‹‹የሐዋሳ ሀብቷ ሆቴሎቿ ናቸው››
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ አቶ ፍትሕ ወልደሰንበት፣ የሐዋሳ ሆቴሎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ፍትሕ ወልደሰንበት የሐዋሳ ሆቴሎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ የሐዋሳ ሴንትራል ሆቴሎች ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በማኅበሩ ወቅታዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ቀጣይ ዕርምጃ ታምራት ጌታቸው አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር ፡- ማኅበሩ እንዴት ተቋቋመ ምን ያህል አባላትስ አሉት? አቶ ፍትሕ ፡- የሐዋሳ ሆቴሎች ማኅበር ከተቋቋመ ገና አንድ ዓመቱ ነው፡፡ መጀመሪያ ፎርም በትነን ሞልተው የላኩና የተመዘገቡ 100 የሚሆኑ ናቸው፡፡ ማኅበሩ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ከዚህም በላይ ብዙ አባላት እንደሚኖሩን እንጠብቃለን፡፡ ሪፖርተር ፡- አንድ ሆቴል ሲቋቋም ብዙ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል፡፡ የማኅበሩ አባላት የሆኑ ሆቴሎች በምን ያህል ደረጃ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል? አቶ ፍትሕ ፡- ያሰራጨነው ፎርም ብዙ ነገሮችን የያዘ ነው፡፡ ምን ያህል ሠራተኞች አሉ? በምን ያህል ካፒታል ነው የተቋቋመው? ሆቴሉ ምን ያህል የመኝታ ክፍሎች አሉት? የሚሉና ሌሎችም በመጠይቁ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን እነዚህን የተሰበሰቡ መረጃዎች ወደ ዳታ ቤዝ ገና እየቀየርናቸው ነው፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ምን ያህል ሠራተኛ እንደሚያስተዳድሩ መናገር አይቻልም፡፡ ነገር ግን መረጃውን የማጠናቀር ሥራ ሲጠናቀቅ ይታወቃል፡፡ ሪፖርተር ፡- የማኅበሩ ተቀዳሚ ዓላማ ምንድነው? አቶ ፍትሕ ፡- አንድ ማኅበር ሁሌም የሚመሠረተው ከችግር በመነሳት ነው፡፡ ችግሩ ካለፈ በኋላ ብዙ የመቀጠል ነገር አይታይም፡፡ እኛ ግን ከዚህ ለየት ያለ ነገር እናስባለን፡፡ ማኅበሩን የመሠረትንበትና ትልቅ ዓላማ ብለን የያዝነው ሐዋሳ ከኢትዮጵያ ተመራጭ የመዝናኛ ቦታ እየሆነች በመሆኑ ከዚህ ገበያ በሰፊው መጠቀም አለብን ብለ