Posts

The Sidama has no grievance with sisterly oppressed Nation(s)

Image
The Sidama has no grievance with sisterly oppressed Nation(s) Mulugeta B. Daye . Frustrated SPDM on Sidamas’ commitment to abide law of the land and keeping on the demand for regional autonomy in civilised manner, opted to pervert the course of justice.    The President of SNNPRS   forced   820 cadres to declare nine points, against the will and wish of the Sidama.  This distortion was transmitted on Ethiopian Television on 2, October 2012. Nine points can be analysed into three main categories. 1)        public confession for part of the 820 Sidamas, those who are  integrated to SPDM political system that marginalised 3.4 million Sidamas for either they  are  suspected ofsupporting , sympathising and joining the struggle for S idama’s quest for regional autonomy, that worried the president of SNNPRS who f elt left alone.   2) Reducing the demand of 3.4 million Sidamas’ for regional self-administration as the demand of internally:- parasites and rent see

የሲዳማ ክልል እውን ትሆናለች

ናት ሐመሶ በሲዳማ ህዝብ ላይ ሲዶልቱ፣ ሲያሴሩ፣ ሲሰልሉና በህዝባችን ላይ በደል ሲፈጽሙ የነበሩ ትላንትና በሂስ ግለሂስ ወቅት ተጋለጡ በሲዳማ ምክክር ፎረም (sidama dialogue forum) – ከዚህ ቀደም “የሲዳማ ታጋዮች ፎረም” ይባል የነበረው ነው፡፡ ሰሞኑን የደኢህዴን/ኢህአዴግ አመራሮችና ካድሬዎች (የሲዳማ ዘርፍ) ከያሉበት ተሰባስበው በሲዳማ ባህል አደራሽ ከተው ሲመክሩና ህዝባችንን ሲክዱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ስብሰባው የተጀመረው ባሳለፍነው ሳምንት ሰኞ መስከረም 13/2005 ዓ/ም ሲሆን እስከ ትላንትናው ቀን ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ዘልቋል፡፡ ሽፈራውም በመኖሪያ ቤቱ በርካታ መንፈሳዊ አገልጋዮችንና መንፈሳዊ ሰዎችን ጠርቶና አስጠርቶ የምስጋና ጊዜ አዘጋጅቶ ቀኑን ሲያስብ የዋለው ቅዳሜ ቀን መስከረም 18/2005 ዓ/ም ነው፡፡ ይህ ቀን የተመረጠበት ምክንያት ግልጽ ነው - ከያሉበት አከባቢ ሁሉ የተሰባሰቡ ካድሬዎችን (እጅ ብቻ የሚያነሱ የማይናገሩና የራሳቸው የሆነ አቋምና ዓላማ የሌላቸው ሰው መሰል ፓርላማ ተብየ ፍጡራንን ጨምሮ) “ለሲዳማ ክልል አያስፈልገውም” በሚል ሀሳብ ዙሪያ እጅ አስነስቶ አስወስኖ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ይህ የክህደት ውሳኔ የተላለፈው “ከምስጋና ቀን” አንድ ቀን አስቀድሞ አርብ ለት  በ17/01/2005 ሲሆን ለምስጋና ፕሮግራም ቅዳሜ የተመረጠውም ለዚህ ነው፡፡ በርግጥ ይገባዋል፤ የሲዳማ ህዝብ ሁሉ “ደኢህዴንም ሆነ አንተ አትወክለንም፤ አንተ ከስልጣን ውረድ…” ብሎ በአንድ ሀሳብ ካወገዘውና የጫምባላላ ታዳሚ ሁሉ በረገመውና በሰደበው ማግስት ካድሬውን መልሶ ማሳመን ከቻለ ለርሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በርግጥ ስብዕና ቢኖረው ኖሮ ከዛ ሁሉ ውርደት በኋላ ሀገር ጥሎ በጠፋ ነበር፡፡ ቢሰደብ የሚዋረድ ስብዕና ስለለሌው ግን እንኳ

የሞዴል ትምህርት ቤቶችን ቁጥር በማበራከት በትምህርት ተደራሽነት ላይ የተገኘውን ውጤት በትምህርት ጥራትም ላይ ለመድገም እየሠራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የማልጋ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በወረዳው 6ቱንም የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችንና ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን በአግባቡ በማከናወን የሞዴልነት ማዕከል የሆነው የማልጋ የመጀመሪያ ሳይክል 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ተሞክሮን ሌሎችም እንዲቀስሙ የልምድ ልውውጥ ኘሮግራም አካሂዷል፡፡ በዚህም ወቅት የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ሻላሞ እንዳሉት ጥራቱ በተጠበቀ ትምህርት የተቀረፀ ዜጋና የልማት ሠራዊት ለማፍራት በወረዳው የተጠናከረ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት በ2ዐዐ4 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ከ86ዐ በላይ ተማዎች 9ዐ በመቶ በላይ የሚሆኑ ፈተናውን ማለፋቸውንና ይህም ከቀደሙት ዓመታት 49 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየለ አላካ በበኩላቸው በተገኘውን ውጤት አጠናክረን ካስቀጠልን በታላቁና በባለራዕዩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተነደፈውን የትምህርት ፖሊሲ አጭር መንገድ ተጉዘን እናሳካለን ብለዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተስፋሁን በየነ 2ዐ የ1 ለ5 አደረጃጀቶችን በመጠቀም ውጤታማ ሥራ መሥራቱን ገልፀው ተማሪዎችም ኩረጃን ሙሉ በሙሉ እንዲፀየፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ ላስመዘገበው ውጤት የላቀ ድርሻ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የምስክር ወረቀት መስጠቱንና የትምህርት ቤቱ እሴቱ የሆኑ ምርጥ ተሞክሮዎች በታዳሚዎች መጎብኘቱን የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/16MesTextN405.html

ሲዳማን ማነው የወከለው?

