Posts

Signs of health and safety in Hawassa

Image
Busy with packing, goodbye lunches and dinners, etc., etc. So, I’ll quickly share some more public health signage from around campus and downtown Awassa. There are a few variations of this sign located throughout campus, including one with a quote from Helen Keller, “Disability is a reality for me, but a possibility for all.” located at the main entrance of Hawassa University main campus vaccinate! The billboard below emphasizes that ones financial situation should be an important part of family planning. family planning Some of the billboards are very graphic so as to get their point across. anti female genital cutting sign Here’s a sign promoting the use of crosswalks, or zebras as they call them. Unfortunately, it is rare for a car to actually stop for a pedestrian in the crosswalk, so they are less effective than they could be. I always thank my bajaj driver when he actually stops to let a pedestrian pass. Source:  http://awayinawassa.wordpress.com/

HwU hands over a Poultry Center it establishes at Hulla District

Image
It has been two years since HwU established technology villages to manage the research activities in an organized manner, test improved findings down on farmers’ field and smoothen technology transfer to the society. The villages are located in 6 different districts of Sidama Zone. Hulla District is one of these 6 villages where HwU funded poultry center inaugurated on June 22, 2013. The poultry center has been handed over to an association named ‘Birhan’ formed by 24 unemployed youth local residents.  According to a report read on the inaugural ceremony, the poultry center costed HwU more than 350,000ETB without considering the professional and laborious contributions. Therefore, the University provided the center with 1210 hens, feedings for 3 months and 20 cages. HwU also covers a lodging expense of the youth during their stay in Hawassa to receive training in the University and their transportation. Speaking on the occasion, Dr. Tesfaye Abebe, Director Research and Development a

በሀዋሳ ከተማ ዘንድሮ ከ33 ሺህ በላይ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆኑ

Image
አዋሳ ሰኔ 24/2005 በሀዋሳ ከተማ በዘንድሮ የበጀት አመት ከ33 ሺህ በላይ ወጣቶችና ሴቶች የቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት ድጋፍ ማዕቀፍ አፈጻጸምና ክትትል ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኤፍሬም አለማየሁ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ወጣቶችና ሴቶች የሥራ እድል ተጠቃሚ የሆኑት በማኒፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ፣ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎትና በንግድ ስራ ዘርፎች ተደራጅተው በተደረገላቸው ሁለገብ ድጋፍ ነው፡፡ ከተጠቃሚዎች መካከል 11ሺህ 612 ሴቶች መሆናቸውን አስተባባሪው ገልፀዋል፡፡ የሥራ እድል ተጠቃሚ የሆኑት እነዚሁ ወጣቶችና ሴቶች ከ17 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በላይ እንዲቆጥቡ መደረጉንም አመልክተዋል፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት ዋና የስራ ሂደት አሰተባባሪ አቶ ውቤ ቤላሞ በበኩላቸው ከ18 ሺህ 600 ለሚበልጡ አንቀሳቃሾች የንግድ ስራ አመራር፣ የቴክኒክ ሙያ ፣ የምክር አገልገሎት፣ የተስማሚ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ድጋፍ መሰጠቱን ጠቁመው ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ የብድር ገንዘብ በመከፋፈል እንዲጠናከሩ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ለሌሎች 7 ሺህ 772 አንቀሳቃሾች ደግሞ ከ186 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስሰርና ገቢ እንዲያገኙ መደረጉን በመምሪያ የማምረቻ ማዕከላት ግንባታ ማስተዳደርና የገበያ ልማት ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አለማየሁ አብርሀም አስረድተዋል፡፡ የተፈጠረው የገበያ ትስሰርና ገቢውን ያገኙት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ባዛርና አውደርኢ በማዘጋጀት፣ በኮብል ስቶንና በሌሎችም የግንባታ ስራዎች ቅድሚያ ዕድል እንዲያገኙ በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም 18 ሺህ 526 ካሬ

ታላቁ ሩጫ ለኃይሌ ገብረሥላሴ ማራቶን አሸናፊዎች 340 ግራም ወርቅ አዘጋጀ

Image
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመጪው ጥቅምት 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ በሚካሄደው የመጀመርያው የኃይሌ ገብረሥላሴ ማራቶን አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 340 ግራም ወርቅ እንደሚሸልም አስታወቀ፡፡ ታላቁ ሩጫ ከአሜሪካው ሞሬ ማውንቴን ስፖርት ጋር በመተባበር ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ ስለሚያካሂደው የማራቶን ውድድር በሰጠው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ትልቁን ሽልማት ለአሸናፊ ወንድና ሴት አትሌቶች ያቀረበ መሆኑንና አሸናፊዎቹ እያንዳንዳቸው 340 ግራም ወርቅ (12 አውንስ) ወርቅ ተሸላሚ ይሆናሉ ብሏል፡፡ ‹‹ኃይሌ ገብረሥላሴ ማራቶን›› ተብሎ በየዓመቱ የሚካሄደው ውድድር የመጀመርያው ሕዝባዊ ማራቶን እንደሚሆንና ከዋናው ማራቶን በተጨማሪ ግማሽ ማራቶን፣ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫና የልጆች ሩጫንም ያካትታል፡፡ ይህን ልዩ የሩጫ ዝግጅት አሸናፊዎች ብቻ ሳይሆኑ 12 ዕድለኛ ተሳታፊዎችም በልዩ ዕጣ እያንዳንዳቸው አንድ አውንስ (28 ግራም) ወርቅ ይሸለማሉ፡፡ ተባባሪ አዘጋጁ ሞሬ በሐዋሳው ውድድር ከመላው ዓለም ተሳታፊዎች እንዲመጡ ለማድረግ በበርሊን፣ ቺካጎ፣ ኒው ዮርክ ማራቶኖች የቅስቀሳ ሥራ ማድረጉም እስካሁን ባለው ምዝገባ ከ20 አገሮች ከ100 በላይ ተሳታፊዎች መመዝገባቸውንም አስታውቋል፡፡ እንደመግለጫው፣ ሐዋሳ ከተማ ባሏት ሰፋፊ መንገዶችና መልክአ ምድራዊ አቀማመጧ ዳገት ቁልቁለት ያልበዛባትና ለጣማነት ስላላት ከባሕር ወለል በላይ ያላት አቀማመጥ ለማራቶን ተመራጭ አድርጓታል፡፡ በተያያዘ ዜና የ2006 ዓ.ም. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር ዓለም አቀፍ ውድድር ምዝገባ ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. መጠናቀቁን አዘጋጁ ክፍል አስታውቋል፡፡ ተሳታፊዎች ትጥቃቸውን የሚረከቡት ውድድሩ አራት ቀን ሲቀረው ከኅዳር 11-14/2006 ዓ.ም. በኤግ

የስምንት ሚኒስትሮች ሹመት ሰሞኑን ይፀድቃል

 የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ዛሬ ግምገማ ያካሂዳል የኢህአዴግ 36 ከፍተኛ መሪዎችን ያካተተው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመታዊ ግምገማ ለማካሄድ ዛሬ የሚሰበሰብ ሲሆን የስምንት ሚኒስትሮች ሹም ሽርና ሽግሽግ በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡ ለሹመት የሚቀርቡት ባለስልጣናት፤ የፍትህ ሚኒስትር፣ የከተማና ኮንስትራክሽን ልማት ሚኒስትር፣ የግብርና ሚኒስትር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የገቢዎች ሚኒስትር የደህንነትና መረጃ ሚኒስትር፣ የደንና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ናቸው ተብሏል፡፡ አንዳንዶቹ ሹምሽር እርምጃዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር እንዲዛወሩ በተደረጉ ባለስልጣናት ምትክ የሚካሄድ ሽግሽግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የእጩ ተሿሚዎችን ማንነት ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ዛሬ የሚካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከሹምሽሩ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ቢታሰብም፣ የሰብስባው ዋና ርዕሰ ጉዳይ አመታዊ ግምገማና አመታዊ እቅድ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት አስፈፃሚ አካል የመቆጣጠር ስልጣን ያለው የአገሪቱ ፓርላማ ጠንካራ የቁጥጥር ሃላፊነቱን በተግባር ማሳየት እንደጀመረ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጭምር ቢናገሩም፤ በሚኒስትሮች ሹመት ዙሪያ ግን የቀድሞው አሰራር አልተሻሻለም፡፡ በተለያዩ ዲሞክራሲያዊ አገራት ውስጥ የእጩ ሚኒስትሮች ማንነት በይፋ ታውቆ ለበርካታ ሳምንታት በፓርላማና በዜጐች ዘንድ ውይይት የሚካሄድበት ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን የተሿሚዎች ማንነት የሚገለፀው ሹመታቸው በሚፀድቅበት እለት ነው፡፡ የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የገለፁት የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ የስብሰባው ዓላማ የዓመቱን የስራ አፈፃፀ