የሲዳማ ፓርቲዎች ህብረት ለነጻነት እና ፍትህ (USPFJ)፤ የራሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች!
የሲዳማ ፓርቲዎች ህብረት ለነጻነት እና ፍትህ የሰሞኑ ጋዜጣዊ መግለጫ በኣንባቢያ ዘንድ ክርክር ጫረ የተባበሩት የሲዳማ ፓርቲዎች ለነጻነት እና ፍትህ በምጻረ _ ቃል (USPFJ) ሰሞኑን በኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በኣገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች የተወሰደውን የኃይል እርምጃ በመቃወም ጋዜጣዊ መግለጫ ስጥቷል። በመግለጫውም ለበርካታዎች ሞት እና ኣካል ጉዳት ምክንያት የሆነውን የመንግስት እርምጃ ኮንኗል። ይህንን የድርጅቱን መግለጫ የወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ ከጋዳ ድህረገጽ ላይ በማግኘት ለኣንባቢያኑ ያደረሰ ሲሆን፤ የህብረቱን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ የተለያዩ ሰዎች ኣስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው። በርካታ ኣንባቢያን ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በጻፏቸው መልዕክቶች እንዳመለከቱት፤ የተባበሩት የሲዳማ ፓርቲዎች ህብረት ለነጻነት እና ፍትህ፤ በበርካታ ሲዳማውያንን እና የሰብኣዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች የተወገዘውን፦ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች በቅርቡ በሃዋሳ ከተማ የኣላሙራ እና ታቦር ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሲዳማ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የወሰዱትን የኃይል ጥቃት ካለማውገዙ በላይ በጥቃቱ ልጆቻቸው ለተጎዱባቸው ቤተሰቦች ኣጋርነቱን ኣለመግለጹን እንዳዛዘናቸው ገልጸዋል። ከኣስተያየት ስጪዎቹ መሃከል፦ ስሙን T H በማለት የጠራው እና የዩቨርሲቲ መምህር መሆኑን የገለጸው ኣስተያየት ሲጪ እንዳለው፤ ህብረቱ ምንም እንኳን እታገልለታለው ከሚለው ህዝብ ጋር የግንባር ለግንባር ግንኙነት የሌለው ብሆንም ባለፉት ኣመታት በሲዳማ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ እና ስብኣዊ መብት ጥስቶችን በማጋለጥ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ኣስተውሰዋል። ኣክለውም ህብረቱ በቅርቡ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ በመንግስት የተወሰደውን የኃይል እር