Posts

Ethiopia's coffee, gold income declines

Image
Compared to last year, Ethiopia's export has shown decline this year  on major export commodities of the country including coffee and gold, which fall  25% and 27%, respectively. Prime Minister Hailemariam Desalegn told Parliamentarians on Thursday  while presenting his report of the past nine months. He attributed the  decline to gold and coffee prices fall globally. "Though we have witnessed 9% increase in agricultural commodities  export, because coffee represents a major portion in the export, we  didn't achieve necessary result from our agriculture which constitutes  80% of our export," he said. Total export growth of the country is now  stood at only 2% compared to last year. During the fiscal year concluded July 7, 2013, Ethiopia has earned  $3.15 billion by exporting agricultural commodities, minerals and  manufactured goods to 133 countries. Out of the total earnings coffee  covers around $745 million. On the other hand, the premier also mention

በሲዳማ ለምነሱት የክልል ኣስተዳደር ጨምሮ ለሌሎች የመልካምኣስተዳደር እና የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎችን ለማፈን መንግስት የምወስደውን የኃይል እርምጃ እንድያቆም የሲዳማ መብት ተከራካሪዎች ድምጻቸውን ማሰማት ኣለባቸው ተባለ፤የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

Image
ፎቶ  ኢንተርኔት  ሰሞኑን ከሬውተርስ የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የኣሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዋናነት ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብትን ማሳደግ በሚቻልበት አቅጣጫ ላይ ከሀገ ሪ ቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይ መክራ ሉ ተብሎ ይጠበቃል ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ጉብኚት ኣስመልክቶ ሪፖርተራችን ሚሊዮን ማቲያስ ያናገራቸው ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኞች የሆኑት ምሁራን እንደተናገሩት፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኣገሪቱ ባለው የሰብኣዊ መብት ኣያያዝ ላይ የምመክሩ በመሆኑ በዚህ ኣጋጣም በሲዳማ ያለውን የስብኣዊ መብት ረገጣ የማጋለጥ ስራ መስራት ኣለበት ብለዋል። ኣክለውም መንግስት በሲዳማ በተለያዩ ጊዚያት የሰብኣዊ መብት ረገጣ መፈጸሙን ኣስታውሰው፤ መንግስት በሲዳማ የምፈጽመውን የሰብኣዊ መብት ተባብሶ መቀጠሉን ኣመልክተዋል። ለኣብነትም በዚህ ወር ውስጥ በሃዋሳ ከተማ የኣላሙራ እና ታቦር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የሲዳማ ተማሪዎች ከሲዳማ ኣፎ ጋር በተያያዘ ላነሱት የመብት ጥያቄ መንግስት የኃይል ምላሽ መስጠቱን ኣብራርተዋል። በሲዳማ ለምነሱት የክልል ኣስተዳደር ጥያቄን ጨምሮ ለሌሎች የመልካምኣስተዳደር እና የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች መንግስት በሰላማዊ መንገድ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የኃይል እርምጃ መውሰድ መምረጡን እንድያቆም ብሎም ዞኑ የምፈጽመውን የዲሞክራሲ እና ሰብኣዊ መብት ረገጣ ለማስቆም የምታገሉ ህዝባዊ ድርጅቶች ይህንን ኣጋጣሚ በመጠቀም ድምጻቸውን ማሰማት ኣለባቸው በማለት እኝኑ ምሁራን መክረዋል። ኬሪ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ እና ከኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር የሚገናኙ ሲሆን በቀጠናው

ሩጥ ሃዋሳ

Image
ፎቶ @  http://www.photorun.net/index.php?content=photodisplay&id=1065&event=Gebrselassie_Hawasa_Resort ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት፦  ኃይሌ ሪዞርት ሃዋሳ

ኢህአዴግ ራሱ ጥያቄ አውጥቶ፣ ራሱ ተፈትኖ፣ ራሱ ያርማል!

