የቀድሞው የቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ጥፋተኛ ተባሉ
የቀድሞው የቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጥፋተኛ ተባሉ የተለያዩ የመንግሥት ቤቶችን የኪራይ ዋጋ በመቀነስና በዜጎች መካከል ልዩነት በመፍጠር፣ መንግሥት 370,476 ብር ጉዳት እንዲደርስበት ለማድረግ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል የተከሰሱት፣ የቀድሞ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥፋተኛ ተባሉ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ጎሳዬ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለፈው ዓመት የመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ነው ጥፋተኛ የተባሉት፡፡ አቶ ተፈሪ በሥልጣን ላይ እያሉ፣ በቀድሞ ወረዳ 23 ቀበሌ 12 የቤት ቁጥር 106 የሆነውና በውጭ ምንዛሪ ተከራይቶ የነበረን ቤት፣ የኤጀንሲውን መመርያ አንቀጽ 13 (5) ውድቅ በማድረግ ለኢትዮጵያዊ ማከራየታቸው፣ በቀድሞ ወረዳ 21 ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር 112/40 ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ለንግድ በጨረታ አሸንፎ የነበረውን ቤት በመመሳጠር ወደ መኖሪያ ቤት በመቀየርና ኪራዩን በመቀነስ፣ በቀድሞ ወረዳ 18 ቀበሌ 05 የቤት ቁጥር 008/14 ውስጥ ተከራይ የነበሩትን የምክር ቤት አባል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ሳይኖር በመመሳጠርና በምክር ቤት አባላት ላይ ልዩነት በመፍጠር እንዲከራዩ በማድረግና ሌሎችንም ተጨማሪ ቤቶች ሥልጣናቸውን በመጠቀም ኪራይ ቀንሰው እንዲከራዩ በማድረግ በመንግሥት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ የሰነድና የሰዎች ምስክሮችን በማቅረብ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ፍርድ ቤቱ በብይኑ ገልጾ፣ አቶ ተፈሪ እንዲከላከሉ በማዘዝ ተከላክለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት ዶ/