Posts

‘Fichche’ is the most celebrated Sidama cultural holiday which represents the Sidama New Year.

Image
Add caption ‘Fichche’ is the most celebrated Sidama cultural holiday which represents the Sidama New Year. The Fichche is based on the lunar system. Sidama elders (astrologists) observe the movement of the stars in the sky and decide the date for the New Year and the Fichche celebration. The Sidama New Year is therefore is unique in that it does not have a fixed date. It rotates every year following the movements of the stars. Sidama has 13 months in a year. And each of the months is divided equally into 28 days while the 13th month has 29 days. This is because the Sidama week has only 4 days and hence each month has 7 weeks instead of the conventional 4 weeks. The names of the 4 days in Sidama week are called: Dikko, Deela, Qawadoo and Qawalanka to be followed by Dikko completing the cycle of a 4-day week. Read more on   http://en.wikipedia.org/wiki/Socio-Economic_Status_of_Sidama_Zone

Documentary - Fiche - Sidama New Year

Image
Watch here:  http://www.ethiotube.net/video/15783/Documentary--Fiche--Sidama-New-Year

የዋጋ ንረት በነጋዴዎች እንደማይመጣ እንደገና በጥናት ተረጋገጠ

Written by  ዮሐንስ ሰ. ግን ደንታችን አይደለም፤ ነጋዴዎችን ከማውገዝ ለአፍታም አንቆጠብም! ታዋቂዋ የኢኮኖሚክስ ምሁር ዶ/ር ኢሌኒ ገብረመድህን በእህል ገበያ ዙሪያ ከ20 አመት በፊት ባደረጉት ሰፊ ጥናት የተገኘውን ውጤት በድጋሚ የሚያረጋግጥ አዲስ ጥናት ሰሞኑን በተካሄደው የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር ኮንፈረንስ ላይ ቀርቧል። ከጥናቶቹ ውስጥ ጎልቶ የሚታይ አንድ ሃቅ ቢኖር፣ በእህል ገበያ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችና ደላሎች በየፊናቸው ወይም ተመካክረው እንዳሻቸው የዋጋ ንረትን እንደማይፈጥሩ ነው። እንዲያውም፣ ነጋዴዎች የዋጋ ንረትን የሚፈጥርና ጉዳት የሚያደርስ ቅንጣት ያህል አቅም እንደሌላቸው ጥናቶቹ ያስረዳሉ። እንዲህ አይነቱ ሃሳብና መረጃ የማይዋጥላቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን፣ ከገበሬ እህል ገዝቶ የሚያመጣ ነጋዴ ከደላላ ጋር ሆኖ፣ ያሰኘውን ያህል ዋጋ እየጨማመረ በሰፊ ልዩነት የሚሸጥ ይመስላቸዋል። ከገበሬ የሚገዛበት ዋጋ ከወለል በታች በጣም ዝቅተኛ፣ ለሸማች የሚሸጥበት ዋጋ ደግሞ ከጣሪያ በላይ ከፍተኛ ነው ብለው ያምናሉ። ነጋዴው በሰፊ የዋጋ ልዩነት እጥፍ ሲያተርፍ፣ ከዚያም አልፎ የእጥፍ እጥፍ ዋጋ እየጨመረ ትርፍ ሲዝቅ በምናብ ይታያቸዋል። በተጨባጭ መረጃዎች እና በዝርዝር ጥናቶች ተደጋግሞ የተረጋገጠው እውነታ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ነጋዴዎች ከገበሬ እህል የሚረከቡበት ዋጋ እና ለሸማች የሚሸጡበት ዋጋ ሲነፃፀር፣ በሁለቱም መካከል ሰፊ ልዩነት እንደሌለ ጥናቶቹ ከመግለፃቸውም በተጨማሪ፣ የዋጋ ልዩነቱ ከአመት አመት በእጅጉ እየቀነሰ መምጣቱን ያስረዳሉ። ታዲያ በእነዚህ ጥናቶችና መረጃዎች ምክንያት የአብዛኛው ሰው አስተሳሰብ የሚቀየርና በነጋዴዎች ላይ የሚሰነዘረው ውግዘት የሚረግብ እንዳይመስላችሁ። ቀድሞውንም፣ በጥናቶችና በመረጃዎች እጦት አይደ

ተቃዋሚዎችም እኮ እየተሰደዱ ነው!

