Posts

የሲዳማ ዞን ኣስተዳደር ለወጣቶች የስራ እድል ፈጥራለሁ ኣለ

በሲዳማ ዞን ዘንድሮ ከ72 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል   ሐዋሳ ህዳር 20/2006 በሲዳማ ዞን በተያዘው ዓመት ከ72 ሺህ የሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች በገጠር ስራ እድል ፈጠራ እና ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ ገለጹ፡፡ የዞኑ የገጠር ስራ እድል ፈጠራና ልማት ጽህፈት ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ ከግል ኮሌጆችና አስርኛ ክፍል ላጠናቀቁ ዜጎች ሰፊ የስራ እድል ተዘጋጅቷል፡፡ ሃገራዊም ሆነ ክልላዊ የምጣኔ ሃብታችን እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የገጠር ስራ እድል ፈጠራና ልማት እንቅስቃሴ ለማሳካት የሚያስችሉ ጠንካራ ስልቶች ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የባለድርሻ አካላት ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ ሀገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ለማሰለፍ በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ልማታዊ እንቅስቃሴዎች አንዱ ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባዋል ብለዋል፡፡ ለዘርፉ ወቅታዊ ድጋፍና ክትትል ማድረግ በግብርና የሚመራው ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገርና ልማታዊ ባለሃብቶችን ለመፍጠር ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ስራ አጥነትንና ድህነትን ለመቅረፍና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም መረባረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ የአመራርንና የባለሙያውን አመለካከት ከመቀየር አኳያ ከ100 ሺህ ለመበልጡ የዞን፣ የወረዳና ለቀበሌ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና

Opticians set sights on helping People near Hawassa

Image
An optician and lab technician from Ellesmere Port travel to Ethiopia this week to give vital aid to people who don’t have access to eyecare. Optometrist Alex Whitter and lab technician Mike Horsefield, who both work in the Ellesmere Port Specsavers store, will be travelling to villages near Hawassa to give much-needed eye tests and glasses to the locals. They aim to test at least 1,200 people. Working with Vision Aid Overseas (VAO), they will also be helping to train optometry students at Hawassa University. Another item on their agenda is to teach individuals to make their own glasses, to help the locals become self-sufficient and improve the level of eyecare in the area. This will be Alex’s sixth trip with the charity, and he is the team leader of the group, which consists of five optometrists from all over the UK. Mike will be glazing and dispensing the glasses. The visit will be Matt’s first VAO trip to Ethiopia and he is being sponsored by Specsavers. Store direct

''ከ1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ተስፋ ይታይበት የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ምህዳር በምርጫው ምክንያት በተፈጠረው ቀውስ ከምርጫው በፊት ወደነበረበት አስከፊ ሁኔታ ተመልሷል'' አና ጐሜዝ

Image
አና ጐሜዝ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን አደረግኩ አሉ ከዘጠኝ ዓመት በፊት በተካሄደው የግንቦት 1997ቱ ምርጫ የአውሮፓ ኅብረትን በመወከል የምርጫ ታዛቢ የነበሩት ፖርቱጋላዊቷ አና ጐሜዝ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ፡፡ ዛሬ በሚጠናቀቀው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ የመጡት አና ጐሜዝ፣ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የጋራ ስብሰባው ላይ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ የመጡት የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባልና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት አና ጐሜዝ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ምንም ዓይነት የቪዛ ችግር እንዳልገጠማቸው ገልጸው ይህም አዲስ ዓይነት የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡ ምንም እንኳን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላ በኢትዮጵያ የተለየ የፖለቲካ አተያይ አለ ያሉት አና ጐሜዝ፣ አጠቃላይ የፖለቲካው ምህዳር ግን ከ1997ቱ ምርጫ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የባሰ ነው የሚል አመለካከት አላቸው፡፡ «ከ1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ተስፋ ይታይበት የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ምህዳር በምርጫው ምክንያት በተፈጠረው ቀውስ ከምርጫው በፊት ወደነበረበት አስከፊ ሁኔታ ተመልሷል፤» በማለት መንግሥትን ተችተዋል፡፡ ለዚህም እንደ መከራከሪያ የሚያነሱት ከምርጫው በኋላ የወጡትን ሕጐች በምሳሌነት በማቅረብ ነው፡፡ «ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ሁሉም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት መታሰራቸው፣ የሲቪክ ማኅ

«የልፋታችንን ዋጋ አላገኘንም» - ቡና አምራች አርሶ አደሮች « ቡናን በጥራትና በብዛት ማምረት ግድ ነው» - የሲዳማ ዞን ግብይትና ኅብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ

