Posts

Sidama - Religion and Beliefs

Image
Photo by http://commonriver.files.wordpress.com/2013/01/sr-under-tree1.jpg Introduction to Sidama Religion by Kifle WANSAMO (culled from www.sidamaconcern.com/country/religion_and_beliefs.htm )   1. Introduction 2. Elements of faith in the Sidama religion Belief in God Belief in spirits Belief in ancestors 3. The elements of Response in the Sidama Religion Morality   Prayer & sacrifice Sacrifice Offered to Magano     Sacrifice Offered to the Ancestors   Offering Places 4. Conclusion Endnotes About the author 1. Introduction This paper results from the

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛው ስብሰባውን ዛሬ ግንቦት 3/2005 ዓ.ም እያካሄደ ነው፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በዚሁ ስብሰባው በያዝነው አመት የተሰሩ በክልሎች የከተማና የገጠር ሪፖርት እንዲሁም የገጠር እና የከተማ ሱፐርቪዥን ሪፖርት ላይ ይወያያል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአጀንዳው ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል በሚያዝያ ወር በተካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫ አፈጻጸምን በተመለከተ ይመክራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎችን ወደ አባላት እና ወደ ተለያዩ አካላት ለማድረስና ውሳኔዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይ ሁለት አመታት የሚከናወኑ መሰረታዊ ተግባራቶችን ይዳስሳል፡፡ በወቅቱ ከቤቱ በሚነሱ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን ያጠቃልላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምንጭ-የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ምክር ቤት ፅ/ቤት

አመራሩ የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከምንጩ ለይቶ መታገል ይገበዋል-የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር

Image
አዋሳ ግንቦት 01/2005 የኪራይ ስብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከምንጩ በመለየት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አመራሩ መረባረብ እንዳለበት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አሳሰቡ፡፡ በክልል የሚገኙ ከአንድ ሺህ በላይ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በከተሞች የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰራዊት ግንባታ አፈፃፀም ያለበት ሁኔታና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ላይ ለሁለት ቀን ያካሄዱት ውይይት ትናንት ማምሻው ተጠናቋል፡፡ ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በከተሞች የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አንድ በአንድ ለይቶ በማውጣት ለህብረተሰቡ ተገቢውን ምላሽ መስጠት የአመራሩ ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ በየከተሞች ጎልቶ እየታየ ለመጣው የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዋናነት ተጠያቂው አመራሩ በመሆኑ እነዚህን ችግሮች ሌት ከቀን በመረባረብ መፍታት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የከተማ ነዋሪዎች ለልማት ስራዎች ያላቸውን ፍላጎትና መነሳሳት አደራጅተውና አቀናጅቶ በመምራት፣ ይህን የልማት አቅም የመጠቀም ውስንነት በአመራሩ ዘንድ በሰፊው የሚታዩ ችግሮች ስለሆነ በፍጥነት ተፈቶ ወደ ስራ መገባት አለበት ብለዋል፡፡ በከተሞች ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ ያሉ ስራዎችን አንድ በአንድ የመፈተሽ፣ በልማት ሰራዊት የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን በየቀኑ የመከታተል፣ እንዲሁም ለስራው ስኬት የሚያግዙ ግብአቶችን በወቅቱ የማቅረብ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በከተሞች የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ዓለማ ለማሳካት የዜጎች፣ የባለሙያዎች፣ የባላሃብቶችና የአመራሮች መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ የሚጠይቅ ቢሆንም አመራሩ የመሪነት ሚናውን በተገቢው መንገድ ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ጠንካራ የልማ

አማራጮች ያልቀረቡበት የዘንድሮ ምርጫ!

“ምርጫዎች ቀን ቆጥረው ይመጣሉ፤ ውጤቱን እንዲለውጡ ግን አንፈልግም” ሶሻሊስቶች ለህዝብ ጥቅም በሚል ሰበብ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚሹት በዲሞክራሲያዊ መንገድ አይደለም፡፡ በዚህም ሳቢያ ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ አይዋጥላቸውም፡፡ ተፈጥሯዊ ባህርያቸውም አይደለም፡፡ የእነሱ ዝነኛ ብሂል “የትም ፍጪው [ስልጣኑን] አምጭው” የሚል ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገራችን በሚካሄዱ ምርጫዎች፣ ምርጫ ቦርድና አስፈጻሚዎቹ ለምርጫ ሕጎችና አሰራሮች አልፎ ተርፎም ለመርሆዎች ተገዢ አለመሆናቸውና ለጉዳዩ ትኩረት መንፈጋቸው ሳያንስ፣ ገዢው ፓርቲ በገሃድ “ተቃዋሚዎች መጡም አልመጡም ግድ የለንም” እስከማለት መድረሱ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ፈታኝ ጥያቄ ነው፡፡ የምርጫ ቦርድና የአስፈጻሚዎቹ ትኩረት፣ አማራጭ ሃሳቦች አብብው ሕዝብ በአማራጭ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ማገዝ ሳይሆን እንደ ዓመታዊ በዓል ቀን ቆጥሮ ምርጫውን በማንኛውም ኪሳራ(At any cost) ውስጥ ማስፈፀም እየሆነ የመጣ ይመስላል ፡፡ ይህ አካሄድ የሚጠቁመን ነገር ቢኖር ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደ የመጣው ሃቀኛ ዴሞክራሲ ሳይሆን የመንግስታዊ ከበርቴና የልማታዊ መንግስታት አስተሳሰብ መሰረት የሆነው የተምሳሌታዊ ዴሞክራሲ መሆኑን ነው፡፡ መጀመርያ ተቃዋሚዎችን ከነአቤቱታቸው በማስወገድ፣ ቀጥሎ በምርጫው አካሄድና ወግ አልባነት የተቆጣውን መራጭ ሕዝብ፣ ከቁጣው ለማብረድና እምነቱን በተጽእኖ ለማስለወጥ፣ ቤት ለቤት በሚያደርጉት መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳና ወከባ ማስጨነቃቸው፣ የፈለጉት የሕዝቡን “የይስሙላ ተሳትፎ” እንጂ ውጤት የማስለወጥ ሕጋዊ መብቱን እንዳልሆነ አይተናል፡፡ ልማታዊ መንግስታት፣ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የመሸነፍና የለውጥ ጥያቄ እንዲነሳባቸው አይፈቅዱም፡፡ ለዚህ ሲባልም የምርጫ ውድድር ቀንን ጠብቆ ምርጫ

የአካባቢ ምርጫ ትኩረት ነፋጊዎች

በኢትዮጵያ አምስት ዓይነት ምርጫዎች ይካሄዳሉ፡፡ እነዚህም ጠቅላላ ምርጫ፣ የአካባቢ ምርጫ፣ ማሟያ ምርጫ፣ ድጋሚ ምርጫና ሕዝብ ውሳኔ ይሰኛሉ፡፡ በያዝነው ወር ሚያዝያ 6 እና 13 ቀን 2005 ዓ.ም. የተካሄደው የአካባቢ ምርጫ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ከተወዳዳሪዎች አለመመጣጠን የተነሳ ብቻውን ተወዳድሯል የሚባለው ኢሕአዴግ ምርጫው ሳይደረግ ውጤቱን ያውቀዋል፡፡ የአካባቢ ምርጫ በቅድመ ምርጫው፣ በምርጫው ዕለትና በድኅረ ምርጫው ትኩረት እንዲነፈግ ያደረጉት ዓበይት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? የአካባቢ ምርጫ በየደረጃው በሚገኙ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ፣ የማዘጋጃ ቤት፣ የክፍለ ከተማ ወይም የቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡ በመላው አገሪቱ የተካሄደው ምርጫ ከኢሕአዴግ ውጪ የብዙ ዜጎችን ትኩረት እንዳላገኘ የተለያዩ መገናኛ ብዙኀን የዘገቡ ሲሆን፣ ከዚህ በተቃራኒ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ምርጫውን ‹‹ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምሳሌ የሚሆን›› ሲሉ ነው የገለጹት፡፡ ለዚህ ድምዳሜ ፕሮፌሰሩን ያደረሳቸው ምክንያት ደግሞ ምርጫው ሰላማዊና የተሳካ መሆኑ፣ እንዲሁም የዜጎች ንቁ ተሳትፎ ከሁሉም አቅጣጫ የተረጋገጠበት መሆኑ ነው፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ የፖለቲካ ተንታኞችና የጥናት ውጤቶች ግን ከምርጫ ቦርድ ይፋዊ አቋም በተቃራኒ የአካባቢ ምርጫዎች ካላቸው መጠነ ሰፊ ጠቀሜታ አኳያ የተሻለ ትኩረት እንዲያገኙ አገሪቱ ቅድሚያ ሰጥታ ልትሠራበት እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ የዕጩዎች ብዛት፣ የግንዛቤ ችግር፣ የፌዴራል መንግሥት ጫና፣ የፖለቲካ ባህልና የፖለቲካ ፓርቲዎች ደካማ ይዞታን በአንኳር ምክንያትነት የሚያነሱት አስተያየት ሰጪዎች እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ከሕግ