በሀዋሳ የጎብኚዎች ቁጥርና ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ እየጨመረ ነው
ሃዋሳ, ሚያዝያ 16 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - ዜና ትንታኔ በደቡብ ኢትዮጵያ ሰምጥ ሸለቆ የምትገኘው ሀዋሳ ለቱሪስቶች ምቹና ተመራጭ ከተማ እየሆነች መምጣቷን የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎቿና አስተናጋጆቿ ይናገራሉ፡፡ በቅርቡ ሀዋሳ ከተማ ጎራ ብለው የቆዩት ቻይናዊው ሚስተር ጆ ጂን እና ኬንያዊው ሚስተር ኒልሰን ቴምሊ የሀዋሳ ሃይቅ፣የአካባቢው የተፈጥሮና መልከአድራዊ አቀማመጥ፣ሀይቁ ዳር የሚገኘው የሌዊ ሪዞርትና መዝናኛ ፣የህዝቡ እንግዳ አቀባበል ስርአት እንደተመቻቸውና እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡ የከተማው ንጽህናና ውበት፣በመገንባት ላይ ያሉ አዳዲስ ህንፃዎች ፣ምቹ የመናፈሻ ቦታዎችን ጨምሮ ሀዋሳ ለኑሮ ተስማሚ በመሆኗ ወደፊትም የመዝናኛ ምርጫቸው እንደሆነች ተናግረዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ለመዝናናት ወደ አዋሳ ያቀኑት አቶ ኩቲ ኢታይ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ማረፊያቸውን ሌዊ ሪዞርት በማድረግ የሀዋሳ ሃይቅ ላይ በዘመናዊ ፈጣን የጀልባ ሽርሽር አሳን በማስገር እንዲሁም የሆቴሉ መስተንግዶና አገልገሎት ምቹ በመሆኑ ትዳር ሲይዙ እዚሁ ለማሳለፍ ምርጫቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በከተማውና አካባቢው ያሉት ተፈጥሮአዊ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ለመጎብኘት የሚመጣው የቱሪስት ፍሰትና ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹት የከተማው ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የመረጃና ፕሮሞሽን ባለሙያ ወይዘሮ እታፈራሁ ተምትም ናቸው፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 97 ሺህ 187 የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ተስተናግደው ከ22 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል ፡፡ ከጎብኚዎቹም መካከል ከ21 ሺህ በላይ የውጭ ቱሪስቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በጎብኚዎች ብዛ