የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄን በመጀመሪያ ለክልል ማቅረብ እንደ ግዴታ ሊቀመጥ ነው
የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄን በመጀመሪያ ለክልል ማቅረብ እንደ ግዴታ ሊቀመጥ ነው የጠያቂውን ማኅበረሰብ አምስት በመቶ ፊርማ ማሰባሰብ ያስፈልጋል የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ከመቅረቡ በፊት፣ የክልል መፍትሔን አሟጦ የመጨረስ ሕጋዊ ግዴታ ሊቀመጥ ነው፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባርን ለመዘርዘር ተሻሽሎ የተረቀቀው አዋጅ እንደሚያስረዳው፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የመብት ጥያቄ በማንኛውም ማኅበረሰብ ሊቀርብ እንደሚችል፣ ነገር ግን ይህ ጥያቄ ለፌዴሬሽን ከመቅረቡ በፊት የክልል መፍትሔዎችን መጠቀም ግዴታ መሆኑን በረቂቁ አዋጅ አንቀጽ 27 ላይ ሠፍሯል፡፡ ‹‹የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የመብት ጥያቄ ወደ ምክር ቤቱ የሚቀርበው በክልሉ በሚገኙት የተለያዩ የመስተዳደር እርከኖች ቀርቦ አጥጋቢ መፍትሔ ያልተሰጠው መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፤›› ይላል የረቂቁ ድንጋጌ፡፡ ክልሎችም የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የተመለከቱ ጥያቄዎች ሲቀርቡላቸው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መወሰን እንደሚኖርባቸውም የሚገልጽ የጊዜ ገደብ በረቂቁ ተቀምጧል፡፡ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን የመብት ጥያቄዎች የሚባሉትም ማንኛውም ማኅበረሰብ ማንነቴ አልታወቀልኝም ብሎ የሚያነሳው ወይም ማንኛውም ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ቋንቋዬን፣ ባህሌንና ታሪኬን የማሳድግበት ሁኔታ አልተመቻቸልኝም፣ በክልልና በፌዴራል አስተዳደሮች ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት መብቴ አልተከበረም፣ ወይም በማንኛውም ሌላ ምክንያት አድልኦ ተፈጽሞብኛል የሚል እምነት ካደረበት ክልላዊ አስተዳደሩን ጠብቆ ለፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሊቀርብ የሚችል መሆኑን ይገልጻል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ለክልል አስተዳደር አ