Posts

16ኛው ሃገር አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ጉባኤ በሃዋሳ እየተካሄደ ላይ ነው፡፡

የክልለ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንዳሉት ሃገሪቱ ያላትን ውስን ሃብት በአግባቡ በመጠቀም የተያያዝነውን  የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባል፡፡ ለዚህም  ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለበት የኦዲት አሰራር ስርዓትን መከተል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በሃገሪቱ አየታዬ ያለው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኦዲት አሰራር ስርዓቱ ተኪ የሌለው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መንግስት ካፀደቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሸን እቅድ አንፃር የኦዲት ተቋማትን የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚገባ መለየት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ለእቅዱ ስኬት የገቢ አሰባሰብ፣ ሥርዓት፣ የበጀት አጠቃቀምና የመንግስታዊ ተቋማትን አፈጻጸም በየጊዜው በመገምገምና የማሻሻያ ሃሳቦችን በማመንጨት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የደቡብ ክልል ኦዲት መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ሳህሌ ገብሬ በበኩላቸው የኦዲት ተቋማት ያሉባቸውን ችግሮች በውል ተገንዝበው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጉባኤው አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጉባኤው የእርስ በርስ ተሞክሮን በማስፋት ጠቃሚ ግብዓት የሚገኝበት እንደሚሆንም አስረድተዋል፡፡ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው 16ኛው ሃገር አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ጉባኤ ላይ ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ከድሬደዋ መስተዳድሮች የተወጣጡ ዋና፣ ምክትል ኦዲተሮችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውም ታውቋል፡፡

በሲዳማ ዞን አርቤጎና ዳሎታ እና ሃገረ ሰላም ወረዳዎች የአሳ ጫጩት ማራቢያ ማዕከል እየተገነባ ነው

ሃዋሳ, ታህሳስ 10 ቀን 2003 (ሃዋሳ) -በደቡብ ክልል አሳን በብዛት ለማምረት በ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ የአሳ ጫጩት ማራቢያ ማዕከል እየተገነባ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ባለፉት ሶስት ወራት ከ3ሺህ ቶን በላይ አሳ ተመርቶ ለገበያ መቅረቡም ተገልጧል ። በቢሮዉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን የስራ ሂት ባለቤት አቶ ብርሃኑ ጦፉ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት የአሳ ማራቢያ ማእከሉን መገንባት ያስፈለገዉ በእርባታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አርሶ አደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ነዉ ። የአሳ ማራቢያ ማዕከሉ መቋቋም በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ አርሶ አደሮች የአሳ ጫጩት በማቅረብ ከሚሰጠዉ አገልግሎት በተጨማሪ ለአርሶ አደሩና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠትና በምርምር ማዕከልነት እንደሚያገለግል አስረድተዋል። በክልሉ ዉሃ ገብ በሆኑ ደጋማ አካባቢዎች በአርሶ አደሮች ጓሮና በእርሻ ማሳ አካባቢ አነስተኛ የአሳ ማራቢያ ኩሬዎችን በማዘጋጀት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ባለፉት ሶስት አመታት የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸዉን ተናግረዋል ። በተለይም በሲዳማ ዞን አርቤ ጎና ፣ዳሎታ ፣ሃገረ ሰላም ወረዳዎች፣ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳና በሌሎችም አካባባቢዎች ከ100 የሚበልጡ ሰዉ ሰራሽ ኩሬዎችን በማዘጋጀትና ከ25ሺህ በላይ የአሳ ጫጩቶችን በመጨመር ከእርባታዉ ከ1ሺህ በላይ ቤተሰቦች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል ። የወላይታ ግብርና ምርምር ማዕከል አርሶ አደሮች ከመደበኛ የእርሻ ስራቸዉ ጎን ለጎን የተሻለ የስጋ ምርት የሚሰጡ የአሳ ዝርያዎችን በማራባት ተጠቃሚ እንዲሆን የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ መሆኑም ተገልጧል ። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች አሳ ለምግብነት ያለዉን ጠቀሜታ እየተረዱ በመምጣታ

በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል በተከሰተ ብጥብጥ ጉዳት ደረሰ፤ አዋኪዎቹ በፖሊስ ተይዘዋል