Image
አርሶ አደሮቹ እንደሚናገሩት ቀደም ሲል አንድ ኪሎ እሸት ቡና እስከ  13  ብር ድረስ ሸጠው ነበር፤ አሁን ግን ተመሳሳይ መጠን ያለውን ቡና በአምስት ብር ብቻ ለመሸጥ ተገድደዋል፤ በሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ የአዋዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪው አርሶ አደር ተፋዬ ወቴ ከቡና ሌላ በማሳቸው እንስትም በቆሎም ያመርታሉ። ይሁንና ሰፋ ያለው መሬት በቡና የተሸፈነ ነው። ከዚህ መሬት በየዓመቱ የሚያገኙት የገንዘብ መጠን እንደ ቡና ገበያ ዋጋው መለያየቱን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ፤ቀደም ባሉት ጊዜያት የቡና ምርታማነት ከፍ ያለ ቢሆንም በመሀል ደግሞ መቀነስ ታይቶበታል። ነገር ግን በአካባቢው ያሉ የግብርና ባለሙያዎች የቡናን ችግኝም ሆነ ዛፍ እንዴት መያዝ እንደሚገባ በሰጡት ትምህርት አሁን ላይ ለውጥ ይታያል። ምርቱ ቢኖርም የገበያ ሁኔታው አሳሳቢ ሆኗል። በተለይ በተጠናቀቀውና በተያዘው ዓመት የቡና ዋጋ ከሚጠበቀው በታች ዝቅ ማለቱን የሚያመለክቱት አርሶ አደር ተስፋዬ ዘንድሮ አንድ ኪሎ እሸት ቡና በአምስት ብር ለመሸጥ መገደዳቸው የልፋታቸውን ዋጋ እንደሚያሳጣቸው ይገልፃሉ። ዋጋው ከፍና ዝቅ የማለቱ ጉዳይም እንዳሳሰባቸው ነው የሚጠቅሱት። « እኛ የምንፈልገው የተጋነነ ትርፍ አይደለም። ከሁለት ዓመት በፊት የነበረው የቡና መሸጫ ዋጋ ከአምናና ከዘንድሮው ይሻል ነበር። ቢያንስ አንዱን ኪሎ እሸት ቡና እስከ  13  ብር ድረስ ሸጠናል። ነገር ግን ትርፍ አጋብሰናል ማለት ሳይሆን ለድካማችን የተሻለ ዋጋ ነበር የሚያስብል ነው። ስለዚህም የክልሉና የዞኑ ቡና ግብይት በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግረው የልፋታችንን ዋጋ የምናገኝበትን መፍትሄ ቢያመቻቹ መልካም ነው »  ይላሉ አርሶ አደር ተስፋዬ። በአሁኑ ወቅት አንድ ኩንታል ጤፍ በአካባቢው በ 1 ሺ 300 

አምራቹ በቡና ዋጋ መቀነስ እንዳይጎዳ ማድረግ ያስፈልጋል

 ... ይህ በሲዳማ ቡና አምራቾች ላይ የተከሰተው ችግር የቡና ዋጋ በዓለም ገበያ ዋጋ የሚወሰን ከመሆኑ አኳያ የሌሎች ሀገሮች ቡና አምራች አርሶ አደሮችም ችግር ነው። ችግሩ ከቡና ጋር የጠበቀ ግንኙነት ላለውና ቡና ምግቡ፣ ልብሱ፣ መዝናኛው በአጠቃላይ የኑሮው ዋልታና ማገር ለሆነው የኢትዮጵያ ቡና አምራች ምን ያህል አሳሳቢ ሊሆን እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የቡና ዋጋ እየቀነሰ መምጣት በአስቸኳይ የሚፈታ ካልሆነ የቡና አምራቾች የልፋታቸውን ዋጋ ወደ ሚያስገኙላቸው ዘርፎች ፊታቸውን እንዲያዞሩ የሚያስገድድ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፤ የግብይት ህብረት ሥራ ማህበራትም ይህንኑ ስጋት እያረጋገጡ ናቸው። ሀገሪቱም ከቡና በከፍተኛ ደረጃ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሪ እንዲቀንስ የሚያደርግም ይሆናል። ችግሩ በቡና ልማቱና ግብይቱ ሰንሰለት የሚሳተፈውን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ኑሮ እንዲናጋ ያደርጋል። ኢትዮጵያ ለቡና ልማት በሰጠችው ትኩረት በቡና ተክል የተሸፈነው መሬትም ሆነ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። ቡና ከሚመረትባቸው ክልሎች በተጨማሪ በአማራና በትግራይ ክልሎች ጭምር ቡናን በማምረት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው። ለቡና አምራቾች ወሳኝ ግብዓቶችን በማቅረብ ጭምር ድጋፍ እየተደረገ ነው። አርሶ አደሩ ምርቱን በአቅራቢያው ለሚገኙ የራሱ የህብረት ሥራ ማህበራት እንዲያቀርብ የሚያስችል ሁኔታ በመፈጠሩም ምርቱ የደላሎችና ህገወጥ ነጋዴዎች ያለአግባብ መጠቀሚያ ከመሆን እየዳነ ነው። በአሁኑ ወቅት የቡና ግብይት የሚካሄድባቸው በርካታ የግብይት ማዕከላት ተቋቁመው እየሰሩ ናቸው። በተለይ አርሶ አደሩ ምርቱን ለህብረት ሥራ ማህበራት ማቅረብ በመቻሉ የቡና ዋጋ በሚወድቅበት ወቅት ምርቱን የሚያደ