Posts

ኢህኣዴግ የድርጅቱን ከፍተኛ ኣመራሮች መረጠ፤ ኣዲስ ፊት የለም

Image
ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው 10ኛ  የኢህኣዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ የፓርቲውን ከፍተኛ ኣመራሮች በመምረጥ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ድርጅቱ በመከተል ላይ ባለው የመተካካት ፖሊሲ መስረት ኣዳዲስ የፓርቲው መርዎች ብጠበቁም ኣዲስ ፍት ሳይታይ ቀርቷል። ፎቶ ከፋና ድረገጽ ዝርዝር ወሬው ያፋና ነው፦ ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ካለፈው አርብ ጀምሮ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቀሌ ሲያካሂድ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን የግንባሩ ሊቀመንበር በማድረግ በድጋሚ መርጧል። ድርጅቱ አቶ ደመቀ መኮንንን ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2005 ዓመተ ምህረት በተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊቀመንበርነት መመረጣቸው ይታወሳል። ዛሬም 180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ምክር ቤት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን በድጋሚ ግንባሩን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ተኩል ግንባሩን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ መርጧል። አቶ ሀይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሀዋሳ በተካሄደው የኢህአዴግ አባል ድርጅት በሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ የንቅናቄው ሊቀመንበር አድርጎ እንደመረጣቸው ይታወቃል። እንዲሁም የድርጅቱ የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላት እና አመራሮች ተሰይመዋል። 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትም ተጠናቋል። ጉባኤተኞቹ በአገሪቱ የተጀመረውን ፈጣን እድገት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል በመግለጫቸው። የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታትም የሞት ሽረት ትግል እናደርጋለን ብለዋል። የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመ

ከሲዳማ ቡና ኣምራቾች ጋር በመስራቷ የምትታወቀው ጃፓን በኣጠቃላይ በኣገሩ የቡና ምርት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ካነሳች ከስድስት ዓመት በኋላ በቡና ጥራት አለመደሰቷን ይፋ አደረገች

Image
ወሬው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው ፎቶ ከኢንተርኔት ላይ ከስድስት ዓመት በፊት ወደ ጃፓን በተላከ የቡና ጆንያ ላይ በተገኘ የኬሚካል ቅሪት ሳቢያ ጃፓን ከኢትዮጵያ የሚላከውን ቡና አግዳ ብትቆይም፣ አሁንም በሚላክላት ቡና ላይ የጥራት ጉድለት እየታየ በመሆኑ የቀድሞውን ያህል እየገዛች አለመሆኗ ተገለጸ፡፡  በኢትዮጵያ የጃፓን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ካዙሂሮ ሱዙኪ ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ከስድስት ዓመት በፊት በፀረ አረምና ፀረ ተባይ ኬሚካል ሳቢያ ጃፓን ትገዛው የነበረው ቡና ለተወሰነ ጊዜ ከተቋረጠ በኋላ መልሶ ማገገም ቢጀምርም፣ ከስድስት ዓመት በፊት ወደነበረበት ደረጃ ሊመለስ አልቻለም ብለዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ ጥራት ያለውና ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው ቡና ተብሎ የሚላከው ጥራቱም ደረጃውም ዝቅተኛ ከሆነው ጋር እየተደባለቀ በመገኘቱ እንደሆነ አምባሳደር ሱዙኪ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያም የሚፈለገውን ያህል ቡና ወደ ጃፓን መላክ ባይቻልም በየጊዜው እያደገ መምጣቱ ግን ተነግሯል፡፡  የግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚጠቁመው በዓመት ከ170 እስከ 190 ሺሕ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ ይቀርባል፡፡ ከዚህ መጠን ውስጥ የጃፓን ድርሻ ግን ከአሥር በመቶ እንደማይበልጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአንፃሩ ከስድስት ዓመት በፊት ወደ ጃፓን ይላክ የነበረው የቡና መጠን ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ኤክስፖርት እስከ 25 ከመቶ ይደርስ ነበር፡፡  የኬሚካል ንክኪውን ለማስቀረት የጃፓን ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጃፓን መንግሥት ድጋፍ የላቦራቶሪ ማዕከል ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና ከመደበኛው ቡና ጋር ተቀላቅሎ እየተላከ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ቡና የጃፓንን የጥራት ደረጃዎች ማሟላት ተስኖት እንደሚገኝ አምባሳደሩ ይ

ከጊዜ ወደ ጊዜ በኣለማችን ላይ ተወዳጅነትን እያተፈሩ ከመጡት የቡና ኣይነቶች ኣንዱ ስለሆነው ስለ ሲዳማ ሁንቁጤ ቡና ምን ያህል ያውቃሉ

Image
ከጊዜ ወደ ጊዜ በኣለማችን ላይ ተወዳጅነትን እያተፈሩ ከመጡት የቡና ኣይነቶች ኣንዱ ስለሆነው ስለ ሲዳማ ሁንቁጤ ቡና  ምን ያህል ያውቃሉ፦ ዝርዝሩን በምከተለው ድረገጽ ላይ ተጭነው ይመልከቱ ለዝርዝሩ

