በዘንድሮው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት 8 ከተሞች ሲዳማን ወክለው ይወዳደራሉ
ከህዳር 7 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በባህርዳር ከተማ በሚካሄደው የከተሞች ሳምንት ላይ ዞኑን በመወከል የሚሳተፉት የይርጋለምና አለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደሮች ለኩ ዳዬ ያዬ አለታ ጩኮ ወንዶ ኬላና መጪሾ ከተሞች ሲሆኑ የሲዳማ ዞን መንግስት በከተሞቹ የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና የመሰረተ ልማት ተቋማትን በማሟላት ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግበራት ህብረተሰቡ ተሳታፊ በመሆን የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ማበርከት ኣለበት ማለቱ ተሰምቷል። ዝርዝር ዜናው የኢዜኣ ነው። ሐዋሳ ህዳር 4/2006 በከተሞች የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና የመሰረተ ልማት ተቋማትን በማሟላት ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግበራት ህብረተሰቡ ተሳታፊ በመሆን የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት የሲዳማ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ አስታወቀ። አምስተኛውራ የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት በማስመልከት መምሪያው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሻሸመኔ 103 ነጥብ 4 ጋር በመተባበር በይርጋለም ከተማ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለጸው ባለፉት ዓመታት በከተሞች የመሰረተ ልማት ተቋማትን በማስፋፋት ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል። የሲዳማ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ለገሰ ማሬሮ እንዳሉት ከ1989 ዓ.ም በፊት በዞኑ የነበሩት 14 ከተሞች ምንም ዓይነት የመሰረተ ልማት ተቋማት ያልተሟላላቸውና ለኑሮ ምቹ ያልነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ በተፈጥሮ ያላቸውን ሀብት አልምተው ለመጠቀም በርካታ ችግሮች እንደነበሩባቸው ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በዞኑ በፕላን የሚመሩና የመብራት፣ የስልክ፣ የመንገድና ሌሎች አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ተቋማት የተገነቡላቸው 52 ከተሞች እንደሚገ