Posts

ሪፖርተር ጋዜጣ 3 ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ በማለት ያወጣው ዘገባ መሰረተ ቢስ ነው-የደቡብ ክልል

Image
ሪፖርተር ጋዜጣ በነሃሴ 29/2005 እትሙ “ የደቡብ ክልል 3 ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ”  በማለት ያወጣው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ መግለጫው የክልሉ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራትን በአንድ መንፈስ እያካሄደ በሚገኝበት ወቅት ጋዜጣው ይህን መሰል መሰረተ ቢስ ዘገባ ማሰራጨቱ  አሳዛኝ ድርጊት ነው ብሏል፡፡ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ የሀገሪቱን ህጎች የሚፃረር በመሆኑ የክልሉ መንግስት ተግባሩን የፈፀሙት አካላት ህጉን በሚያዘው መሰረት ተከታትሎ  ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጿል፡፡ ምንጭ፡- የደቡብ ክልል የመንግስት ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ምንጨ ፦ http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/item/1964-%E1%8B%A8%E1%88%AA%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8C%8B%E1%8B%9C%E1%8C%A3-%E1%8B%A8%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%89%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%98%E1%88%AB%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%88%98%E1%88%88%E1%8A%A8%E1%89%B0-%E1%8B%AB%E1%8B%88%E1%8C%A3%E1%8B%8D-%E1%8B%98%E1%8C%88%E1%89%A3-%E1%88%98%E1%88%B0%E1%88%A8%E1%89%B0-%E1%89%A2%E1%88%B5-%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8B%B0-%E1%89%A5-%E1%89%A5%E1%88%84%E1%88%A8%E1%88%B0%E1%89%A6%E1%89%BD%E1%8A%93-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A6%E1%89%BD-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸኛኘት ተደረገለት

Image
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ቅዳሜ ከሴንትራል ሪፐብሊክ አፍሪካ የሚያካሂደውን ወሳኝ ጨዋታ በቂ ዝግጅት እንዳደረገ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ነሀሴ 29/2005 በተካሄደው የአሸኛኘኘትና የሽልማት  ስነ-ስርአት አሰልጣኝ ሰውነት እንዳሉት ብሄራዊ ቡድኑ  አሸንፎ ለማለፍ ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡   የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ሳህሉ ገብረወልድ በበክላቸው  ቡድኑ አባላት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ውጤት በማስመዝገብ  አዲስ ታሪክ ለማስመዝገብ  አስፈላጊው ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

የ‹‹ሜትሮ ፖሊታን›› ደራሲ ከስልጣን ተባረሩ

Image
‹‹ሜትሮ ፖሊታን›› የተሰኘውንና የሐዋሳ ከተማ አስተዳዳር 70/30 (ሰባ በመቶ ብሔር ብሔረሰቦች ተዋፅኦ፣ ሰላሳ በመቶ በሲዳማ ተወላጆች እንዲዋቀር) ባለፈው ሚያዚያ 2004 ዓ.ም. አዘጋጅተው ለውይይት ያቀረቡት  አቶ አለማየሁ አሰፋ ከስልጣን ተባረሩ፤ ዝርዝር ዜናውን ከታች ያንቡ፦ የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ  የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡ የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡  በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ

የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ

Image
የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ  የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡ የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡  በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው እንደ አንድ ምክንያት መነሳቱን ያስረዳሉ፡፡ በሌላ በኩል የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ አንዳንድ አስተያት ሰጪዎች ለሦስቱም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነት መነሳት የአመራር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ችግሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡  በሥነ

በመጪዎቹ አስር ቀናት የክረምቱ ዝናቡ መጠንና ስርጭት ይቀንሳል-ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ አጀንሲ

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 28/2005 በመጪዎቹ አስር ቀናት የክረምቱ ዝናቡ መጠንና ስርጭት እየቀነሰ እንደሚሄድ ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ አጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ለኢዜአ እንደገለጸው በቀጣዮቹ አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ሰጪ ክስተቶች ወደ ደቡብና ምዕራብ ማፈግፈግ ጋር ተያይዞ ከሰሜንና ከሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የዝናቡ መጠንና ሥርጭት እየቀነሰ ይሄዳል። በአንፃሩ የክረምቱ ዝናብ በምዕራብ የሀገሪቱ አጋማሽ ክፍሎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል። ኤንሲው እንደገለጸው በዚህ ወቅት በሚኖረው የተጠናከረ የፀሐይ ኃይል በመታገዝ በሚፈጠር የደመና ክምችቶች ሳቢያ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ነጎድጎዳማና አልፎ አልፎም በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሊፈጠር ይችላል። በቀጣዮቹ አስር ቀናትም ዝናብ ሰጪ የሚትዎሮሎጂ ገዕታዎች በሰሜንና ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ላይ አንጻራዊ የመዳከም አዝማሚያ ሊኖር እንደሚችል የኤጀንሲው ትንበያ ይጠቁማል። በዚሁ መሠረት የምዕራብ ትግራይና አማራ፣ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፣ ጋምቤላና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሰሜናዊ አጋማሽ፣ የምዕራብና የመካካለኛው ኦሮሚያ አብዛኛው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል ። ኤጀንሲው በምሥራቅ ኦሮሚያ፣ድሬደዋ፣ሐረርና ሰሜን ሶማሌ ከመደበኛው ጋር የሚቀራረብ ዝናብ እንደሚኖራቸውም አስታውቋል። የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፊል ደመናማ የአየር ሁኔታ እያመዘነባቸው በተወሰኑ ቦታዎች ላይ አነስተኛ ዝናብ ማግኘት ይጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጿል። ይህ ሁኔታ ለመደበኛ የእርሻ ሥራ እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ በልዩ ልዩ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰብሎችና ቋሚ ተክሎች የውሃ ፍላጎትን በማሟላቱ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የኤጀንሲው ትንበያ ያሳያል። የ