የቀድሞ ሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን (SDC) እህት የልማት ድርጅቶች የት ደረሱ?
የሲዳማ ዞን መንግስት በቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን እህት የልማት ድርጅቶች ላይ በያዘው የተሳሳተ ኣቋም ድርጅቶቹን ኣጠናክሮ ለታለሙለት ኣላማ እንድውሉ እና ስፊውን የሲዳማን ህዝብ እንድጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ ድርጅቶቹን እንደጠላት ንብረት በማየት የሚጠፉበትን እና የሚበተኑበትን ሁኔታዎችን ብቻ በማመቻቸት ላይ የተጠመዷል የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ የመንግስት ድጋፍ ያስፈልገዋል ክፍል ሁለት የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ ተቋም (SMFI) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፋቃድ ኣግኝቶ በራሱ ቦርድ የሚተዳደር የገንዘብ ተቋም ነው።ተቋሙ በከተሞች ኣካባቢ ቤትን እና ሌሎች ንብረቶችን በመያዝ ብድር የመስጠት ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን፤ እንደሌሎች መሰል የኣገሪቱ የብድር እና የቁጠባ ተቋማት ሁሉ ሰዎች በቡድን ተደራጅተው ገንዘብ የሚበደሩበትን መንገዶች በማመቻቸት ኣገልግሎት ይሰጣል። በኣገልግሎቱም እስከ ሃምሳ ሺ ነው የሚያበድር ሲሆን በግለሰብ ደረጃ ግን ከሶስት ሺ ብር በላይ ኣያበድርም። ለነገሩ በኣሁኑ ወቅት በኣገሪቱ ባለው የኑሮ ውድነት ብድሩን የሚወስዱ ሰዎች በሶስት ሺ ብር ምን ኣይነት ኢንቨስትመንት ልያደርጉ እንደምችሉ ግልጽ ባይሆንም ብዙዎቹ በገንዘብ ኣያያዝ ላይ ትምህርት ሳይሰጣቸው የብድሩ ተጠቃሚ ስለምሆኑ የተበደሩትን ገንዘብ ላላለሙለት ጉዳይ ላይ በማዋል እዳ ውስጥ ስገቡ ታይተዋል። ሰዎች የተበረሩትን ገንዘብ በውቅቱ ኣለመመለሳቸው ከብድር እና ቁጠባ ተቋሙ ጋር እንድካሰሱ ምክንያት ሆኗል። ጉዳዮቻቸው በፍርድ ቤቶች እየታየ ያሉ እና ቤት ንብረቶቻቸውን ሽጠው ለመክፈል የተገደዱ ብዙዎች ናቸው። ለማንኛውን ተቋሙ በኣሁኑ ጊዜ የብድር እና የቁጠባ ኣገልግሎትን በተዳከመ መልኩ በመስራት ላይ ይገኛል። ለሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