ዩኤን ኤድስ 2030 የኤድስ ማብቂያ ሊሆን ይችላል አለ
የተባበሩት መንግስታት የኤድስ ድርጅት (UNAIDS) ከቀናት በፊት የለቀቀው ሪፖርት እ.ኤ.አ በ2030 ኤችአይቪ ኤድስ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችልበት ዕድል መኖሩን አስታውቋል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በህጻናትና አዋቂዎች አዳዲስ የኤችአይቪ ኢንፌክሽኖች ከ2001 ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ሶስተኛ ቀንሰዋል፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር 2.3 ሚሊዮን ሲሆን ይህ በ2001 ከታየው አዳዲስ ኢንፌክሽን 33 በመቶ መቀነሱን ያሳያል፡፡ በዚሁ ዓመት በቫይረሱ የተያዙ ህጻናት ቁጥር 260 ሺህ ሲሆን ከ2001 ጋር ሲነጻጸር የ52 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ የአዳዲስ ኢንፌክሽኖች ቁጥር የቀነሰው በስፋት እንዲዳረስ በተደረገው በፀረ-ኤችአይቪ መድሃኒት ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የፀረኤችአይቪ መድሃኒት ተደራሽነት ከ2005 ወዲህ በኤችአይቪ ምክንያት የሚደርስ ህልፈተ ህይወትም 30 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል፡፡ ከ2011 እስክ 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ 20 በመቶ ለሚሆኑት ሰዎች (9.7 ሚሊዮን) ፀረኤችአይቪ መድሃኒት ተደራሽ መሆኑን የዩኤን ኤድስ ዳይሬክተር ሚሼል ሲዲቤ ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ በ2015፤ 15 ሚሊዮን ሰዎችን የፀረ-ኤችአይቪ ተጠቃሚ ለማድረግ ግብ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በሪፖርቱ እንደተመለከተው በ2012 ዓለም ላይ ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ቁጥር 35.3 ሚሊዮን ነበር፡፡ ከኤችአይቪ ህክምና ጋር በተያያዘ የታዩ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን መሠረት በማድረግ የዩኤን ኤድስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሉዊስ ሎሬስ የኤችአይቪ ኤድስ ማብቂያ ከ2030 በፊት እንደሚሆን ግምታቸውን መስጠታቸውንም የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ ‹‹የኤችአይቪ ወረ