ፋና ብሮድ ካስት ኮርፖሬት ሻሸመኔ ኤፍ ኤም 103 ነጥብ 4 በሲዳምኛ ቋንቋ የሬዲዮ ስርጭት መጀመሩንም አብስሯል፡፡
አዋሳ ግንቦት 21/2005 የግንቦት 20 የድል በዓል የሀገሪቱን ታሪክ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አኩሪ የትግል ውጤት መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ገለጹ፡፡ ፋና ብሮድ ካስት ኮርፖሬት ሻሸመኔ ኤፍ ኤም 103 ነጥብ 4 ከሲዳማ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር የግንቦት 20ን በዓል ትናንት በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ፕሮግራሞች አክብሯል፤ በሲዳምኛ ቋንቋ የሬዲዮ ስርጭት መጀመሩንም አብስሯል፡፡ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሺፈራው ሽጉጤ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የዘንድሮው የግንቦት 20 በዓል ትግሉን በመምራት ለድል ያበቁት ታላቁ መሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን በሞት በተለዩን ማግስት የሚከበር በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ እሳቸውን ብናጣም የሀገራቸንን ታሪክ ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር ራዕያቸውንና የህዳሴ ጉዞችንን ለማሳካት ጠንካራ መሰረት በመጣል የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አኩሪ የትግል ውጤት እንዳለ አስረድተዋል፡፡ ሀገሪቱ ከጨለማው ዘመን በመውጣት በአሁኑ ወቅት የቡድንና የግለሰብ መብት ከመረጋገጡም በላይ በተለይ በትግል ወቅትና ከዚያም ወዲህ እንደሚዲያ የህዝብ ድምጽ በመሆን ሲያገለግል የቆየው የፋና ብሮድ ካስት ኮርፖሬት የግንቦት 20 ሌላው የድል ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፋና የስርጭት አድማሱን በማስፋት ተደራሽ ከሆነባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች በተለይም በሲዳምኛ ቋንቋ አሁን የጀመረው ፕሮግራም ቀጥሎ 17 ሚሊዮን ለሆነው የደቡብ ክልል ህዝብ በተመሳሳይ እንዲሰራ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እንሚያደርግ በማረጋገጥ እሰካሁን ላደረገው አስተዋጾኦ አመስግነዋል፡፡ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የሲዳማ ህዝብ እንደሌላው ጭቁን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የግንቦት 20 የድል ውጤ