ስሞኑን ከፌደራል እስከ ወረዳ ደረጃ የምገኙ የሲዳማ ኣመራር ኣባላት በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ መክረው ባለ ዘጠኝ ነጥብ የኣቋም መግለጫ በማውጣት ኣጠናቀዋል። ኣንዳንዶች እንደምሉት ከሆነ የሲዳማ ኣመራሮች ዳግመኛ በሃዋሳ ከተማ ላለመሰባሰብ የወሰኑ ይመስላል፤ ምክንያቱም የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በሌሎች በሳል በምባሉ ብሄሮች እንድተዳደርላቸው ተሰማምተዋል እና ሃዋሳ ከእንግድህ የሲዳማ ኣስተዳደር ኣካል ባለመሆኑ በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ስም የመሰባሰብ እድል የላቸውም ይህንን እንኳን ኣርቆ ማየት ብሳናቸውም። ወደ ቁምነገሩ ስንመለስ የሲዳማ ህዝብ ኢህኣደግ ይጠቅመኛል በመልካምኣስተዳደር በኩል ያለብኝን ችግር ይፈታልኛል በማለት በተደጋጋሚ በችግሩ ጊዜ ፈጥኖ በመድረስ ሲመርጠው ብቆይም፤ ደኢህዴን / ኢህኣዴግ የሲዳማን ህዝብ ሲያሳዝን የሰሞኑ ክስተት የመጀመሪያው ኣይደለም። የዛሬ ኣስር ኣመት ደምኣፍሳሹ የደኢህዴን መንግስት የጸጥታ ኃይሎቹን ኣሰማርቶ በንጽሃን የሲዳማ ተወላጆችን ላይ በጠራራ ጸህይ የጥይት መዓት ኣውርዶ በርካታዎቹን በመግደል ሌሎቹን ኣቁስለዋል ፤ በድርግቱም የሲዳማ ህዝብ ክፉኛ ኣዝኗል፤ ሆኖም ከስህተቱ ይማራል ዳግመኛ መሰል ተግባር ኣይደግምም በማለት በባለፈው ምርጫ በነቅስ ወጥቶ እንደመረጠው ይታወሳል። ሰሞኑን ደግሞ ከባለፈው ስህተቱ ያልተማረው ደኢህዴን የሲዳማ ህዝብ ላሳየው ክብር እና ፍቅር የፓርቲው ኣመራሮች የሰጡት ምላሻ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱን በመንጠቅ የራሱን ከተማ በተቀጣሪዎች እንዲያስተዳድር ማድረግ ሆኗል። የምገርመው ደግሞ የሲዳማ የክልል ጥያቄን የሚያነሱ ኣካላት የሲዳማን ህዝብ የማወክሉ ናቸው ብለዋል። ለሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር ሲሉ በደኢህዴን እስር ቤቶች የሚማቅቁት ብሎም ተሰደው

አመራሮቹ በባለ ዘጠኝ ነጥብ በገለጹት የአቋም መግለጫቸው የሀዋሳን ከተማ የአመራር ስምሪት ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳና ብቁ አመራር ከየትኛውም መዋቅር ቢመደብ ትግሉን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል፡፡

ባለፈው አመት ነሐሴ ወር ላይ ነበር በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች ሁከት የመፍጠር አዝማሚያ የተከሰተው፡፡ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄና ፍላጎት ነው በሚል የብሔሩን አቋምና ሀሳብ የማይወክሉ ግን ደግሞ ይህንኑ መንፈስ የያዙ ሁከት የመፍጠር አዝማሚያ መከሰቱ ይታወሳል፡፡ እናም የተፈጠረውን ሁኔታ ለመገምገምና ጉዳዩን ለማጣራት የብሔሩ ተወላጆች የሆኑ ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተገኙበት ግምገማ ለአንድ ሳምንት ተካሂዷል፡፡ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ሽፈራው ሹጉጤ እንዳሉት የተፈጠሩት ሁኔታዎች የኪራይ ሰብሳቢና የጸረ ሰላም ኃይሎች አጀንዳ እንጂ የሲዳማ ህዝብ ፍላጎት ያለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ የተፈጠረው ሁኔታ ለማርገብ የተደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የኪራይ ሰብሳቢ እና የጸረ ሰላም ኃይሎች የህብረተሰቡን አቅጣጫ ለማስቀየር ያደረጉት ጥረት ያለመሳካቱንና ህልማቸው ቢሳካ ኖሮ በውስጠ ድርጅቱ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ የከፋ ይሆን ነበር ብለዋል፡፡ የሲዳማ ህዝብ ከየትኛውም ብሔር እና ብሔረሰብ ጋር ተፋቅሮ እና ተከባብሮ የኖረ ወደፊትም የሚኖር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ይሁንና ኪራይ ሰብሳቢዎች እና የጸረ ሰላም ኃይሎች በወቅቱ የፈጠሩት አጀንዳ ይህንን ህብረ ብሄራዊነት ለማጥፋት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ በታየባቸው አንዳንድ አመራሮች ላይም በየደረጃው በተካሄደው የሂስ ግለሂስ መድረኮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ በቀጣይም የኪራይ ሰብሳቢነትን አስተሳሰብ ከምንጩ የማድረቁ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ አመራሮቹ መንታ መንገድ የለም በሚል ርዕስ ለአንድ ሳምንት ያካሄዱትን ግምገማ ያጠናቀቁት በጋራ መግባባት