በሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ በሻፊና የምርጫ ክልል ተመርጠው በኣለፉት ሁለት ኣመት ተኩል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያገለግሉ የቆዩት ክቡር ወይዘሮ ከበቡሽ ካዊሶ መንግስት ሲዳማ ውስጥ ግለሰቦችን ያለምንም ምክንያት ህዝባዊ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ብቻ በማሰር እና በማንገላታት ላይ መሆኑን ገለጹ።
በሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ በሻፊና የምርጫ ክልል ተመርጠው በኣለፉት ሁለት ኣመት ተኩል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያገለግሉ የቆዩት ክቡር ወይዘሮ ከበቡሽ ካዊሶ መንግስት ሲዳማ ውስጥ ግለሰቦችን ያለምንም ምክንያት ህዝባዊ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ብቻ በማሰር እና በማንገላታት ላይ መሆኑን ገለጹ። የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ተከትሎ የተለየ ኣመለካከት ያላቸውን በብሄሩ ምሁራን እና ተወላጆች ላይ የምፈጽመው የመብት ረገጣ መንግስት ህገ መንግስቱን መጣሱን ላይ መሆኑን ያመለክታል ያሉት የተወካዮች ምክር ቤት ኣባል፤ የሰልጣን ባለበት ህዝብ ሆኖ ሳለ መንግስት ለህዝብ የምሰጠው ግምት ዝቅተኛ መሆን በሲዳማ ውስጥ ከህዝብ ለምኑሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት ኣለመቻል ይህም የዲሞክራሲ ረገጣን ያመለክታል ብለዋል። የሲዳማ ህዝብ ተወካይ ከመሆናቸው የተነሳ በሲዳማ ውስጥ በመንግስት የሚፈጸመውን ዲሞክራሲያዊ መብት ረገጣ እንደምቃዎሙ እና ተቃውሞቸውን በተለያዩ ጊዚያት ለገዥው ፓርቲ ያቀረቡ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ የህዝብ ጥያቄዎች በኣግባቡ ይመለሱ በማለታቸው ጠርተው እንደገመገማቸው ተናግረዋል። የመረጣቸውን ህዝብ በኣግባቡ እንዳያገለግሉ እና መብቱ እንዳላስከብር ገዥው ፓርቲ የተለያዩ ተጽኖዎችን ስለሚያደርግባቸው በኣሜሪካን ኣገር የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ መገደዳቸውብ ኣብራሪተዋል። ከኣዲስ ሬድዮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ያዳምጡ: http://www.addisdimts.com/wp-content/uploads/2013/02/02-23-13.mp3 http://sidamaliberation-front.org/