የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ በተመለከተ ኣስታያየቶች እየጎረፉ ነው
ከኣስታያዬቶቹ መካከል፥ የዳንግላው ዋርካ ተብሎ በሚታወቀው ትልቁ የኢትዮጵያውን ዌይብ ሳይት ላይ እንደጻፈው: የሲዳማ ሕዝብ በሀዋሳ ከተማ ባለቤትነት ጥያቄ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በአዋሳ ከተማ በፌደራል / ወያኔ መልዕክተኞችና በሲዳማ ክልል የፓርላማ ተወካዮች መካከል በተደረገው ፍጥጫ የሲዳማ ተወካዮች ጉባኤውን ረግጠው ሲወጡ በርካታ የሲዳማ ተወላጅ ባለሀብቶች : ባለስልጣኖችና ተማሪዎች ከየቤታቸው በሌሊት እየታፈኑ እየታሰሩ ሲሆን አንድ ግለሰብ በአጋዚ ተደብድቦ ሕይወቱን አጥቷል :; ከተማዋ በአጋዚ ሠራዊት ታንክና ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ሄሊኮፕተሮች በብዛት እያንዣበቡባት ነው :: አዋሳ ባሁኑ ጊዜ በፍርሐትና በጭንቀት ተውጣለች :: ሲዳሞች ሲዳማ ሕዝብ በአዋሳ ከተማ የዞን ዋና መሥሪያ ቤቶች አዋሳ ውስጥ እንዳይኖሩ በከተማዋ ውስጥ ሲዳሚኛ እንዳይነገሩ ባህላችን ተገፍትሮ ከገዛ ወገኑ እንዲርቅ ተገዷል ይላሉ :: ኃ /ማሪያም ደሳለኝ ከ 6 ዐመት በፊት የሲዳማ ተወላጅ የሆነውን የቀድሞ የደቡብ ፕሬዚዳንት አባተ ኪሾን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በገዛ ፊርማው ከሥልጣን አባሮ በወንበሩ ላይ ጉብ ብሎ ፕሬዚዳንት እንደሆነ ይታወሳል :: በጊዜው በተነሳውም ረብሻ የ 121 ሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ወንጀለኛው ኃይለማሪያም ፕሮሞት ተደርጎ ላሁኑ ቦታ እንደበቃ ይታወቃል :: አሁን ደግሞ የክልሉ መደበኛ ስብስባ ሲደረግ የሲዳማ ተወካዮች ሁሉም ባንድ ቃል መብታችን ይከበርልን ብለው ሲጠይቁ አምባገነኑ ኃይለማሪያም ይህን ጥያቄ ደጋግማቹ የምታነሱ ከሆነ አዋሳ ይገባናል ካላችሁ የደቡብ ዋና ከተማ ወደ ራሴ ትውልድ ቦታ ወላይታ ሶዶ ይሆናል ብሎ አረፈው :: This message expresses the views and opinions