• ሁከቱ ሊቀ ጳጳሱ ወደተመደቡበት ሀገረ ስብከት እንዳይመጡ ለማሣቀቅ እና አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ችግር መፍታት እንደተሳናቸው ለማሳየት ጀምበር በጠለቀችባቸው በእነ ያሬድ አደመ የታለመ ነው፤ •‹‹በሁከቱ ስለት፣ ዱላ እና ድንጋይ የተጠቀሙት ወሮበሎቹ ባደረሱት ድብደባ ከአምስት ያላነሱ የሰንበት ት/ቤት አባላት እና ፖሊሶች ተጎድተዋል፤ አንዱ ወጣት ጆሮው የተቆረጠ ሲሆን በጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሌላው ወጣት ደግሞ ራሱን ስቶ በጉሉኮስ እየተረዳ ይገኛል፡፡›› (የሆስፒታል ምንጮች) •ፖሊስ ከያሬድ እና ዓለምነህ ሽጉጤ በተጨማሪ በሁከቱ የተሳተፉ ሰባት ቀንደኛ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፤ •ፓትርያሪኩ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና በጋሻው ደሳለኝ ሁከተኞቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ ነው፤ •የሐዋሳ የአገር ሽማግሌዎች ዛሬ የክልሉን ርእሰ መስተዳድር እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል • በመጪው ቅዳሜ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ወደ ሐዋሳ እንደሚመጡ በአዲሱ ሥራ አስኪያጅ ሲነገራቸው ያጉረመረሙት ‹‹የተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› አባላት የሊቀ ጳጳሱ ወደ ሀገረ ስብከቱ መምጣት እንደሚያስከፋቸው በአዎንታ አረጋግጠዋል •‹‹እነያሬድ አደመ ተከልክለው ማንም አራት ጎማ ያመጣው ሁሉ በዚህ መድረክ ላይ አያዝበትም፡፡›› (ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 8/2010፤ ጥቅምት 29/ 2003 ዓ.ም) – ትናንት እሑድ ሰንበት ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም ረፋድ ላይ በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ዓለም እሸቱ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለማነጋገር የጠሩት ስብሰባ ዓለምነህ ሽጉጤ በሚባለው ግለሰብ በሚመራው ‹‹ተስፋ ኪዳነ ምሕረት የፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማኅበር›› እየተባለ በሚጠራው አካል በታቀፉ እ

Sidama: the Luwa and the Anga Culture and their Social Implications

By Wolassa Kumo 1. Introduction In my previous articles, I mentioned the Sidama grand social constitution Seera, and various sub constitutions which derive from this grand constitution. We have also seen that all social constitutions or Seera in Sidama were based on the Sidama moral code of halale, the true way of life. In this socio-cultural and socio-political system, the role of the elders was very important. Elders were bestowed with the power of enforcing the Seera and referring the recalcitrant to Magano or God if he/she refuses to abide by the Seera. The power of elders in the Sidama society was not based on a simple age count as is the case in most modern societies. The Sidama elder is more the product of various social processes through which he passes than the product of a simple aging. For a person to become a recognised elder with authority in Sidama, he has to become a Cimeessa (respected elder with authority) or Cimeeyye for many respected elders. There are three importa

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ‹‹ረብሻ አስነስተዋል›› በሚል የተጠረጠሩ ተማሪዎች ክስ ተመሠረተባቸው

ለ‹‹ስድስት ቀናት ፖሊስ ጣቢያ ስንታሰር ፍርድ ቤት አልቀረብንም››  ተማሪዎች ‹‹በሕጉ መሠረት ፍርድ ቤት አቅርበናቸዋል››  የዲላ ከተማ ፖሊስ (በታምሩ ጽጌ) ከአዲስ አበባ 338 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኅዳር 24 ቀን 2003 ዓ.ም. ተነስቶ ለነበረውና በልዩ የፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ሥር ለዋለው የተማሪዎች ረብሻ ላይ በመሳተፍ፣ በማነሳሳትና ጉዳት በማድረስ በተጠረጠሩ ሁለት ተማሪዎችና ሌሎች ሦስት ግለሰቦች ላይ በትናንትናው ዕለት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በከሳሽ መርማሪ ፖሊስ በዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ የተመሠረተባቸው የሦስተኛ ዓመት የቋንቋ ተማሪ በሆኑት ተማሪ ሜላት ዓይናለም፣ ተማሪ ምዕራብ አለማየሁ፣ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ባልሆኑት ሚሊዮን ምንጊዜም ግዛቸው፣ ፍጹም ብዙአየሁና አብዱ አቡበከር ላይ መሆኑን የክስ ቻርጁ ያስረዳል፡፡ በዲላ ከተማ መግቢያ ዳርቻ ላይ የተመሠረተው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ካምፓሶች ሲኖሩት፣ ረብሻው የተነሳው ኦዳአያ (አዲሱ ካምፓስ) በሚባለው ውስጥ ሲሆን፣ የረብሻውም መነሻ በአንድ ተማሪ ላይ በደረሰ ድብደባ ምክንያት መሆኑን ክሱ ያመለክታል፡፡ ኅዳር 24 ቀን 2003 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ሲሆን ተማሪዎች ፈተና ጨርሰው ይወጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ ቀድሞ የወጣ ተማሪ (ምንተስኖት ጌቱ) ጋር በተፈጠረ ግጭት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በተንቀሳቃሽ ስልክ ከትምህርት ቤቱ ውጭ ያሉትን 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች በመጥራት ተማሪውን በማስደብደባቸው ሆን ብለው አስበው፣ ፀብ በማስነሳት፣ በሰው አካልና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል መከሰሳቸውን ቻርጁ ይገልጻል፡፡ መርማሪ ፖሊስ 1ኛ እና 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ እንዲሁም 5ኛ ተከሳሾች የፈጸሙትን ወንጀል በመዘርዘር ክስ መርስቶባ