Written by  ኤሊያስ ዲሞክራሲው ያመጣው ነው እናላችሁ --- ኢቴቪ ያነጋገራቸው ምሩቃን በሙሉ “በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተን --- የዶሮ ወይም የንብ እርባታ አሊያም ኮብልስቶን እንሰራለን” ሲሉ ዋሉ (በከንቱ ነዋ ጥይት የባከነው!) እኔ የምለው ግን--- ዶሮ ለማርባት የአራት ዓመት ድግሪና ማስተርስ ምን ይሰራላቸዋል? ወይስ የዛሬ ድግሪና ማስትሬት እንደ 100 ብራችን በኢንፍሌሽን ተጠቅቷል! (ኢህአዴግ ቁምነገሩን ሁሉ ፖለቲካ እያደረገብን ተቸገርን እኮ!) የሆኖ ሆኖ ግን 40ሺ የጦቢያ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተመርቀዋልና “ኮንግራ!” ብለናቸዋል (ቢደራጁም ባይደራጁም!) ያለፈው ሳምንት ፌሽታ እንዴት ነበር? (አልገባንም እንዳትሉኝ ብቻ!) ስንት ሚኒስትሮች እንደተሾሙ ዘነጋችሁት ማለት ነው? (“ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም” ብትሉ አልሰማችሁም!) ከአስር በላይ ሹመት እኮ ነው የተሰጠው! ያውም የአዲስ አበባ ከንቲባና ሌሎች ሹመቶችን ሳይጨምር (በሙስና ከስልጣን መነሳቱም ቀጥሏል!) ፌሽታው ግን የሹመት ብቻ አልነበረም፡፡  የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ምርቃትስ? እሱም እኮ ከሹመት አይተናነስም፡፡ 40ሺ ገደማ ተማሪ እኮ ነው የተመረቀው፡፡ ችግሩ ግን ምን መሰላችሁ? ለኢቴቪ በሰጡት ቃለምልልስ አንዳቸውም እንኳን “በተማርኩት ትምህርት እንዲህ እፈጥራለሁ” ወይም “አንድ አዲስ ነገር እፈለስፋለሁ” የሚል የተስፋ ቃል አልሰጡንም (ምናለ ለአፋቸው እንኳ ቢሉት) አብዛኞቹ ከካድሬ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የወጡ ይመስል “ተደራጅተን --” እያሉ ሲናገሩ እኮ ነው የሰማነው፡፡ (“ተደራጅተን እንታገላለን” ግን አላሉም) ቢሉስ ከማን ጋር ነው የሚታገሉት? (ብድር ከሚሰጣቸው ፓርቲ ጋር? አይሞከርም!) በዚያ ላይ እኮ የዜጎች መብትና ነፃነት ከተከበረ 2O ዓመት ገደማ አለፈው

በደቡብ ክልል ከ12ሺህ 400 በላይ የባዪ ጋዝ ተቋማት ግንባታ እየተከናወነ ነው

ሃዋሳ ሐምሌ 27/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀዉ በጀት አመት የ12ሺህ 415 የባዮ ጋዝ ተቋማት ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ውሃ ሀብት ቢሮ አስታወቀ ። የቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለሙያ አቶ ጁሲ ጥላሁን ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የባዮ ጋዝ ተቋማቱ ግንባታ እየተካሄደ ያለዉ አማራጭ የሀይል አቅርቦትን ለህብረተሰቡ ለማዳረስ መንግስት በያዘው ፕሮግራም መሰረት ነዉ ። በተጨማሪ በክልሉ የተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች 193ሺህ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን በማሰራጨት ከ190ሺህ ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ። የባዮ ጋዝ ተቋማቱ የግብርና ተረፈ ምርቶችን በማብላለት ከሚወጣዉ ጋዝ በርካታ ቤተሰቦችን የመብራትና የምግብ ማሰያ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አገልጠዋል ። በክልሉ አማራጭ የሃይል አቅርቦት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በተደረገው ጥረት ባለፉት አመታት በተመሳሳይ በርካታ የገጠር ነዋሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታዉቀዋል ። ይህም ለማገዶና ለሀይል ፍላጎት እየተባለ የሚወድመውን የደን ሀብት ከመታደግ በሻገር የህብረተሰቡን የስራ ጊዜ ፣ ጉልበትና ወጪ ለመቆጠብ ከፍተኛ አስተዋጾኦ አድርጓል ብለዋል ። በደቡብ ክልል በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ታዳሽና አማራጭ የሀይል አቅርቦት በ2002 ከነበረበት 15 በመቶ ሽፋን ወደ 25 በመቶ ለማሳደግ ሰፋፊ ፕሮግራሞች ተነድፈው እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል ። በበጀት አመቱ ለኢነርጂና ለማእድን ልማት ጨምሮ የሚስፈልገው አጠቃላይ የማስፈጸሚያ በጀት ከ19ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን በእቅዱ ላይ ተመልክቷል፡፡