በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ማርቆስ ተክሌ አምስት አባላት ያሉት ጃፓን የኢትዮጵያን ቡና እንድትገዛ የሚያግባባ የልዑካን ቡድኑ መርተው ከትናንት በስቲያ ጃፓን ገቡ፡፡
የአሜሪካና የአውሮፓ ኢኮኖሚ ለሁለተኛ ጊዜ አዘቅት ውስጥ እየገባ መሆኑን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሆነው ቡና ገበያ እንዳያጣ መንግሥትና የቡና ነጋዴዎች አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን በመፈለግ ሥራ ላይ ተጠምደው ሰንብተዋል፡፡ አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎች እንዲሆኑ የተመረጡት ጃፓን፣ ቻይናና ሩሲያ ሲሆኑ፣ ለሥራ ጉዳይ አዲስ አበባ የቆዩት በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ማርቆስ ተክሌ፣ አምስት አባላት ያሉት የልዑካን ቡድኑ መርተው ከትናንት በስቲያ ጃፓን ገብተዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት በጊዜያዊነት የወጣውን አዲስ ዕቅድ ማለትም የቡና ነጋዴዎች ከገበሬዎች ሰብስበው በምርት ገበያ በኩል ከሚቀርበው ቡና በተለየ ሁኔታ፣ በዩኒየኖችና በኢንቨስተሮች የሚቀርበውን ቡና ጃፓን እንድትገዛ ለማግባባት ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው የቡና መጠን ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነውን ትገዛ የነበረችው ጃፓን፣ በቡና ውስጥ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ኬሚካሎችን አግኝቻለሁ በሚል ቡና ከኢትዮጵያ መግዛቷን በማቋረጧ ነው፡፡ የተቋረጠውን ግብይት ለማስጀመር ኢትዮጵያና ጃፓን ባለፉት ጊዜያት በጉዳዩ ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ በያዘችው አቋም ጃፓን ኬሚካሉን ያገኘችው ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ከተላከ ቡና እንጂ፣ በቀጥታ ከኢትዮጵያ ወደ ጃፓን ከተላከ ቡና ውስጥ አይደለም፡፡ ኬሚካል ተገኘበት የተባለው ቡና ደግሞ በጉዞና በተለያዩ ምክንያቶች ጃፓን እስኪደርስ ድረስ ስምንት ወራት የቆየ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ልትጠየቅ አይገባም የሚል መከራከርያ ቀርቧል፡፡ ይሁንና ጃፓን የኢትዮጵያን ቡና መግዛት በማቋረጥ ከቡና ውስጥ አራት ዓይነት የኬሚካል ይዘቶችን ስትመረምር ቆይታለች፡፡ በአሁኑ ወቅት ሦስት ኬሚካሎችን በቡናው ውስጥ ባለማግ