Image
ፓርላማው እንዲሟሟቅ ትኩስ ቡናና ሳቅ ያስፈልጋል!         ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለፓርላማ ያቀረቡት በፋሲካ ማግስት ነው ማለት ይቻላል- ባለፈው ሐሙስ፡፡ ለዚህም ነው አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ከሌላው ጊዜ በተለየ እንቅልፍ እንቅልፍ ያላቸው (የበዓል ማግስት እኮ ይጫጫናል!) ለነገሩ … ያንን ሁሉ ሰዓት አዳራሽ ውስጥ መሰብሰብም እኮ እንቅልፍ ያመጣል፡፡ ምናልባት በጣም የባሰበት እኮ ጥያቄውን ለጠ/ሚኒስትሩ ከአቀረበ በኋላ፣ “ለሽ” ሊል ይችላል፡፡ ደግነቱ እኛ እንሰማዋለን (“እኛ” ወካዮቼ ማለቴ ነው!) በነገራችሁ ላይ በበቀደሙ ፓርላማ  እንቅልፍ ያስቸገራቸውን የምክር ቤት አባላት ለመውቀስ አይደለም - የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያፈላልግ መተንኮሴ ነው (የግምገማ ተጠሪውን ሳይሆን የሪፍሬሽመንት ክፍሉን!)   ከምሬ ነው--- ለምን አጭር የቡና ሰዓት አይኖርም? (“ኖሮ አያውቅም ወይም አልተለመደም” እንዳትሉኝ!) ለነገሩ ብትሉኝም አልቀበልም፡፡ ይኼውላችሁ---- ድሮ የሌሉ አሁን የተጀመሩ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እናም ----- ድሮ የቡና ሰዓት የሌለው ምናልባት ዘመኑ ስለማይጫጫን ይሆናል፡፡ አሁን ግን ይጫጫናል እያልን ነው፤ስለዚህ መፍትሄ የግድ ነው፡፡ በእርግጥ መፍትሄው ትኩስ ቡና ብቻ ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ትኩስ ቀልድ ሊሆንም ይችላል፤ ዋናው ነገር ከእንቅልፍና ከድብርት ስሜት ማነቃቃቱ ነው፡፡ ያለዚያ እኮ ጠ/ሚኒስትሩ ከስንት አንዴ ተገኝተው የሚያቀርቡት ሪፖርትና ማብራሪያ ከንቱ ሆነ ማለት ነው! (እንቅልፍ ወስዶት “ገና” እንዳመለጠው ትንሽ ልጅ!)  እናላችሁ --- አባላቱ ሁሉን ነገር በንቃት እንዲከታተሉ ከፈለግን coffee break ቢኖር አይከፋም፡፡ አሊያም ደግሞ አንድ ሁለት ሞቅ ያለ

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ ተመረጠች

- ውድድሩ አፍሪካና አውሮፓን አፎካክሯል በዓለም አቀፍ የቡና ግብይት ውስጥ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወቱት ቡና ገዥ ኩባንያዎችና አምራቾች በአባልነት የታቀፉበት ዓለም አቀፍ የቡና ድርጅት፣ ኢትዮጵያ አራተኛውን ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ መረጠ፡፡ እ.ኤ.አ. በማርች 2016 የሚዘጋጀውን ኮንፈረንስ ለማስተናገድ የመጨረሻው ውድድር ላይ ቀርበው የነበሩት ኢትዮጵያና ጣሊያን ናቸው፡፡ ምርጫው በተካሄደበት  ለንደን ከተማ ተገኝተው የነበሩ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት እንደገለጹት፣ ውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር የነበረበት ቢሆንም ኢትዮጵያ ልታሸንፍ ችላለች፡፡  በመጨረሻው ውድድር ላይ ከድምፅ ሰጪዎች መካከል ግዙፎቹ የአውሮፓ ቡና ገዥ ኩባንያዎች ድምፃቸውን ለጣሊያን ሰጥተው ነበር፡፡ አፍሪካውያንና ሌሎች ቡና አብቃዮች ደግሞ ለኢትዮጵያ ድምፅ በመስጠት ውድድሩ በአፍሪካውያንና በአውሮፓውያን መካከል እንዲሆን አድርገው ነበር ብለዋል፡፡ በተለይ በዓለም አቀፉ ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ ድምፅ ካላቸው አገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ብራዚል ድምጿን ለኢትዮጵያ በመስጠቷ ለኢትዮጵያ አሸናፊነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል፡፡ ከመጨረሻው ውድድር ቀደም ብሎ ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት ከአፍሪካ ኮትዲቯር፣ ጋቦንና ኬንያ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ሁሉም አገሮች የኢትዮጵያን የተወዳዳሪነት ጥያቄ በመቀበል ድምፃቸውን ሰጥተዋታል፡፡ ኮንፈረንሱ አፍሪካ ውስጥ መካሄዱ ትልቅ ዕድል ነው በማለት ለኢትዮጵያ ዕድሉ እንዲሰጣት አፍሪካውያኑ ድጋፍ እንዳሰባሰቡም በቦታው ከነበሩ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት ለመረዳት ተችሏል፡፡  ከዓለም የቡና ድርጅት (አይሲኦ) መካከል 50 በመቶዎቹ የቡና ገዥ ኩባንያዎች የሚወከሉባቸው አገሮች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ቡና አምራች አገሮች