቅ ላይ ነው ተብሏል:: በሲዳማ ዞን ውስጥ በኣንድ ሳምንት ጊዜ  ውስጥ ካጫፍ እስከ ጫፍ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ መንግስትን ግራ ያጋባው ሲሆን እስከ ኣሁን የንቅናቄው መሪዎች ተለይተው ኣለማቻወቃቸው ሁኔታውን ኣስቸጋሪ እንዳደረገው እየተነገረ ነው:: በሌሎች የዞኑ ወረዳዎች እየተደረጉ ያሉ የክልል ጥያቄ ሰልፎች በሚቀጥለ ሶስት ቀናት ውስጥ