Posts

ስለ ሃዋሣ እና ዣ – ን – ዣ – ድ … ባ – ር

Image
ስለ ሃዋሣ እና ዣ – ን – ዣ – ድ … ባ – ር እግር ጥሎኝ… ውበትና ተፈጥሮን አድሎኝ… በፍቅርና በሃሴት ተፍነክነክ ብሎኝ… ደልቶኝ… ሞቆኝ… ምችት፣ ምችትችት ብሎኝ… የሐዋሳ ሰማይ ስር ከርሜ ነበር :: ሐዋሳ ፍቅር እንደሆነች ባየኋት ልክ የምታስደስተኝ… በኖርኩባት ልክ የምትናፍቀኝ… በሸሸኋት ልክ የምታስጨንቀኝ… መሽቶ በነጋ ቁጥር ነገን የምታስመኘኝ የስስት ከተማዬ ናት :: አይደለም አሁን እንዲህ በአስፋልትና በውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን ንጣፍ አሸብርቃ ይቅርና አቧራ እየለበስን፣ በጠራራ ፀሃይ እየተጠበስን፣ የሞላልን ቀን በጋሪ፣ ያልሞላልን ቀን በኮቴ አሸዋውን በሲሊፐራችን እየዛቅን ስናዘግም እንኳ ለፍቅሯ ጥግ አልነበረኝም… ያን ደማቅ ሰማያዊ የታቦር ሃይስኩል ዩኒፎርም ራሳችን ላይ ጣል እንዳደረግን ጀላቲ እየመጠጥን… አሊያም ሸንኮራ እየጋጥን… ሲደላንም የማዘር ቤትን የ 60 ሳንቲም አምባሻ እየጎመጥን… በላዩ ውሃችንን አንዳንዴም ʿ ሴሏችንን ʾ እየጨለጥን ጎዳናውን ስንሸከሽከው እንኳ ለፍቅሯ ልክ አልነበረኝም… እንዲህ እንደዛሬው በባጃጅ ሽር በሚባልበት ወቅት ይቅርና የጡረታ ዘመኗ ባለፈባት ድክሞ ሳይክል SOS ን አልፌ ጥቁር ዉሃ ድረስ ስንተፋተፍ እንኳ ለፍቅሯ የሚያህላት አልነበረኝም !… ዛሬም የሰላምና የደስታ ጥጌ ሐዋሳ ናት !… ሐዋሳ ሰላም… ሐዋሳ ፍቅር !… እናም የሲዳማን የቆጮ ምግቦችና የወተት አይነቶች እያጣጣምኩ፣ የቶኪቻውን ( የዮሐንስ በቀለን ) ጫምባላላ እየዘፈንኩ ሐዋሳ ከርሜ ነበር… ምንም እንኳ በዛ ያሉ የጭፈራ ዘፈኖች ቢኖሩም ጫምባላላን ግን እጅግ እወደዋለሁ… ከባህል አንፃር ደህና ትርጉም ስላለው ይሆን ?!… ነሸጥ ስለሚያደርገኝ ይሆን ?!… እንጃ ብቻ !… “ አይዴ ጫምባላላ” … “አይዴ ጫምባላላ” … ማ