የቡና ዘርፍ ችግሮችን ለመፍታት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ
በቡና ልማትና ግብይት ዘርፍ የተንሰራፋውን ችግር ለመፍታት መሠረታዊ የመዋቅር ለውጥ ያመጣል የተባለ የውሳኔ ሐሳብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ መነሻ በማድረግ ዕርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ ታውቋል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከወሰዳቸው ዕርምጃዎች መካከል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የተቋቋመበትን ካፒታል አሳድጓል፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ተጠሪነቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወደ ንግድ ሚኒስቴር እንዲዛወርም አድርጓል፡፡ የፌዴራል መንግሥት አገሪቱ ከውጭ ንግድ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ ዕቅዶች ቢያወጣም፣ አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ ግን እየቀነሰ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በተለይ ከአንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያስገኙ ዘርፎች ላይ የተጋረጠውን እንቅፋት የማስወገድ ኃላፊነት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለሚገኘው የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ክፍል ተሰጥቷል፡፡ የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ዘርፍ አስተባባሪ አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) ከመቶ ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ የሚያስገኙ ስድስት የኤክስፖርት ዘርፎችን በመለየት ለእያንዳንዳቸው ከመንግሥት፣ ከግልና ከማኅበራት የተውጣጡ 20 አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ግብይት ባለሥልጣን አማካይነት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ የመጀመሪያው ትኩረት ያገኘው ዘርፍ አገሪቱ ከምታስገባው የውጭ ምንዛሪ 26 በመቶ ድርሻ ያለውና በብዙ መሰናክሎች ውስጥ የሚገኘው ቡና ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለሥልጣን ባለቤትነት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀው ዝርዝር የውሳኔ ሐሳብ ሰሞኑን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት