የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሃዋሳ ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ህዳር 29 2003 (ሬዲዮ ፋና) አምስተኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በዛሬው ዕለት በተለያዩ ክልሎችበድምቀት ተከበረ። በዓሉ የተከበረው " የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘንየአገራችንን ህዳሴ ወደ ማይቀለበስት ደረጃ እናደርሳለን" በሚል መሪ ቃል ነው። በአሉትናንት በተለይ በሃዋሳ ከተማ ሲከበር በበአሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙትየፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ካሳ ተክለብርሃን የኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርአት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ በመሆን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው ድህነትን ታግለን ማሸነፍ እንደሚገባ አስታውቀዋል። በበአሉ ላይ የተገኙ የብሄር ብሄረሰብ ተወካዮች ፌዴራላዊ ስርአቱ ተጠቃሚ እያደረገ ያለው ብሄርብሄረሰቦችንና ህዝቦችን መሆኑን ጠቅሰው ህገ መንግስቱን በመጠበቅ ድህነትን ለመዋጋት እንደሚረባረቡ አረጋግጠዋል። በተያያዘምየብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሀገራችን ህዝቦች በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነታቸውን በማጠናከር ኢትዮጵያንመካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የገቡትን ቃል ዳግም የሚያድሱበት እንደሆነ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ተናግረዋል። ምክትልርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አወል ወግሪስ ለሬዲዮ ፋና እንዳሉት ቀኑ ህዝቦች ያገኟቸውን ህገ መንግስታዊ መብቶች በመጠቀም ልማትንለማፋጠንም ቃል የሚገቡበት ነው። ለህዝቦች ራስን በራስ ማስተዳደር እንዲሁም በራስ ቋንቋ መማር፣ መስራትና መዳኘት መሰረት ለሆነው ለዚሁ ቀን ከፍተኛ ስፍራ በክልሉ ህዝብ እንደሚሰጠው ገልጸዋል። በተተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች