የሲዳማ ቡና አምራቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር
ውድድሩ የቡና ጥራትንና አቅርቦትን ለማሻሻል ያግዛል፤ ውድድሩ ከጥር እስከ የካቲት 2008 ዓ . ም የሚካሄድ ሲሆን፤ በሲዳማ አካባቢ የሚገኙ ከ 24 ሺ በላይ የቡና አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ዩሺማ ኮፊ ካምፓኒ በተሰኘ የጃፓን የቡና ማቀናበሪያ ካምፓኒ አማካኝነት የኢትዮጵያን ቡና በዓለም የቡና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ የሚያስችልና የቡና አምራች አርሶ አደሮቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢትዮጵያ የቡና አምራቾች ውድድር ሊካሄድ ነው። የውድድር ሂደቱን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በጃፓን አምባሳደር መኖሪያ ግቢ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት እንደተነገረው፤ ውድድሩ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም የመጀመሪያ ነው። የውድድሩ ተግባራዊ መሆንም የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ እውቅና ባላቸው ድርጅቶች እንዲተዋወቅ ዕድል የሚፈጥርና አምራቾችም ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው። የካምፓኒው ዳይሬክተርና የአቅርቦት ትስስር ማኔጅመንት ሊቀመንበር ሚስተር ቲቲሱያ ሴኪ በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት፤ በዚህ ውድድርም እስከ ስድስተኛ በመውጣት የሚያሸንፉ አምራች ገበሬዎችን ካምፓኒው ምርቶቻቸውን ከመደበኛው ዋጋ ጨምሮ የሚገዛና ለምርት ጥራት የሚያግዙ ድጋፎችን የሚያደርግ ሲሆን፤ ከስድስተኛ በላይ ለሚወጡ ደግሞ የምርት ግዥውን በተወሰነ መልኩ የሚያከናውን ይሆናል። በውድድሩም የሲዳማ ቡና አምራቾች ብቻ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቡና አምራች አገር እንደመሆኗ በቀጣይ የሌሎች አካባቢ አምራቾችን ለማሳተፍ የሚሰራ ይሆናል። ቡናው ወደ ጃፓን ከተወሰደ በኋላም አስፈላጊው የጥራት መመዘኛ ተከናውኖ የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራበታል። በመሆኑም አምራቾቹ በውድድሩ መሳተፋቸው የቡና ምርትና ጥራትን ጠብቀው እንዲያመርቱና በዛው ልክ ከሚገኘው የገበያ ዋጋ ተጠቃ