የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ የህብረተሰብ አገልግሎትን ለማጠናከር እየሰራ ነው ይላል
አዋሳ ግንቦት 22/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የህብረተሰብ አገልግሎትን እንደ መደበኛ ፕሮግራሙ በማቀፍ የምርምር ውጤቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ስራውን አሰፋፍቶና አጠናክሮ መቀጠሉን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ገለጹ፡፡ ዩኒቨርስቲው ለስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶች በዘመናዊ የዶሮ እርባታ ዙሪያ ያዘጋጀው ስልጠና ትናንት በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ ስልጠናውን የከፈቱት የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚደንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት የመማር ማስተማር ስራቸውን ከምርምር ጋር አቀናጅተው ያገኟቸውን አዳዲስና ችግር ፈቺ ውጤቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ስድስት የቴክኖሎጂ መንደሮች ተቋቁመዋል፡፡ የህብረተሰብ አገልግሎትን እንደ መደበኛ ፕሮግራማቸው በማቀፍ በምርምር የተገኙ የግብርና፣ የጤናና ሌሎችን ውጤቶችን በተለይ ስራ አጥ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ስልጠናዎችንና የመስሪያ ግብአቶችን በማሟላት ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ብቻ በደን ልማትና ችግኝ እንዲሁም በእንጉዳይ አመራረትና አጠቃቀም ላይ ከሀዋሳ ከተማና ከሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ ለተወጣጡ በርካታ ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን አመልክተው አሁንም ለ24 ወጣቶች በዘመናዊ የዶሮ እርባታ ዙሪያ ስልጠና አዘጋጅተው እራሳቸውን ችለው በተመሳሳይ ለሌሎችም የሚበቁበት የአቅም ግንባታ ድጋፍ አያደረጉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን እናበረታታለን ያሉት ዶክተር ዮሴፍ ዩኒቨርስቲው አጠቃላይ የትምህርት ተቋም እንደመሆኑ ሌሎችንም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የምርምር ውጤቶችን ለህብረተሰቡ በማሸጋገር ተጠቃሚ ለማድረግ ስራቸውን በሁለገብነት አስፋፍተውና አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው የምርምርና ልማት ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ አበበ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ተጠ