የገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞርት በዱላ ቅብብል ውድድር ይመረቃል
ማራቶን የማዘጋጀት ሃሳብ አላቸው በሀዋሳ ከተማ የተገነባውን ገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞርት ህዳር 14 በይፋ ሲመረቅ ልዩ የ10 ኪሎሜትር የዱላ ቅብብል ውድድር እንደሚካሄድ ታወቀ፡፡ በምረቃው ስነስርዓት ላይ በክብር እንግድነት እንዲገኙ ኡጋንዳዊው የኦሎምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮን የማራቶን ድርብ አሸናፊ ስቴፈን ኪፕሮች እና ኬንያዊ አትሌት ጄፈሪ ሙታይ ተጋብዘዋል፡፡ በሌላ ዜና ባልና ሚስቶቹ ማራቶኒስቶች አትሌት ገዛኸኝ አበራ እና አትሌት እልፍነሽ አለሙ በሚቀጥለው ዓመት አንድ የማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ማሰባቸውን ሲያስታወቁ ተተኪ አትሌቶችን ለማግኘት የአገር ውስጥ ውድድሮች መብዛታቸው አስፈላጊ እንደሆነ ስላመኑበት የነደፉት እቅድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አትሌት ገዛኸኝ አበራ እና አትሌት እልፍነሽ አለሙ ትናንት በዋና ፅህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ የሆቴልና ሪዞርት ምረቃው ከአትሌቲክስ ውድድር ጋር ማያያዝ ያስፈለገው ተተኪ አትሌቶች የእነሱን አርዓያ እንዲከተሉ ለማነሳሳት በማሰባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አትሌት እልፍነሽ አለሙ‹‹ ማንኛውም ሰው ዓላማዬ ብሎ ከሰራ ለየትኛውም ደረጃ ይደርሳል፡፡ በአሁን ዘመን ያሉ አትሌቶች ደከመን፣ ሰለቸን፤ ከሳን ፤ ጠቆርን ሳይሉ በትጋት መስራት አለባቸው፡፡ በስፖርቱ እኛ የደረስንበት ስኬት ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ከእኛ በላይ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው›› ብላለች፡፡ አትሌት ገዛኸኝ በበኩሉ ‹‹እኛ ሮጠን ሆቴሉን ሰርተናል፤ አትሌቱም እንደማንኛውም ህብረተሰብ በትጋት ከሰራ ይሳካለታል፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ በሆቴልና ሪዞርቱ ምረቃ ላይ የሚካሄደው የ10 ኪሎሜትር የዱላ ቅብብል ውድድሩ መነሻውና መድረሻው ገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞርት እንደሆነ የገለፀው አትሌ