Posts

ስለ ሃዋሣ እና ዣ – ን – ዣ – ድ … ባ – ር

Image
ስለ ሃዋሣ እና ዣ – ን – ዣ – ድ … ባ – ር እግር ጥሎኝ… ውበትና ተፈጥሮን አድሎኝ… በፍቅርና በሃሴት ተፍነክነክ ብሎኝ… ደልቶኝ… ሞቆኝ… ምችት፣ ምችትችት ብሎኝ… የሐዋሳ ሰማይ ስር ከርሜ ነበር :: ሐዋሳ ፍቅር እንደሆነች ባየኋት ልክ የምታስደስተኝ… በኖርኩባት ልክ የምትናፍቀኝ… በሸሸኋት ልክ የምታስጨንቀኝ… መሽቶ በነጋ ቁጥር ነገን የምታስመኘኝ የስስት ከተማዬ ናት :: አይደለም አሁን እንዲህ በአስፋልትና በውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን ንጣፍ አሸብርቃ ይቅርና አቧራ እየለበስን፣ በጠራራ ፀሃይ እየተጠበስን፣ የሞላልን ቀን በጋሪ፣ ያልሞላልን ቀን በኮቴ አሸዋውን በሲሊፐራችን እየዛቅን ስናዘግም እንኳ ለፍቅሯ ጥግ አልነበረኝም… ያን ደማቅ ሰማያዊ የታቦር ሃይስኩል ዩኒፎርም ራሳችን ላይ ጣል እንዳደረግን ጀላቲ እየመጠጥን… አሊያም ሸንኮራ እየጋጥን… ሲደላንም የማዘር ቤትን የ 60 ሳንቲም አምባሻ እየጎመጥን… በላዩ ውሃችንን አንዳንዴም ʿ ሴሏችንን ʾ እየጨለጥን ጎዳናውን ስንሸከሽከው እንኳ ለፍቅሯ ልክ አልነበረኝም… እንዲህ እንደዛሬው በባጃጅ ሽር በሚባልበት ወቅት ይቅርና የጡረታ ዘመኗ ባለፈባት ድክሞ ሳይክል SOS ን አልፌ ጥቁር ዉሃ ድረስ ስንተፋተፍ እንኳ ለፍቅሯ የሚያህላት አልነበረኝም !… ዛሬም የሰላምና የደስታ ጥጌ ሐዋሳ ናት !… ሐዋሳ ሰላም… ሐዋሳ ፍቅር !… እናም የሲዳማን የቆጮ ምግቦችና የወተት አይነቶች እያጣጣምኩ፣ የቶኪቻውን ( የዮሐንስ በቀለን ) ጫምባላላ እየዘፈንኩ ሐዋሳ ከርሜ ነበር… ምንም እንኳ በዛ ያሉ የጭፈራ ዘፈኖች ቢኖሩም ጫምባላላን ግን እጅግ እወደዋለሁ… ከባህል አንፃር ደህና ትርጉም ስላለው ይሆን ?!… ነሸጥ ስለሚያደርገኝ ይሆን ?!… እንጃ ብቻ !… “ አይዴ ጫምባላላ” … “አይዴ ጫምባላላ” … ማ

የሲዳማ ተረቶችን ያዳምጡ

Image
የብሪትሽ ካውንስል ኣዘጋጅነት ከሲዳማ ዞን ተሰባሰበው ሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ግለሰቦች የቀረቡ ተረቶች የሲዳማ የሳር ቤት የሲዳማ ተረት በይሳሃቅ ኣልዳዳ (ሃዋሳ)

ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ በመጪው እሁድ በሐዋሳ ከተማ ይካሄዳል

Image
ፎቶ  @  http://www.photorun.net/index.php?content=photodisplay&id=1065&event=Gebrselassie_Hawasa_Resort አዲስ አበባ ሚያዝያ 29/2006 አምስተኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ  ''የጨቅላ ህጻናትን ህይወት እንታደግ''  በሚል መሪ ቃል በመጪው እሁድ በሃዋሳ ይካሄዳል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት የማርኬቲንግና የገቢ ማሰባሰቢያ አስተባባሪ አቶ መርዕድ ዮሴፍ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ውድድሩ ከ10ሺ በላይ ሰዎችን ያሳትፋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ከ'ሁሉም' ዘመቻ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው ሩጫ በህጻናት፣ በጤና ቡድኖችና በአትሌቶች መካከል የሰባት ኪሎ ሜትርና የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ይደረጋል፡፡ አቶ መርዕድ እንዳሉት በሰባት ኪሎ ሜትሩ ውድድር ከ10ሺ በላይ የጤና ቡድኖችና 750 ህጻናት ይሳተፉበታል። በሩጫው 120 የክለብ አትሌቶች ሲሳተፉ ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አትሌቶች የ14፣ የሰባትና የአራት ሺህ ብር ሽልማት ይበረከታል፡፡