«የልፋታችንን ዋጋ አላገኘንም» - ቡና አምራች አርሶ አደሮች « ቡናን በጥራትና በብዛት ማምረት ግድ ነው» - የሲዳማ ዞን ግብይትና ኅብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ
አርሶ አደሮቹ እንደሚናገሩት ቀደም ሲል አንድ ኪሎ እሸት ቡና እስከ 13 ብር ድረስ ሸጠው ነበር፤ አሁን ግን ተመሳሳይ መጠን ያለውን ቡና በአምስት ብር ብቻ ለመሸጥ ተገድደዋል፤ በሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ የአዋዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪው አርሶ አደር ተፋዬ ወቴ ከቡና ሌላ በማሳቸው እንስትም በቆሎም ያመርታሉ። ይሁንና ሰፋ ያለው መሬት በቡና የተሸፈነ ነው። ከዚህ መሬት በየዓመቱ የሚያገኙት የገንዘብ መጠን እንደ ቡና ገበያ ዋጋው መለያየቱን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ፤ቀደም ባሉት ጊዜያት የቡና ምርታማነት ከፍ ያለ ቢሆንም በመሀል ደግሞ መቀነስ ታይቶበታል። ነገር ግን በአካባቢው ያሉ የግብርና ባለሙያዎች የቡናን ችግኝም ሆነ ዛፍ እንዴት መያዝ እንደሚገባ በሰጡት ትምህርት አሁን ላይ ለውጥ ይታያል። ምርቱ ቢኖርም የገበያ ሁኔታው አሳሳቢ ሆኗል። በተለይ በተጠናቀቀውና በተያዘው ዓመት የቡና ዋጋ ከሚጠበቀው በታች ዝቅ ማለቱን የሚያመለክቱት አርሶ አደር ተስፋዬ ዘንድሮ አንድ ኪሎ እሸት ቡና በአምስት ብር ለመሸጥ መገደዳቸው የልፋታቸውን ዋጋ እንደሚያሳጣቸው ይገልፃሉ። ዋጋው ከፍና ዝቅ የማለቱ ጉዳይም እንዳሳሰባቸው ነው የሚጠቅሱት። « እኛ የምንፈልገው የተጋነነ ትርፍ አይደለም። ከሁለት ዓመት በፊት የነበረው የቡና መሸጫ ዋጋ ከአምናና ከዘንድሮው ይሻል ነበር። ቢያንስ አንዱን ኪሎ እሸት ቡና እስከ 13 ብር ድረስ ሸጠናል። ነገር ግን ትርፍ አጋብሰናል ማለት ሳይሆን ለድካማችን የተሻለ ዋጋ ነበር የሚያስብል ነው። ስለዚህም የክልሉና የዞኑ ቡና ግብይት በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግረው የልፋታችንን ዋጋ የምናገኝበትን መፍትሄ ቢያመቻቹ መልካም ነው » ይላሉ አርሶ አደር ተስፋዬ። በአሁኑ ወቅት አንድ ኩንታል ጤፍ በአካባቢው በ 1 ሺ 300