የአና ጐሜዝና የኢህአዴግን “ፍቅር” እንመነው እንዴ?
“ወሬኛም ያውራ ሃሜት ይደርድር እኛስ ሆነናል ፍቅር በፍቅር ሊያፈርስ አስቦ የሸረበውን ተክቦ ሆኗል የሚያገኘው…” ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው! ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ፡፡ አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡ እንዴ … የ97 ምርጫ ጊዜ አና ጐሜዝ በኢህደዴግ ላይ የሰነዘረችው ትችትና ነቀፌታ “ዓይንሽ ላፈር” የሚያስብል ነበር እኮ! እናም ኢህአዴግ “ዓይንሽ ላፈር” ብሏት ነበር፡፡ (በዓይኑ መጣቻ!) ጊዜ ደጉ ግን ሁሉንም ገለባበጠው፡፡ በነገራችሁ ላይ በጐሜዝና በአፈጉባ