Posts

Ambo Ethiopia Police Open Fire on Protesters

Ethiopian Music - Teferi - Limbo - Sidama (Official Music Video)

BBC World News reports on Oromo Protest against Addis Ababa Master Plan

“..የነበራት ባልም ይፈታታል... ሌላ ባልም...”

Image
ፎቶ ከ http://kwekudee-tripdownmemorylane.blogspot.com/2013/08/sidama-people-ethiopias-kushitic-expert.html “...እስከአሁን የማልረሳው አንድ አጋጣሚ አለኝ፡፡ አንዲት እናት በቤትዋ ሳለች ምጥ ጀምሮአታል፡፡ ከዚያም ይበልጥ ስትታመምባቸው እኔ ወዳለሁበት በሲዳማ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ ባለው የጤና ጣቢያ ያመጡአታል፡፡ እኔም ስመለከታት የማህጸን መተርተር ደርሶባታል፡፡ አጋጥሞኝ ስለማያውቅ እጅግ በጣም ነበር የደነገጥኩት፡፡ በእርግጥ በኦፕራሲዮን ማህጸንዋ ይወጣል። ነገር ግን እሱም እርምጃ ቢወሰድ እና ሕይወቷ ቢተርፍ ማህጸንዋ ሲወጣ ወደፊት ልጅ መውለድ ስለማትችል ባለችበት ሕብረተሰብ አስተሳሰብ የምትገለል ትሆናለች፡፡ ምክንያቱም ልጅ ለወደፊቱ መውለድ ስለማትችል የነበራት ባልም ይፈታታል... ሌላ ባልም አያገባትም፡፡ በህብረተሰቡም ዘንድ ተቀባይነት ስለማይኖራት ዝም ብላ የምትኖር ትሆናለች፡፡ይሄንን ነገር ዛሬ ላይ ሳስበው ይቆጨኛል፡፡ ምክንያቱም እንደአሁኑ እውቀቱ ቢኖረኝ ኖሮ ወደከፍተኛ ሕክምና ጊዜ ሳልፈጅ አስተላልፌ በሴትየዋ ላይ የደረሰው ችግር ሊቃለል ይችል ነበር…”  ከላይ ያነበባችሁት ገጠመኝ ከአንድ የጤና መኮንን የቀረበ ነው፡፡ የጤና መኮንኑን ያገኘነው በሐዋሳ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እና በዞኑ የጤና መምሪያ እንዲሁም በፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ትብብር WATCH (women & their child health) የእናቶችና ሕጻናት ጤናን ለማሻሻል በተነደፈው ፕሮጀክት ድጋፍ ስልጠና ሲወስድ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር WATCH (women & their child health) የተሰኘው ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቢንያም ጌታቸው እን

“...ክፍተቱን ማጥበብ ትልቅ ነገር ነው...”

“...ክፍተቱን ማጥበብ ትልቅ ነገር ነው...” የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (WATCH) ዋች ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚወለዱ ጨቅላ ሕጻናትና እናቶች ዙሪያ አፋጣኝና መሰረታዊ የሆኑ ሕክምናዎችን ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና በተለያዩ መስተዳድር አካላት ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ስልጠና አስቀድሞ በየመስ ተዳድር አካላቱ የሚገኙ የዞን ...የወረዳ... አካላት እና  ሌሎች መሰል ተቋማት ውስጥ በኃላፊነት የሚሰሩ አባላትን ስለጉዳዩ በቂ እውቀት እንዲያገኙ ከጤና ባለሙያዎቹ አስቀድሞ ስልጠና ሰጥቶአል፡፡ ከስልጠናው በሁዋላ ያለው የስራ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? በሚል በደቡብ ብሔር ብሔረ ሰቦች ሐዋሳ ዙሪያ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ ለዚህ እትም ንባብ እነሆ ብለናል፡፡ ...አንድ አባት ከመኪና ውስጥ አጠገቤ ተቀምጠዋል። በምናልፍበት አካባቢ ከርቀት አንድ ጤና ጣብያ ተመለከትን፡፡ የምንመለከተው ጤና ጣቢያ ማን ይባላል? አልኩና ጠየቅ ሁዋቸው፡፡ እሳቸውም እኔም ለአገሩ እንግዳ ስለሆንኩ አላውቀውም የሚል ነበር መል ሳቸው፡፡ ቀጠል አድርገውም ...ምን...ጤና ጣብያ በየቦታው ተሰርቶ እያለ ነገር ግን ተጠ ቃሚው በተለይም እናቶች እምብዛም ናቸው... ብዙዎቹ የሚወልዱትም በቤታቸው ነው ...አሉኝ፡፡ ለምንድነው ብዬ ስጠይቅ ...ይህንን እኔም አላውቅም...እራሳቸውን ብታገኝ ያቸው እና ብትጠይቂ ጥሩ ነው አሉኝ ...እና ተለያየን፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ብሄረሰቦች ዘንድ የተለያዩ ጎጂና ጎጂ ያልሆኑ ልማዳዊ ድርጊች እንደነበሩ እና አልፎ አልፎም አሁንም እንደሚፈጸሙ እሙን ነው፡፡ አንዲት የሲዳማ ሴት እንዳወጋችን ከሆነ... “...በደቡብ ሲዳማ አካባቢ ሐሜሳ የሚባል ከእንጨት መሰል