Posts

በሀዋሳ ከተማ በህይወት ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው የብሉ ናይል ሆቴል ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋለ

Image
በሀዋሳ ከተማ ከአስር ቀን በፊት የሰው ህይወት አጥፍቷል ተብሎ በተጠረጠረበት ወንጀል ሲፈለግ የነበረው የብሉ ናይል ሆቴል ባለቤት አቶ ታምራት ሙሉ ሰሞኑን ከቁጥጥር ስር ውለዋል። ግለሰቡ መስከረም 28 ረቡዕ ጠዋት ሁለት ሰአት ከ15 ገደማ በሀዋሳ መሀል ከተማ አንድ ጠበቃ ሽጉጥ ተኩሶ ህይወቱን በማጥፋትና ሌላኛውን አቁስሏል በሚል ነው የተጠረጠረው። ወንጀሉን ፈጽሞ ተሸሽጎ ነበር የተባለው ተጠርጣሪ ከከተማው መሰወሩን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ከአዲስ አበባ፣ ከፌደራልና ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመተባበር ፍለጋ ሲያካሂድ ቆይቶ ነው፤ ሰሞኑን በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሀ ጋረደው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት። ግለሰቡ ከሀዋሳ ከወጣ በኋላ አዲስ አበባ፣ባህር ዳር ፣ሚሌና ወሎን አቋርጦ ከሀገር ለመውጣት ሞክሮ ሳይሳካለት ቀርቷል። በዚህም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ሌላ የማምለጫ መንገድ ሲፈልግ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። የትኛውም ግለሰብ ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር ለመኮብለል ቢሞክር በጸጥታ ሀይል ቁጥጥር ስር እንደሚውል ከተጠርጣሪው ታምራት ሙሉ ሊማር ይገባልም ብለዋል ኮሚሽነሩ። ግለሰቡ መያዙን ተከትሎም ምርመራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል። የወሬው ምንጭ ኤፍ.ቢ.ሲ ነው

Ethiopia to Host International Coffee Symposium

Image
Ethiopia is to prepare international coffee conference aiming at promoting its brands, said on Monday, the Ethiopian Coffee Exporters Association (ECEA). Accordingly, the conference will take place from 6-7 November 2014 in Addis Ababa. ECEA board chair Hussein Agiraw said that the conference helps the country find better international markets, especially in such countries as China, India, and South Africa with high coffee demand. The coffee yield of Ethiopia, in this year, is expected to have the increase from 20-25 percents from the previous one, he added. The conference is expected to entertain international experiences and papers in the area. Source: allAfrica.com

በማንኛውም ቦታ የሚለበስ የሲዳማ ባህላዊ ልብስ

Image
 የፋሽን ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ ከመጣበት ዘመን አንስቶ በርካታ የአለባበስ ልምዶችም አብረው ተፈጥረዋል። በተለይ በአውሮፓውያኑ አካባቢ አንድን ልብስ ከመምረጣቸው በፊት ለምን ጉዳይ እንደሚለብሱትና በምን ወቅት እንደሚያዘወትሩት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአገራችን የሚዘጋጁ ባህላዊ አልባሳት ጊዜና ቦታ ተመርጦላቸው እንዲለብሱ እየሆነ ነው። ብዙ ጊዜ የባህላዊ አልባሳት በበዓላት ቀን ላይ ብቻ እንዲለበሱ የተወሰኑ ነበሩ። አሁን አሁን ግን የባህላዊ አልባሳትን በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት በተለያዩ ወቅቶች በማንኛውም ቦታ እንዲለበሱ እየደተረገ ነው። በሐዋሳ ከተማ የሚገኘው አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻና ማከፋፈያም ከአገራችን አልፎ እስከ ውጭ አገር ድረስ ባህላዊውን አልባሳት በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት ዕውቅናን እያተረፈ መጥቷል፡፡  ለተጨማሪ ንባብ

ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢ የእግር ጉዞ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 10/2007 የአካል ጉዳተኞች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቅረፍ እኩል እድል፣ ተጠቃሚነትና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡  “የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ  እናድርግ” በሚል መሪ ቃል ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት ድጋፍ እንዲውል ቸሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ሃዋሳ ቅርንጫፍ ለሰባተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰብ የእግር ጉዞ ትናንት በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡ የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተሾመ ታደሰ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት  ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚረዱ ፖሊስዎችና ስትራቴጅዎች ወጥተው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ የአካል ጉዳተኝነት መንስኤዎችንና ከሚያስከትሉት ችግር ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ፣ አካል ጉዳተኛና ቤተሰቦቻቸው ከድህነት የሚላቀቁባቸውን ፕሮግራሞችን የመቀየስ እንዲሁም አድሏዊ አመለካከቶችን የመቀየር ስራዎች ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ከ190 ሺህ በላይ አካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ ገልፀው ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጡ አካላዊ የተሃድሶ አገልግሎቶችን ሊያሳደጉ የሚችሉ ተቋማትን በሰው ሀይል፣ በፋይናንስና በቁሳቁስ የማደራጀት  ስራዎችም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ በተለይም በህዝብ መገልገያና መዝናኛ ሥፍራዎች፣ በማህበራዊ መስጫ ተቋማት፣ በህንፃዎች፣ በመንገዶችና በህዝብ መጓጓዣዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሰሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎችም ተጠናክሮ ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ቸሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ የሃዋሳ ቅርንጫፍ  ስራ አስኪያጅ አቶ መሰረት ኪዳኔ በበኩላቸው የእግር ጉዞው ዓላማ

Organic Ethiopian Sidama Fero: Good Food awards finalist 2014

Image
We’re psyched to release one of our seasonal favorites from the Fero Cooperative in Sidama, Ethiopia. Ethiopia is the birthplace of coffee and the Sidama Union of Growers, comprising of 80,000 individual farmers, put the region’s traditional knowledge into practice through nearly 50 regional base co-ops.  We’ve tasted coffee from many of these groups, but over time have zeroed in on the Fero Cooperative. Their coffee shines due to their particular locale, which is vaulted high in the mountains above the Rift Valley at nearly 2,000 meters. This impressive elevation causes the coffee cherries to mature slowly, developing a physically dense bean, filled with nuanced and complex flavors.  We also love the fact that Fero uses washed processing: immediately after harvest, the pulp of the coffee cherry fruit is removed by milling. After that, the bean is fermented, washed and then dried on raised beds. Washed processing results in a cleaner, brighter, more consistent coffee.  In a busin