ለዝናብ እጥረት ተጐጂዎች የ230 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ተጠየቀ

Image
- 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ ይፈልጋል የኢትዮጵያ መንግሥትና ለጋሾች በጋራ በመሆን ባወጡት የሰብዓዊ ድጋፍ ሰነድ፣ በክረምት ዝናብ እጥረት ምክንያት 230 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልግ ይፋ አደረጉ፡፡  ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮችና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች ባወጡት መግለጫ፣ እ.ኤ.አ. በማርች 2015 ወጥቶ የነበረውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰነድ በመከለስ፣ ቀደም ሲል ተገምቶ ከነበረው በተጨማሪ 1.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል፡፡  የዚህ ምክንያቱም በበልግና በክረምት ወቅቶች በኢትዮጵያ የታየው የዝናብ እጥረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ቀደም ሲል ሰብዓዊ ዕርዳታ ያስፈልገዋል ተብሎ ተገምቶ ከነበረው 2.9 ሚሊዮን ሕዝብ በተጨማሪ 1.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሰብዓዊ ዕርዳታ በመሻቱ፣ አጠቃላይ የተረጂዎች ቁጥርን 4.5 ሚሊዮን እንዳደረሰው የመንግሥትና የሰብዓዊ ድርጅቶቹ የጋራ መግለጫ ያስረዳል፡፡ ለአፋጣኝ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጐቶች የኢትዮጵያ መንግሥት 700 ሚሊዮን ብር ወይም 33 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን መግለጫው ያስረዳል፡፡  ‹‹የአውሮፓውያኑ 2015 ሲጀምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ስለበልግ የአየር ሁኔታ ከተነበየው እጅግ የከፋ የዝናብ እጥረት በመከሰቱ፣ የምግብ እህልና የተመጣጠነ ምግብ እህል ችግር ተከስቷል፤›› በማለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ ዴቪድ ዴል ኮንቴ ገልጸዋል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ አምራች የነበሩት የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በተለይም የአርሲና የምዕራብ አርሲ አካባቢዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳስፈለጋቸው መግለጫው ያብራራል፡፡  በአርብቶ አደር አካባቢዎች የተከሰተው የከብቶች

የሲዳማ ቡና አምራቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር

Image
ውድድሩ የቡና ጥራትንና አቅርቦትን ለማሻሻል ያግዛል፤ ውድድሩ ከጥር እስከ የካቲት  2008  ዓ . ም የሚካሄድ ሲሆን፤ በሲዳማ አካባቢ የሚገኙ ከ 24  ሺ በላይ የቡና አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ዩሺማ ኮፊ ካምፓኒ በተሰኘ የጃፓን የቡና ማቀናበሪያ ካምፓኒ አማካኝነት የኢትዮጵያን ቡና በዓለም የቡና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ የሚያስችልና የቡና አምራች አርሶ አደሮቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢትዮጵያ የቡና አምራቾች ውድድር ሊካሄድ ነው። የውድድር ሂደቱን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በጃፓን አምባሳደር መኖሪያ ግቢ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት እንደተነገረው፤ ውድድሩ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም የመጀመሪያ ነው። የውድድሩ ተግባራዊ መሆንም የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ እውቅና ባላቸው ድርጅቶች እንዲተዋወቅ ዕድል የሚፈጥርና አምራቾችም ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው። የካምፓኒው ዳይሬክተርና የአቅርቦት ትስስር ማኔጅመንት ሊቀመንበር ሚስተር ቲቲሱያ ሴኪ በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት፤ በዚህ ውድድርም እስከ ስድስተኛ በመውጣት የሚያሸንፉ አምራች ገበሬዎችን ካምፓኒው ምርቶቻቸውን ከመደበኛው ዋጋ ጨምሮ የሚገዛና ለምርት ጥራት የሚያግዙ ድጋፎችን የሚያደርግ ሲሆን፤ ከስድስተኛ በላይ ለሚወጡ ደግሞ የምርት ግዥውን በተወሰነ መልኩ የሚያከናውን ይሆናል። በውድድሩም የሲዳማ ቡና አምራቾች ብቻ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቡና አምራች አገር እንደመሆኗ በቀጣይ የሌሎች አካባቢ አምራቾችን ለማሳተፍ የሚሰራ ይሆናል። ቡናው ወደ ጃፓን ከተወሰደ በኋላም አስፈላጊው የጥራት መመዘኛ ተከናውኖ የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራበታል። በመሆኑም አምራቾቹ በውድድሩ መሳተፋቸው የቡና ምርትና ጥራትን ጠብቀው እንዲያመርቱና በዛው ልክ ከሚገኘው የገበያ ዋጋ ተጠቃ