Posts

ለወላጅ አጥና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተገለፀ:

ለወላጅ አጥና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተገለፀ::በሀዋሣ ከተማ የምሥራቅ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የከፍተኛ ሁለት ዐ3 ቀበሌ መረዳጃ እድርና ልማት ማህበር ከእየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ከሳውዲን ተራድኦ ድርጅት ኘሮጀክት ጋር በመተባበር ለ145 ወላጅ አጥና ችግረኛ ህፃናት የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል:: የኢየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት የሀዋሣ ቅርንጫፍ ሥራ አስያኪጅ አቶ ማስረሻ ክብረት እንዳሉት ህፃናቱ ቀደም ሲል የትምህርት ፣ የጤናና የስነ ልቦና ድጋፍ ሲሰጣቸው የቆዩ ናቸው::ከፍተኛ ሁለት ዐ3 መረዳጃ እድርና ልማት ማህበር ከድርጅታቸው ጋር በመተባበር የሚያደርግላቸውን ድጋፍ በመጠቀም ህፃናቱ በትምህርታቸው ውጤታማ ለመሆን መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል:: የምሥራቅ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ ወይዘሮ ዘውዲቱ ገ/መስቀል በበኩላቸው የመረዳጃ እድርና ልማት ማህበሩ ከረጂ ድርጅቶች ጋር በመተባበር  በክፍለ ከተማው በዓላትን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ለወላጅ አጥና ችግርተኛ ህፃናት የተለያዩ ድርጋፎችን  እንደሚያደርግ ተናግረዋል:: የአሁኑ ተረጂ ህፃናት በሚደረግላቸው ድጋፍ ተግተው ከተማሩ የነገይቱ አገር ተረካቢና የተሻለ ዜና መሆን እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡ ባልደረባችን ጌታሁን አንጭሶ እንደዘገበው::

Hawassa constructing 40 mln. Birr worth cultural centre

Image
Hawassa, April 21, 2012 (Hawassa) - Construction of a multi-purpose hall cultural centre is underway in Hawassa town of South Ethiopia Peoples State at a cost of close to 40 million Birr, the town municipality said. Municipality deputy manager, Biru Wolde told ENA that the center, which would be finalized in the next Ethiopian budget year would accommodate 1,700 guests at a time. He said the centre which houses conference hall, theater and art gallery, among others would help conserve historical and cultural heritages of the region. The construction has created dozens of jobs. The regional government and the municipality have covered the construction cost of the centre.

Sidama Libration Front -የሲዳማ ነፃ ኣውጭ ድርጅት ኣላማዎች እና በሲዳማ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ ከድርጅቱ መሪ ከኣቶ ቤታና ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

Image
Seife Nebelbal Radio, April 20, 2012, Interview: Asli Oromo and Sidama Liberation leader Kaala Betana የሲዳማ ነፃ ኣውጭ ድርጅት ኣላማዎች እና በሲዳማ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ ከድርጅቱ መሪ ከኣቶ ቤታና ጋር  የተደረገ ቃለ ምልልስ ከ 24 ደቂቃ ጀምረው ያዳምጡ::

መድኃኒትና ንብረት የዘረፉ ክስ ተመሠረተባቸው

Image
ፈንድ አቅርቦት ኤጀንሲ የሃዋሳ ቅርንጫፍ የጥበቃ ሠራተኛ የነበረው ግለሰብና ሌሎች ስድስት ግለሰቦች በመመሳጠር ከኤጀንሲው የመድኃኒት ማቆያ መጋዘን ውስጥ ከ1ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መድኃኒት በመዝረፍ በከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ተከሰሱ። የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በግለሰቦቹ ላይ የመሠረተው ክስ እንደሚያመለክተው የኤጀንሲው የጥበቃ ሠራተኛ የነበረ 1ኛ ተከሳሽ የመንግሥትን ንብረት እንዲጠብቅ የተሰጠውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ እና ለግብረ አበሮቹ ለማስገኘት በማሰብ ለሕዝብ አገልግሎት ይውሉ የነበሩትን መድኃኒቶች፣ ኬሚካሎች፣ የሕክምና መሣሪያዎች እንዲዘረፉ በማድረጉ ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ፈጽሟል። የኤጀንሲው ሠራተኞች ያልሆኑት ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተከሳሾች ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ተመሳጥረው መድኃኒት የተከማቸበትን መጋዘን ቁልፍ በመስበር መድኃኒቱ የሚጫንበትን ተሽከርካሪ በማዘጋጀት መድኃኒቱን ከመጋዘን አውጥተው በመጫን እንዲሁም መድኃኒቱ የሚራገፍበትን ቦታ በማመቻቸት በወንጀሉ ድርጊት ሙሉ ተሳታፊና በወንጀሉ የተገኘውን ውጤት ተካፋይ መሆናቸውን የክስ መዝገቡ ያስረዳል። 7ኛ ተከሳሽ የሆነው የኤጀንሲው የጥበቃ ተከሳሽ ዘረፋው በተፈጸመበት ዕለት ተረኝነቱን ሳይጠብቅና የሙያ ግዴታውን በአግባቡ ሳይፈጽም ሌሊቱን ጥበቃ ላይ የነበረ በማስመሰል በሰዓት መቆጣጠሪያ ላይ በመፈረሙ በፈጸመው የሥራ ኃላፊነትን ባለመወጣት የሙስና ወንጀል ተከስሷል። በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በግብረአበርነት በፈጸሙት የሙስና ወንጀል ግምቱ 1ነጥብ7ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መድኃኒት ኬሚካሎች ሰፕላይስ እና የሕክምና መሣሪያዎችን በመዝረፋቸው ኮሚሽኑ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ች

በሲዳማ ዞን ይርጋአለም ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከስድስት መቶ ሺህ ብር በሚበልጥ ገንዘብ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገቡ፡

በሲዳማ ዞን ይርጋአለም ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከስድስት መቶ ሺህ ብር በሚበልጥ ገንዘብ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገቡ፡፡ በከተማው በፎቶና ቪዲዮ ስራ የሚተዳደሩት አቶ ናአሚን ፍረሕይወት በበኩላቸው የ5 ሺህ ብር ቦንድ ገዝተው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከፍለው ለማጠናቀቅ ቃል ገብተዋል፡፡ በሌላም በኩል በሸቀጣሸቀጥ ንግድ ስራ የተሰማሩት ወ/ሮ አበባየሁ ለገሰ የ3 ሺህ ብር ቦንድ የገዙ ሲሆን አምስት መቶ ብር ስጦታ መለገሳቸውንም ገልፀዋል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ወንድወሰን ቦልካ ጉዳዩን አስመልክተው እንደገለፁት የግድቡን ስራ ከዳር ለማድረስ የከተማው ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በተለያዩ ጊዜያት ሰፊ የገንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በየጊዜው በተደረገው ውይይት በከተማው የሚኖሩ ነጋዴዎች፣ የሐይማኖት ተቋማትና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ቦንድ ለመግዛት ቃል መግባታቸውን የገለፁት ከንቲባው በቃላቸው መሰረት ግዥውን በመፈፀም ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተራችን መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ እንደዘገበው፡፡