Posts

በሲዳማ ዞን የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ እየተካሄደ ነው

Image
አዋሳ, መጋቢት 12 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሲዳማ ዞን ከ97 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት በ19 ወረዳዎች የውሃ ተቋማት ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ገለጸ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ አብሩ ደቃሞ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በመንግስት፣ በአለም ባንክ፣መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በ19 ወረዳ በመገንባት ላይ ካሉት የውሃ ተቋማት መካከል ጥልቅ ፣መለስተኛና አነስተኛ ጉድጓድ ምንጭ የማጎልበት ይገኝበታል። የአዋዳ ቦርቻ ከፍተኛ ምንጭ ግንባታና ማስፋፊያን በማጠናቀቅ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ለሸበዲኖና ጎርቼ የሚገነቡ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች የመገንባት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የይርጋለምና አለታ ወንዶ ከተሞች የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ለማከናወን ጨረታ ወጥቶ አሸናፊው ግንባታ መጀመሩን ገልጸው ለሁለቱ ከተሞች የመጠጥ ውሃ ግንባታ ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቀዋል። በዞኑ የተጀመረው የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ ከ60 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አስታውቀው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ በገንዘብ በቁሳቁስና ጉልበት አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመው ግንባታቸው ሲጠናቀቅ ከ760 ሺህ የሚበለጥ የዞኑ ነዋሪ ተጠቃሚ በማድረግ የዞኑን የውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ41 በመቶ ወደ 60 በመቶ እንደሚያሳድገው ገልጸዋል

Cost efficacy of Community-Based and In-Patient Therapeutic Feeding …

This investigate estimated a cost efficacy of community-based healing caring (CTC) for children with serious strident gauntness (SAM) in Sidama Zone, Ethiopia compared to trickery formed healing feeding core (TFC). Methods: A cost efficacy research comparing costs and outcomes of dual diagnosis programmes was conducted. The governmental perspective, that considers costs to all sectors of a society, was employed. Outcomes and health use costs of CTC and TFC were performed from Save a Children USA (SC/USA) CTC and TFC programme, supervision health services and UNICEF( in kind supplies) cost estimates of section costs. Parental costs were estimated by interviewing 306 caretakers. Cost categories were compared and a singular cost efficacy ratio of costs to provide a child with SAM in any module (regardless of outcome) was computed and compared. Results: A sum of 328 studious cards/records of children treated in a programs were reviewed; out of that 306 (157 CTC and 149 TFC) were

"An Assessment of the Impacts of Evangelical Christianity on the socio-cultural and religious transformation of Ethiopian society with specific reference to the southern region especially Sidama"

Seminar: Aklilu Lalegoa Submitted by administrator on Tue, 03/01/2012 - 15:25 Calendar Start:  22/02/2012 11:00 Timezone:  Europe/London "An Assessment of the Impacts of Evangelical Christianity on the socio-cultural and religious transformation of Ethiopian society with specific reference to the southern region especially  Sidama " http://www.ocms.ac.uk/content/index.php?q=node/358  

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ መኩሪያ እንደገለፁት ገቢው ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውና የእቅዱ አፈፃፀም 98 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ለገቢው መገኘት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ክትትልና የቅርብ ድጋፍ ማድረጋቸው እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ጋር በቅንጅት መስራቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡በጽህፈት ቤቱ የገቢ አሰባሰብ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ፍስሐ በኬ በበኩላቸው ለባለሙያዎች በገቢ አሰባሰብ ስርአት የሚሰጠው የግልፀኝነት፣ የተጠያቂነትና የስነ ምግባር ትምህርት ስራቸውን በታማኝነት እንዲሰሩ አድርጓቸዋል ማለታቸውን የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ፡፡ ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/8MegTextN104.html  

በሲዳማ ዞን አርቤጐና ወረዳ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን መሰረት ያደረጉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን አርቤጐና ወረዳ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን መሰረት ያደረጉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ሃጥሶ እንደገለፁት ዘንድሮ በወረዳው ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች 38 የንኡስ ተፋሰሶችን በመለየት የተለያዩ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ወረዳው ያለውን ከፍተኛ የውሃ ሀብት ከግምት በማስገባት ጽህፈት ቤቱ በተያዘነው የበጀት አመት 23ዐ ሄክታር መሬት በተለያዩ የውሃ አማራጮች ለማልማት ግብ መጣሉን ገልፀዋል፡፡በእስከ አሁኑ ከ26 ሄክታር በላይ መሬት መልማቱን በመጠቆም፡፡ አምዛዬ አዳነ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው ፡፡ ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/6MegTextN204.html