ሀዋሳ ቤሌማ……!
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኣርት “መጓዝ ማወቅ ነው…..!” ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1995 ዓም (ከአስር ዓመት በፊት መሆኑ ነው) በወርሃ መስከረም ላይ በአሁን ሰዓት ላይ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል በዋና ከተማነት የምታገለግለውን ሃዋሳ ከተማ ለመጀመርያ ጊዜ ለማየት በቃሁ…..፡፡ በሃይቁ ላይ በነጻነት የሚደንሱ የተለያዩ አሶች፤ደስ በሚለው የማያቃጥለው ሞቃት አየሯ እና ሰማይ ላይ በደስታ የሚንሳፈፉ የተለያዩ አእዋፋት……! ባላቸው አቅም ሁሉ በፍቅር አና በደስታ እንግዶቿን የሚያስተናግዱ ህዝቦቿ ልብ የሚመስጥ ነበር…..፡፡ በዚያን ጊዜ ከተማዋ አቅም እንደሌለው…. ወላጅ እንደረሳው…. የህጻን ልጅ ቁምጣ እዚም እዛም የተቦጨቀ የአስፋልትና የጠጠር መንገዶች፤በአሁን ሰዓት መሃል ፒያሳ ጎዳናን በኩራት ተኮፍሶ የሚታየውን የገብርኤል ቤተክርስቲያን ጨምሮ በጅምር የቀሩ ጥቂት ህንጻዎች፤የሃዋሳ ሃይቀርን ተከትለው እንደሚታዩት ግዙፍ የሾላ ዋርካ ዛፎች….እድሜ የጠገቡ አብዛኛውን አሮጌ ቤቶችና የቆዩ ትንንሽ ሆቴሎች…..ወዘተ…. የነበራት ሃዋሳ…. ውበትዋ ማርኮኝ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ እየተመላለስኩ ደስታዬን አጣጥሜያለሁ……!፡፡ እነሆ ዛሬ ከሁለት አመት ቆይ በኋላ ዳግም ተመልሼ እዛው እገኛለሁ ፡፡ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ከተማዋ ተለውጣለች… አምራለች…!፡፡ በየጊዜው ለውጥ አለ የተጀመሩ ህንጻዎች አልቀው ሌሎች ተጀምረዋል፡፡በ1960ዎቹ አካባቢ 6ኪሎ ሜትር ብቻ ይሸፍን የነበረው የአስፋከልት መንገድ ዛሬ 56.6 ኪሎ ሜትር ደርሷል፡፡ ትንሽ የነበረው ወስጥ ለውስጥ የተቦዳደሰ መንገዶችዋ ዛሬ በኮብል ድንጋይ 18 ኪሎሜትር ያህል ተነጥፏል፡፡ ከሌሎች መሰል የሃገራችን ከተሞች በአንጻራዊነት ሲታይ በእድሜ ትንሽ ብትሆንም ተፈጥሮም እያገዛት እጅግ በፍጥነ